09/06/2026
🙌ትልቅ ምስጋና🙌
ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ፣ጉልበት አቅም ሲያጣ ፣አይኖች እየፈዘዙ ሲመጡ ፣ጆሮም ለመስማት ሲርቅ ተፈጥሮ እርጅናን እያሳበቀች ትመጣለች።እርጅናውም ሲመጣ እንደ ቀድሞ ሰርጉን፣ክርስትናውን፣ሀዘኑን፣ተስካሩን ...መድረስ መካፈል መጨዋወት፣እየቀረ ይመጣና በቤት ውስጥ ብቻ ማሳለፍ ይሆናል።ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ተስፋ መቁረጥ ላይ፣ሞትን መመኘት ላይ በትንሹም ቢሆን ያዋ*ጣል።
😊ዛሬ የከበረ ምስጋናችንን እነሆን ለማለት ነው ፤ከላይ በትንሹ ለመንደርደር የሞከርነው።
🙋የኢንጂነር አቶ ገስግስ እና የወ/ሮ ረድኤት ቤተሰቦች የሁለተኛ ልጃቸውን ክርስትና በዕለተ ዕሁድ በማዕከላችን ውስጥ ከአረጋውያን በማክበር ቁርስ በማብላት አሳልፈዋል።ስላደረጋችሁት መልካም ነገር
ምስጋናችን እጅግ ከፍ ያለ ነው።ሁልግዜም በዙሪያችን አሉ ከምንላቸው መካከል እናንተ ፊተኞችስለሆናችሁ፣ድጋፋችሁ እና እርዳታችሁ በፈለግን ግዜ ሁልግዜም ቀኝ እጃችሁን ሰለምትሰጡን እናመሰግናችኃለን!ምን እንላለን? የአረጋውያን ምርቃት ይከተላችሁ!!
🤔እርስዎስ መቼ ሊመጡ አስበዋል?ከታች ባለው አድራሻ ደውለው ያግኙን
ይምጡ #ይጎብኙን #ይመረቁ #ለአረጋውያን ደስታን ይፍጠሩ
አድራሻ :ቀበሌ 5 ኮንዶሚኒየም ሳይደርስ ከውሀ ልማት አጠገብ
⭐️ክብር የተሞላበት የተሟላ ህይወት ለአረጋውያን ይገባቸዋል!⭐️
ለድጋፍ 1000256601951 ROTOM Ethiopia (CBE)
📞0999000444/0989707777