22/06/2026
ሳውዝ ዌስት ራይትስ ኤንድ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (SWRDI)፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ እና የምስጋና መርሃ-ግብር ላይ በክብር ተጋብዞ ተሳትፏል።
ድርጅታችን SWRDI፣ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ግልፅ እና ህዝባችን ሙሉ ግንዛቤ ኖሮት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲያደርግ በሲቪክና መራጮች ትምህርት እንዲሁም በምርጫ ታዛቢነት ዘርፍ በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። የኢፌድሪ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህንን ሀገራዊና ታሪካዊ ስራችንን እውቅና በመስጠት፣ አጠቃላይ የምርጫውን ውጤት ይፋ ባደረገበት በዚሁ ታላቅ እለት ድርጅታችንን በክብር በመጥራት ላበረከተው አስተዋጽኦ ያመሰገነ በመሆኑ የተሰማን ደስታ እጅግ የላቀ ነው።
በዚህ ታላቅ መርሃ-ግብር ላይ የድርጅታችን የፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ (Program Manager) አቶ Samson Demeke ድርጅታችንን ወክለው ተገኝተዋል።
መንግስት የሲቪክ ማህበራትን በአጠቃላይ በሀገራዊ እና ዘላቂ የልማት ጉዳዮች ላይ በስፋት በማሳተፍ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሀገርን እድገት፣ ፍትህንና ብልፅግናን የሚያረጋግጥበት ምህዳር ይበልጥ እንዲሰፋ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለደከማችሁ አስተባባሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ታዛቢዎች እና ለመላው የድርጅታችን አጋሮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
ሀገራዊ ግዴታችንን መወጣታችንን እንቀጥላለን!