ደጉ ሳምራዊነት/Degu Samrawi

ደጉ ሳምራዊነት/Degu Samrawi በጎነት ለራስ ነውና ለተቸገሩ ወገኖች የምንችለውን በማድረግ ደስታ እንፍጠር

ዛሬ ገንዘብ ልመና አይደለም አመጣጤ የቀና ልቦና እና የጊዜ እንጅ ግን እስከመጨረሻው ይነበብ ሸር ሸር ሸር አድርጉልንመሰሉ እንዳልክ ይባላል የ22 አመት ወጣት ሲሆን 9ኛ ክፍል እያለ ድንገት...
17/09/2025

ዛሬ ገንዘብ ልመና አይደለም አመጣጤ የቀና ልቦና እና የጊዜ እንጅ
ግን እስከመጨረሻው ይነበብ
ሸር ሸር ሸር አድርጉልን
መሰሉ እንዳልክ ይባላል የ22 አመት ወጣት ሲሆን 9ኛ ክፍል እያለ ድንገት ታሞ ከትምህርት ገበታ ቀረ በኋላም በህክምና ቢረዳም መድሐኒት መውሰድ ላይ የሚቆጣጠረው በማጣቱ የተነሳና በተስፋ መቁረጥ ወደ መጠጥ በመግባት መድሐኒቱን አቋርጦ ዛሬ በቀላሉ መዳን የሚችል ወጣት በሰንሰለት ታስሮ በቤት ተቀምጧል። ዶክተሮችን ቤት ወስጀ ለማሳየት ሞከርሁ እናም በህክምና ቋንቋ የህመሙን አይነት Schizophrenia with psychotic feature plus Epilepsy(የአዕምሮ ጤና ችግር እና የሚጥል በሽታ በጋራ) በሚል ገልፀውልኛል
በመድሐኒት መከታተል የሚቻል ቢሆንም ከልጁ ከጎኑ ሰው አለመኖርና ጠባቂ ማጣት መድሐኒቱን በተገቢው አለመውሰድ ወደ ከፋ ደረጃ ያደርሰዋል የሚል ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጠዋል።
በመሆኑም ይህንን ወጣት ከአንድ ደካማ እናቱ ጋር ተነጋግረን የተደረሰበት ውሳኔ በአዲስ አበባ የአእምሮ ማገገሚያ ቦታ በተለይም መቄዶንያ; ጌርጌሶን እና መሰል በጎ አድራጎት ማህበራትና ማገገሚያ ቦታዎች ሂዶ መቀመጥ ቢችል በቀላሉ ለውጥ ማምጣት የሚችል በመሆኑ እስኪ አዲስ አበባ ያላችሁ ወንድም እህቶቼ ማገገሚያ ቦታ የምታውቁ ካላችሁ አለያም አፈላልጋችሁ አለያም ስልክ ካወቃችሁ በውስጥ መስመር ላኩልንና እና ልጁ ለተወሰኑ ጊዚያት አብሮ የሚቆይበትን እድል እንፍጠርና እንታደገው
ለበለጠ መረጃ 0952346172

በእለት እመቤታችን በጭንቅ የመድረስ ጥሪ   እናታችን እብስቴ አያሌው  ይባላሉ የሚኖሩት ደምበጫ ከተማ 01 ቀበሌ  ልዩ ስሙ ቁሮ ሰፈር በአንዲት የቀበሌ ቤት ውስጥ ሲሆን የ4ልጆች እናት ናቸ...
27/08/2025

በእለት እመቤታችን በጭንቅ የመድረስ ጥሪ

እናታችን እብስቴ አያሌው ይባላሉ የሚኖሩት ደምበጫ ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቁሮ ሰፈር በአንዲት የቀበሌ ቤት ውስጥ ሲሆን የ4ልጆች እናት ናቸው የሚተዳደሩት ጠላ በመሸጥ የነበረ ሲሆን በአደረባቸው የጡት እብጠት ህመም ህክምና ቢከታተሉም ለውጥ ባለማግኘታቸው ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ሲታዩ ጡታቸው ላይ #የካንሰር ምልክት እንዳለና ወደ ሌላው ሰውነት ሳይሰራጭ ጡታቸው መቆረጥ አለበት በሚል ወስኖ ቀጠሮ ሰጦ ሰዷቸዋል።
ስለሆነም እኝህ እናት በህመሙ ምክንያት ስራ ያቆሙ በመሆናቸው ከርሃብ ጥሙ በተጨማሪ ለህክምና ምንም አይነት አቅም ዘመድ የላቸውምና የእናንተን ፊት ለማየትና ለመጠየቅ መጣሁ እናም የቁሮ ሰፈር ልጆች የቅዱስ ሚካኤል ልጆች በያላችሁበት በማስተባበር አግዛችሁ ሌሎቻችንም ሁሌም የበጎነት ጥያቄ ሲነሳ እጃችሁን የምትዳብሱ እህት ወንድሞቼ በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭው አለም ያለን ደግሞ የምንችለውን አድርገን እናታችንን ከዚህ ክፉ እና ህይወት ቀጣፊ የካንሰር በሽታ ወደ ሰውነታቸው ሳይሰራጭ እና ለሞት ሳይዳርጋቸው እንታደጋቸው
አካውንት ቁጥር #1000367890332 ከተማ አያሌው(ልጅ)
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0952346172
0941504150
ደረሰኝ በውስጥ ላኩልኝ

  አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ ካደለችን መልካም ገጾች መካከል፥ የሰው ልጆች አብሮነታቸውን የሚያጸኑበት የመደጋገፍ ባህላችን ነው። ያጣውን ማገዝ፣ የተቸገረውን መርዳት፣ የታመመውን ማሳከም የሰው የ...
19/08/2025


አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ ካደለችን መልካም ገጾች መካከል፥ የሰው ልጆች አብሮነታቸውን የሚያጸኑበት የመደጋገፍ ባህላችን ነው። ያጣውን ማገዝ፣ የተቸገረውን መርዳት፣ የታመመውን ማሳከም የሰው የኑሮ አንዱ ገጽ ነው፡፡ ለዚህ ሰናይ ምግባር እውን መሆን ደግሞ የተመረጡ ደጋግና ቅን ልቦች በየአካባቢውና በየቦታው አይጠፉም ሁሌም “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ” ነው በማለት በቅን ልቦና የሚያካፍሉ ለመልካም ስራ አይረፍድም ብለው ሁሌም ለተቸገረ ለመድረስ እግራቸውም ሆነ እጃቸው የፈጠነ ወንድም እህቶቼ ብዙዎችን ከርሃብ ብሎም ከህመማቸው እንዲታከሙ አድርገዋል።
እስኪ የፋሲካ በአል እንዳደረግነው ለአዲስ አመት ዋዜማ በየአለንበት ከየጓደኞቻችን ጋር ተነጋግረን በማህበርም ይሁን በተናጠል እዛው በየአለንበት በምንችለው አቅም ልክ አሰባስበን በአይነት (ጤፍ : በቆሎ; የተዘጋጀ ደውቄት); አለያም በገንዘብ ብሎም በአልባሳት መደገፍ ብንችል በሚል አስበናልና ከወዲሁ በምንችለው አቅም ልክ እንድረስላቸው እንላለን
ፍሬ ደምበጫ በጎ አድራጎት ማህበር

13/08/2025


በኑሮ ሂደታችን እግዚአብሔርን መጠበቅ አደከመን ብለን ተስፋ የቆረጥን
#ይከፈታል ብለን የጠበቅነው በር ክርችም ብሎ ቢዘጋ
#ሰዎች በእኛ ላይ እለት እለት ዱላቸውን ቢያከብዱብን
#ስጋዊ ጤንነታችን እንኳ ቢናጋና በህመም ብንያዝ
#በጊዜው ነገሮች ሁሉ ቢያስፈሩን ቢከብዱብን
በውስጣችን ጥያቄ የፈጠረብን እግዚአብሔር ግን ለምን? ብለን ተስፋ የቆረጥን አይዟችሁ እግዚአብሔር ከአዕምሮ በላይ መልስ አለው
#አንተ ተስፋ ስትቆርጥ እርሱ ገና ስራውን እየጀመረብህ ነው እንጅ እግዚአብሔርማ
@አንተ ማንም አይወደኝም ስትል ; እኔ እወድሃለሁ ይልሃልዮሐ 3:16
@ምንም ማድረግ አልችልም ስትል በእኔ ማድረግ ትችላለህ ይልሃል ዮሐ 15:5
@ነገሮችን ማሳካት አልችልም ስትል ; በስራህ ሁሉ አብሬህ አለሁ ይልሃል ኢያሱ 1:4
@ብቸኝነት ይሰማኛል ስትል አልለቅህም ከቶ አልተውህም ይልሃል ዕብ 13:5
ስለሆነም ከእኛ ሃሳብ ይልቅ የእግዚአብሔር ሀሳብ የተመረጠ ነውና በተስፋ መጠበቅ ይገባል። ለዛም ነው በለሷን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል:ጌታውንም የጠበቀ ይከብራል የተባለው

  ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ መንፈሳዊ ጥንካሪያችን እንዳለ ሁሉ ድክመትም ይታይብናልብዙዎች ጠንካራ የነበሩ ደክመው አይተናል   ሶምሶን በደሊላ ሀይሉን አጥቶ ደክሞ አይተናል   ቅ/ጴጥሮስ ...
12/08/2025



ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ መንፈሳዊ ጥንካሪያችን እንዳለ ሁሉ ድክመትም ይታይብናል
ብዙዎች ጠንካራ የነበሩ ደክመው አይተናል
ሶምሶን በደሊላ ሀይሉን አጥቶ ደክሞ አይተናል
ቅ/ጴጥሮስ የኢየሱስን አምላክነት የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ነህ እንዳላለ በእለተ ሐሙስ የምትይውን ሰው አላውቀውም ብሎ አይተናል
ዛሬም እኛ ካለብን ድካም ለመውጣት እነዚህን 5 መፍትሄ ተጠቀም
1ፈቃድህን ከሚያደክመው ከሀጢአት ቀለበት ራቅ
2 ከመጠን በላይ ደካማ ብትሆንም ተስፋ አትቁረጥ
ማርያም መግደላዊትን ይቅር ብሎ አበርትቶልና እኔም እበረታለሁ በል
3 የእ/ር ፋቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል
ያደረገልህን የማዳን ስራ ፍቅሩን እያሰብህ ኑር
4 ብዙዎች ደካማ የነበሩ በመጨረሻ ቅዱሳን መሆናቸውን አትርሳ
ሙሴ ፀሊም ሀሳቦቹን ለመቃዎም በአንድ ምሽት 11 ጊዜ ንስሃ አባቱ ዘንድ ተመላልሷል
በኋላም የብዙ መነኮሳት አባት ለመሆንና ለመመረጥ በቅቷል
5 እ/ር ምንጊዜም ከደካሞች ጋር ነውና ይህን እውነት ተረዳ
ሰይጣን በአንድ ወቅት እ/ርን አለው ጠንካራ ነን የሚሉትን ለእኔ ተዋቸው ያሸነፉኝ ደካማ ነን ብለው አንተን የተጠጉትን ነውና ብሏል
ድክመታችንን አውቀን በእ/ር እቅፍ እንኑር የበለጠ እንድንበረታ መንፈሳዊነታችንን አንተው

Address

Dembech'a

Telephone

+251912745936

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደጉ ሳምራዊነት/Degu Samrawi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ደጉ ሳምራዊነት/Degu Samrawi:

Share