18/08/2026
አመልድ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ቀንን አከበረ (ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም)
ባሕር ዳር፣ ኢትዮጵያ – አመልድ ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ሕይወታቸውን ሰጥተው የሚያገለግሉ ሠራተኞችን ለማክበር በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥሪ ላይ ተሳታፊ ሆኗል።
ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል በደረሰ አሳዛኝ ክስተት ሦስት ባልደረቦቻችን ሲጠለፉ፣ አራት ባልደረቦቻችን ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በ" Aid Workers" ተነሳሽነት እና እንደ ፣ እና Protect Humanitarians ባሉ አጋሮች ድጋፍ ለሟች ቤተሰቦች እንዲሁም ለተረፉት የሥነ-ልቦና፣ ቁሳቁስ፣ ደመወዝ እና ሕጋዊ ድጋፍ ተደርጓል።
ድርጅታችን እነዚህ ፈተናዎች ሳይበግሩት በተስፋ እና በጽናት አገልግሎቱን ቀጥሏል። የዋና ዳይሬክተራችንን የዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴን መልዕክት እዚህ መመልከት ይችላሉ፡ https://www.youtube.com/watch?v=GYlMvOllX0Q]።
በሰብአዊ እንቅስቃሴ እና መልሶ ማቋቋም ፕሮግራማችን አማካኝነት በግጭትና በአደጋ የተጎዱ ማኅበረሰቦችን ሕይወት ለማዳንና መልሶ ለማቋቋም እየሠራን እንገኛለን። የሰብአዊ ድጋፍ ሠራተኞቻችንን ጀግንነት እያከበርን፣ አገልግሎታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ORDA Ethiopia Has Marked World Humanitarian Day 19 August 2026
Bahir Dar, Ethiopia – ORDA Ethiopia has joined the global campaign to honor aid workers who have served amidst severe crises.
Following last year’s tragic incident in the Amhara region—where three colleagues have been kidnapped and four have lost their lives—support has been delivered through the Aid Workers initiative and partners such as , , and Protect Humanitarians. This has included assistance for bereaved families alongside mental health care, material replacement, salary coverage, and legal aid for survivors.
Undeterred by these losses, ORDA Ethiopia has continued its mission with resilience. You can watch the full statement from Executive Director Dr. Alemayehu Wassie here: [https://www.youtube.com/watch?v=GYlMvOllX0Q].
Through its Humanitarian Action and Rehabilitation Program, ORDA Ethiopia has remained dedicated to saving lives, restoring dignity, and supporting conflict‑ and shock‑affected communities while protecting those who serve.