12/06/2026
አይ የኔታ
በትምህርት ዓለም ዕድለኛ ከሆናችሁ ከታላላቅ ሰዎች እግር ስር ቁጭብላችሁ ትማራላችሁ።
እኔ ዕድለኛ ነኝ ብየ እግዚአብሔርን ከማመሰግንባቸው ምክንያቶች አንዱ ከመምህራኖቼ ያገኘሁት በረከትነው።
የኔታ ክፍሌ ብሉዩን ይተረጉማሉ በክርስቶስ ፍቅር ሁሉን ይወዳሉ። የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ በቃል ነግረውህ የሐዲስ ኪዳኑን ትርጓሜ ደግሞ በኑሯቸው ያስጠኑሃል። እኛ ስንገባ ይተረጉማሉ፤ ለቅጸላ ወደ ውጭ ስንወጣ እስከምንመለስ ዳዊት ይደግማሉ።
አይ የኔታ!
አሁን እኛም አስተማርን ብለን።
አንድ ቀን የማይቋጠር ፊት፤ ፈገግታ የማይለየው ጥርስ። አወ የኔታከት ብለው አይስቁም እንጂ ፈገግታ ተለይቷቸው አያውቅም። የኔታ በቃላቸው እንደሚናገሩት ከንቱ ውዳሴ የራቀላቸው፣ ፍቅረ ንዋይየጠፋላቸው፣ ከሁሉም በላይ የዘመኑ በሽታ መቅደሳችንን ያረከሰውዘረኝነት ፈጽሞ ያላረፈባቸው፣ እውነተኛ የእንጦንስ የመቃርስ ተከታይንጹሕ መነኩሴ የተማሩትን የሚኖሩ የሚኖሩትን የሚያስተምሩ አባቴ መሆናቸውን እኛ ደቀ መዛሙርቶቻቸው ምስክሮች ነን።
የኔታ!
ከንቱ ውዳሴ እንዳያጠቃችሁ፤ ፍቅረ ንዋይ እንዳያሸንፋችሁ አደራ ብለውን የለ ? እያለቀስሁ ነው እምጽፍልዎት እኛ ልጆቻችሁ እንደ እናንተ ብርቱዎች አይደለንም እባክዎ በሰማይም ሆነው ይጸልዩልን?
በቤተ ክርስቲያን መኖር ማለት የቤተ ክርስቲያን ደመዎዝ ተከፋይ መሆን መስሎን የምኖርባትን ቤተ ክርስቲያን ሳናውቃት በመንፈስ ልንመላለስባት ሲገባን በሥጋ ገብተን እየኖርን ነው።
አንድ ቀን ታሪክዎትን እጽፈው/እናገረው ይሆናል የኔታ ለእርስዎ የእረፍት ቀን ዛሬ ተጀመረ። እንግዲህ ይሂዱ እንጂ ከሚወዷት ገዳምዎ ከጻድቁ ሐዋርያ ጋር በመዐርግ ከሚመስሉዎ የጻድቁ ልጆች ጋር በዚያ ይኑሩ።
የኔታ ጉልበትዎን ስሜ አጠገብዎ ቆሜ መሸኘት አልታደልሁም እባክዎ አይቀየሙኝ?
ሀገሬ እንጂ ልቤ ከእርስዎ ሩቅ አይደለም። በቃ ወደ ገዳምዎ ይግቡ።
ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melak የተዋስንው