Amhara Development Association- ADA Head office

Amhara Development Association- ADA Head office Amhara Development Association was established as a nongovernmental organization in 1992 to fill the Social development gap of the Region.

በአማራ ልማት ማህበር የአልማ ብቁ ወጣት ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ  ግምት ያለው የህክምና መሳሪያና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ------------------//////--------...
21/08/2026

በአማራ ልማት ማህበር የአልማ ብቁ ወጣት ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና መሳሪያና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
------------------//////---------------

የአማራ ልማት ማህበር የደብረ ብርሃን ከተማ አልማ ልማት ጽህፈት ቤት ከአልማ ብቁ ወጣት ፕሮጀክት በተገኘዉ ፈንድ ለ04፣ለጫጫና ለደብረ ብርሃን ሆስፒታል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነበት የህክምና መሳሪያ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

በርክክቡ ወቅት አልማ በትምህርት፣ በጤናና በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ሰፊ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ማህበር መሆኑን የደብረ ብርሃን ከተማ አልማ ልማት ጽ/ት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ አውግቸው ተናግረዋል።

ማህበሩ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ እና በጫጫ ክፍለ ከተሞች በትምህርትና ጤና ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል ሰፊ ጥረት እያደገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የጤና ዘርፉን ከመደገፍ አኳያም እስካሁን ካደረገው በተጨማሪ ዛሬ ለስነ አዕምሮና ስነ ልቦና ህክምና ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች ትኩረት በመስጠት ለጫጫ፣ ለ04 ጤና ጣቢያዎች እና ለደብረ ብርሃን ኮምሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና መሳሪያ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

የአማራ ልማት ማህበር ከዩኒሴፍ (UNICEF) እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአልማ ብቁ ወጣት ፕሮግራም በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ለደብረ ብርሃን ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝ ልዩ ልዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ፣ፈርኒቸሮች ፣ኮምፒዩተር እና ፕሪንተር ድጋፍ ማድረጉን የደብረ ብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በቀለ ገብሬ ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ በዋናነት የአዕምሮና እና የስነ ልቦና ህክምና አገልግሎት መስጠት በሚያስችሉ ክፍሎች ላይ የታዩ የቁሳቁስ ክፍተቶችን ለማሟላት ያለመ እንደሆነ ጠቁመው፣የተደረገው ድጋፍ መንግሥት የነበረበትን ክፍተት የሚሞላ መሆኑን አመልክተዋል።

ማህበሩ ማህበረሰቡን በማሳትፍ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ በቀለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል ድጋፉ በስነ አዕምሮ እና ስነ ልቦና ተጠቂዎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እጥረት ያቃለለ መሆኑን የደብረ ብርሃን 04 ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ መኮንን አይተንፍሱ ተናግረዋል።የታካሚዎችን መረጃ እና ፋይሎች ከሌሎች ጋር ሳይደራረቡ ለረጅም ጊዜ በአግባቡ ለመያዝ እንደሚያስችላቸውም ገልጸዋል ።

በተመሳሳይ ጤና ጣቢያው ከፍተኛ ታካሚ ተቀብሎ የሚያስተናግድ በመሆኑ ድጋፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያሉት የጫጫ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አይረስ እንን ከዚህ በኋላ በተሟላ መሳሪያ እና ግብዓት ደረጃውን የጠበቀ እና ለታካሚዎች ምቹ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችላቸው አመልክተዋል።መረጃው የሰ/ሽዋ ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት ነው፡፡

#አልማ

#አልማ 15_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ!

ዓባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካየ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ደብተር ድጋፍ አደረገ።------/////--------የ2019 የትሞህርት ዘመን "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" የ...
19/08/2026

ዓባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካየ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ደብተር ድጋፍ አደረገ።
------/////--------
የ2019 የትሞህርት ዘመን "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ባዛር በባህር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ አደባባይ ተከፍቷል።

በአማራ ልማት ማኅበር እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የተቋቋመው ዓባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ በተዘጋጀው "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" ማሰባሰቢያ ባዛር ላይ በመገኘት 60 ሽህ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።

የዓባይ ህትመት እና ወረቀት ፖኬጂንግ ፋብሪካ ምክትል ሥራ አሥኪያጅ ነጋ ይሁኔ ታዳጊዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይኾኑ በየ ዓመቱ 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት 60 ሺህ ደብተር ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።

ድጋፉ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት እንደሚያግዝም ነው የገለጹት። ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንንት አደመ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የኾኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይኾኑ እና የሕጻናትን ችግር ለመፍታት የሁሉም የባለድርሻ አካላት ድጋፍ የሚያስፈልግ በመኾኑ መርሐ ግብሩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በክልሉ ዩኒፎርም ሳይለብሱ፣ ደብተር እና እስክርቢቶ ሳይዙ ብሎም ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አፍረው ከጓደኞቻቸው ተለይተው የሚመለሱ ልጆች በርካታ ናቸው ብለዋል።

ዩኒፎርም እና ደብተር መግዛት የማይችሉ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ፈተና ኾኖባቸዋል።

ይህ መርሐግብርም ችግር ያለባቸውን ልጆች ችግራቸውን የሚፈታ ነው ብለዋል።

ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ገበታ ለማስገባት የመጀመሪያው የሚያስፈልገው የትምህርት ቁሳቁስ ነው። ይህም አንዱ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የመጀመሪያው የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ነው።

በወቅታዊ ችግሩ ምክንያት በርካታ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ እና በኢኮኖሚ እጥረት ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ የሚቸገር ማኅበረሰብ ብዙ መኾኑን ነው የተናገሩት።

የክልሉ ማኅበረሰብ ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎች፣ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ግለሰቦች እና ሌሎችም ይህንን በጎ አድራጎት ተግባር በመደገፍ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

መርሐግብሩ ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

#አልማ #አሚኮ

#አልማ 13_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ!

አባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ 60 ሽህ ደብተር ድጋፍ አደረገ። --------/////-------የ2019 የትሞህርት ዘመን "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" የተማሪዎች የመ...
19/08/2026

አባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ 60 ሽህ ደብተር ድጋፍ አደረገ።
--------/////-------

የ2019 የትሞህርት ዘመን "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ባዛር በባህር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ አደባባይ ተከፍቷል።

በአማራ ልማት ማኅበር እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ተቋቋመው አባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ በባህር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ አደባባይ በተዘጋጀው "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" ማሰባሰቢያ ባዛር ላይ በመገኘት 60 ሽህ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፊን ያስረከቡት የአባይ ህትመት እና ወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅ ነጋ ይሁኔ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ለማስቻል ፋብሪካው በተከታታይ አመታት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ባዛሩ ከዛሬ ረቡዕ ነሐሴ13 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

#አልማ

#አልማ 13_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ!

አልማ በትምህርት ቤቶች ልማት ላይ ውጤታማ ሥራ እየሠራ ነው። ------/////------የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ልማት ጽሕፈት ቤት ከ188 ሚሊዮን ብር በላ...
18/08/2026

አልማ በትምህርት ቤቶች ልማት ላይ ውጤታማ ሥራ እየሠራ ነው።
------/////------
የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ልማት ጽሕፈት ቤት ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን የመገንባት እና የማስተማሪያ ግብዓቶችን የማሟላት ሰፊ ሥራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል።

በተከናወኑት የልማት ሥራዎች ላይ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች የተሳተፉበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የደቡብ ጎንደር ዞን አልማ ልማት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ወርቁ መረሻ እንደገለጹት በተከናወኑት ተግባራት ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

በቀጣይም የዲጂታል ትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ጨምሮ ሁለገብ ሥራዎች በትኩረት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ለተመዘገበው ውጤት ዕውቅና በመስጠት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ እየበሩ አዕምሮ የተገነቡት ጥራታቸውን የጠበቁ ክፍሎች ለትምህርት ጥራት ማደግ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን አልማ ለሚያደርገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ከማኅበሩ ጎን በመኾን ልማቶችን ለማፋጠን ዝግጁ መኾኑን አረጋግጠዋል። አሚኮ::

#አልማ #አሚኮ

#አልማ 12_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ!

ከጎዳና ሕይዎት እስከ አልማ የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊነት_   የአካል ጉዳተኛው ወጣት የሕይዎት ጉዞ -------/////------_-​አንዳንዶች በሕይወት አጋጣሚ በሚገጥማቸው ...
14/08/2026

ከጎዳና ሕይዎት እስከ አልማ የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊነት_ የአካል ጉዳተኛው ወጣት የሕይዎት ጉዞ
-------/////------_-
​አንዳንዶች በሕይወት አጋጣሚ በሚገጥማቸው ፈተና ተስፋ ቆርጠው ሲቀሩ፣ ሌሎች ደግሞ እሾሁን ወደ አበባ፣ ፈተናውን ደግሞ ወደ ስኬት መሰላል ይቀይሩታል።

በደብረ ታቦር ከተማ የተወለደው ወጣት አገኘሁ ደሳለኝ እሾሁን ወደ አበባ፣ ፈተናውን ደግሞ ወደ ስኬት መሰላል ከቀየሩት ወገን ነው።​ ሕይወት ላዘጋጀችው ውድድር ገና በልጅነቱ ነበር የተሰለፈው። በወቅቱ በነበረው የአካል ጉዳት ምክንያት እንግዳ ወደ ቤት ሲመጣ ይደብቁት የነበረበት፣ ለትምህርትም ኾነ ለሥራ አይኾንም ተብሎ የተገፋበት፣ በባሕር ዳር ጎዳናዎች ላይ እስከ መተኛት የደረሰበት መራራ እና አሰቃቂ ጊዜያትን እንዳሳለፈ ይናገራል።

​ነገር ግን ወጣት አገኘሁ ለእነዚህ ችግሮች ሁሉ አልተንበረከከም። ​"አካል ጉዳተኝነት አለመቻል አይደለም፤ ከሰው እጅ መጠበቅን ትተን ሠርተን ለሌሎች መትረፍ እንችላለን" የሚል የማይንበረከክ መንፈስን ሰንቆ ተነሳ።

ከጎዳና ሕይወት እስከ ሊስትሮነት፣ ከኮብልስቶን ሥራ እስከ ልብስ ስፌት የላቡን ጠብታ እየገበረ የጽናት መንገድን ተጓዘ።

​ዛሬ አገኘሁ በሥራው ውጤታማ ኾኖ በራሱ ጥረት የልብስ ስፌት ማሽኖችን በመግዛት የራሱን ሱቅ ከፍቶ እየሠራ ነው። ከዚህ ባሻገር ለሁለት ወጣቶች የቋሚ ሥራ ዕድል ፈጥሯል።

​ለ12 ተማሪዎችም የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) በነጻ ሰፍቶ በመስጠት ትልቅ የሰብዓዊነት አርዓያነቱን አሳይቷል።

ወጣቱ ​በቅርቡ አሚኮ ከአልማ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የብቁ ወጣት የሥራ ፈጠራ ውድድር ላይ በልብስ ስፌት ዘርፍ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ተክቶ በመሥራት የተሻለ ጥንካሬ ያለው ምርት በማቅረብ አሸናፊ መኾንም ችሏል።

ወጣት አገኘሁ አሸናፊ ኾኖ ሲወጣ በበላይነት ያሸነፈው ተወዳዳሪዎቹን ብቻ አልነበረም ከፊት ለፊቱ ተደቅነው የነበሩትን የሕይወት መሰናክሎች፣ የሰዎችን አሉታዊ አመለካከት እና የጎዳናውን አስቸጋሪ ሕይወት ጭምር ነው እንጂ።

​ዛሬ ላይ በሠራው ሥራ አሸናፊ ኾኖ በመድረክ ላይ ሲቆም የስኬቱ ምስጢር እጁ ላይ ያለው ሀብት ሳይኾን በውስጡ የነበረው የማያወላውል ዕምነት እና ጠንካራ ሥነ ልቦና መኾኑን አስመስክሯል።

​አገኘሁ ዛሬም ሕልሙ አልቆመም፤ ሥራውን የበለጠ በማስፋት ለብዙዎች ሥራ መፍጠር እና የሕይወት ታሪኩን ለሌሎች አስተማሪ በሚኾን መልኩ በፊልም ሠርቶ ማቅረብ ይፈልጋል።

​ዕውነትም ተስፋ አለመቁረጥ አሸናፊ ያደርጋል።

#አልማ #አሚኮ
#አልማ 08_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ!

አማራ ልማት ማህበር  ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ልማት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ!።--------///////-------የአማራ ልማት ማህበር...
12/08/2026

አማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ልማት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ!።
--------///////-------
የአማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ት ቤት እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትምህርት፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

‎የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ የሁለቱን ተቋማት የሰው ኃይል፣ ዕውቀት፣ ሙያዊ ልምድና የምርምር አቅም በማቀናጀት ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠቅሙ የትምህርት፣ የምርምርና የልማት ሥራዎችን በጋራ ማከናወን፣ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግሮች በዕውቀትና በምርምር ለመፍታት የጋራ ሥራን ማጠናከር ነው።

በስምምነቱ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አወል ሰይድ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ከአልማ ጋር ለረጅም ዓመታት በመተባበር ሲሠራ ቆይቷል። አሁን የተፈረመው ሰነድ ደግሞ ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሳል። በጥናትና ምርምር በመታገዝ ለህብረተሰቡ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ሥራ በማቀናጀት ለመከወን መስማማታቸውን አስረድተዋል።
‎አልማ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኝና ረጅም የሥራ ታሪክ ያለው ተቋም በመሆኑ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮው መሠረት እንደ አልማ ያሉ በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራቱ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል።

‎ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ የመግባቢያ ሰነዱን መፈራረም ብቻ በቂ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ ስምምነቱ ከፊርማ በኋላ ወደ ተጨባጭ ተግባር ወርዶ በማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ዩኒቨርሲቲው በየዘርፉ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና አጋርነት ትብብር ጽሕፈት ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አስረሴ ሞላ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው ተግባራት መማር ማስተማር፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆናቸውን ጠቁመዋል። የአልማ ድርሻ ደግሞ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስረሴ፣ ሥራዎቹን በማቀናጀት ለህብረተሰቡ በተደራጀ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ደሴ ኮምቦልቻ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አድማሴ እንደገለጹት፣ አልማ በትምህርት፣ በጤናና በሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ሲሆን ሥራዎቹን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በማያያዝ የህብረተሰቡን ችግር በዘላቂነትና በተቀናጀ መልኩ ለመቅረፍ ያለመ ነው። የመግባቢያ ሰነዱ ይህንን አላማ ለማሳካት የሚያስችል መሠረት እንደሚጥል አመልክተዋል።

እስከ አሁንም ሁለቱም ተቋማት ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ወደ ተግባር ሲተረጎም ህብረተሰቡ የበለጠ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት እንደሚቻል የተናገሩት የአልማ ደሴ ኮምቦልቻ ልማት ጽሕፈት ቤት ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሀገር ሽማግሌ አቶ ጫኔ መንገሻ ናቸው።

‎የመግባቢያ ሰነዱን ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰዒድ እና የአልማ ደሴ-ኮምቦልቻ ልማት ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አድማሴ የተፈራረሙ ሲሆን ተቋማቱ በቀጣይ የጋራ ዕቅዶችን በማውጣትና በተግባር በማዋል የትብብር ሥራውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተገልጿል።መረጃው የወሎ ዩኒቨርስቲና የደሴ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

#አልማ #ወሎዩኒቨርስቲ
#አልማ _06_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

አማራ ልማት ማህበር በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች ድጋፍ አደረገ።-----------///////---------አማራ ልማት ማህበር የጎንደርና አ...
11/08/2026

አማራ ልማት ማህበር በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች ድጋፍ አደረገ።
-----------///////---------

አማራ ልማት ማህበር የጎንደርና አካባቢው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳና ከተማ በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው ለተጠፋፉና ለተነጣጠሉ ህፃናቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የጎንደርና አካባቢው አልማ ልማት ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዘውዴ አማራ ልማት ማህበር አልማ በመደበኛው በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀው ከመደበኛ ስራዎቹ ባሻገር ከዩኒሴፍ ጋር በመቀናጀት እንደ ዞን በደባርቅ እና በዳባት ወረዳዎች በ20 ቀበሌዎች በህፃናት ጥበቃ ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም መስፈርቱን መሰረት ተደርጎ የተለዩና ድጋፍ የሚሹ 524 የሚሆኑ ህፃናትን የተለያየ ድጋፍ መደረግ መቻሉን ገልፀዋል። እየተሰራ ባለው ስራ ህፃናትን ወደ ትምህርት ገበታቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው የቆዩትን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

አልማ ከአጋር አካላትና ተቋማት ጋር በመተባበር በርካታ ተግባራቶችን እያከናወነ መሆኑን ያመላከቱት ዳይሬክተሩ የሚገኝን ሃብት በአግባቡ በመጠቀምና ለሚፈለገው አላማ በማዋል ማህበረሰቡን ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የደባርቅ ወረዳና ከተማ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበረ መንደር አጠቃላይ በወረዳና በከተማ አስተዳደሩ አልማ ዩኒሴፍ ከዚህ በፊት በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መማር ላልቻሉ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ለ262 ህፃናት መማር እንዲችሉና የተሟላ የቤተሰብ እንክብካቤ ለመፍጠር 3 ሚሊዮን 26 ሺህ 886 ብር በሆነ ወጭ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀው በዛሬው ቀንም በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከወላጆቻቸው የተጠፋፉና የተነጣጠሉ 56 ህፃናቶችን በመለየት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

በዛሬው ድጋፍ ከአልማ ዩኒሴፍ በተገኘ 865 ሺህ ብር ወጭ በወረዳ እና በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ በ10 ቀበሌዎች ለተለዩ ህፃናት ድጋፍ አድርገናል ያሉት ሃላፊው አልማ ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኑሮ ዘይቤ ማሻሻያ እንዲሁም ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የአልማ ዩኒሴፍ ሶሻል ወርከር የሆኑት ወይዘሪት ሜሮን ታረቀኝ አልማ ዩኒሴፍ በኢኮኖሚ እጥረት መማር ያልቻሉ ፣ በተለያየ ምክንያ ወላጃቸውን ያጡና የተነጣጠሉ ህፃናትን ቤት ለቤት ተከታትሎ ጥናት በማድረግና የመለየት ስራ በመሰራት እንዲሁም ቅድሚያ መሰጠት ያለባቸውን ቅድሚያ በመስጠት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህም በተለያየ ምክንያት ለተበታተኑ፣ ለተጠፋፉ ህፃናት እንደ ብርድ ልብስ፣ ፍርናሽ ከነ ትራቱ፣ ሳሙና፣ የመማሪያ ደብተር፣ እስክብሪቶ፣ እርሳስ፣ ፖርሳ እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደተደረጉ ገልፀዋል።

የደባርቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው አዛናው፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ማሩ አዲስ፣ የደባርቅ ወረዳ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ስመኝ እና ሌሎች አጋር አካላት በድጋፉ ተገኝተዋል።መረጃው የደባርቅ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

#አልማ
#አልማ _05_12_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

የማህበሩን 2019 በጀት ዓመት  እቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ይገባል ፡፡አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ------------//...
06/08/2026

የማህበሩን 2019 በጀት ዓመት እቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ይገባል ፡፡አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ
------------////////---------
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከሐምሌ 28 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በዋናው መሥሪያ ቤት በተካሄደው የምክክር መድረክ፣ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን በስፋት በመገምገም የአዲሱን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አስተዋውቋል።

በውይይቱ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና የተሸለ ተሞክሮ ያላቸው የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ያቀረቡት ስትራቴጅክና ኢኖቬሽን ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ ማህበሩ የሚጠቅመው ትልቅ እቅድ በማቀድ የሚቻለውን ሁሉ ጥረት በማድረግ የማህበረሰቡን ሰፊ የማህበራዊ ልማት ችግር መፍታት እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

በ2019 በጀት አመት ከአባላት ሃብት የማሰባሰብ እቅድ በገንዘብ፣ በአይነት፣ ሙያና ጉልበት ከ4ነጥብ 3ቢሊዩን ብር የልማት ሀብት መታቀዱን ገልጸው ይህም እቅድ እጅግ የተለጠጠ ሰፊ እርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ያሳያል ብለዋል ፡፡ ከዳያስፖራ ከ34ሚሊዩን ዶላር በላይ እንዲሁም ከአጋር አካላት በዶላር 55 ሚሊዮን ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል ፡፡

ከአባላት በተሰበሰበ ሃብት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት 483 መማሪ ክፍል፣ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት 1,247 መማሪያ ክፍል እንዲሁም 2ኛ ደረጃ 321 መማሪያ ክፍል በድምሩ 2,051 መማሪያ ክፍል ለመገንባት ታቅዷል ያሉት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው የጤና ተቋማት የግምባታ እቅድን በተመለከተ መሰረታዊ ጤና ኬላ 27 ብሎክ፣ አጠቃላይ ጤና ጣቢያ 11 ብሎክ በድምሩ 38 የጤና ተቋማት በበጀት አመቱ እንደሚገነቡ ተናግረዋል ፡፡

የቴክኒክ ኮሌጅ ወርክሾፕ ግንባታን በተመለከተ 8 ወርክሾፖችንና 2 ሸዶችን የመገንባት እቅድ የተያዘ መሆኑን ገልጸው ይህን የተለጠጠ እቅድ እውን ለማድረግ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ከወዲሁ መጀመር፣ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ በማግባባት ተሳታፊ ማድረግ፣ የማህበሩን አባላት፣ደጋፊዎች ፣ አጋር አካላትን እና ዲያስፖራውን መሰረት ያደረገ ፕሮጀክትን ለመተግበር የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡

የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና ተሞክሮ ለማቅረብ የተገኙ የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

የ2019 በጀት አመት እቅድን አስመልክቶ ማጠቃለያ የሰጡት የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን ማጠናቀቅ ፣ ባለፈው ዓመት የታዩ ክፍተቶችን ማረም የዚህ ዓመት ዋና ትኩረት ይሆናል ብለዋል ።

የመደጋገፍ ባህልን በማዳበር ከዋናው መ/ቤት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ያለው የክትትል እና የድጋፍ ሥርዓት (Teamwork) መጠናከር ፣በስራ ላይ የሚታዩ የአመለካከት ክፍተቶችን ለመቅረፍ የማያቋርጥ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ፣አዲስ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከሞላ ጎደል ጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ቢሆኑም ተጨማሪ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚገባ ገልጸዋል ። ወጪ ቆጣቢ፣ ውጤታማ እና ተቋማዊ ግቦችን ማሳካት የሚችል የአሠራር ማዕቀፍ መዘርጋት እንደሚገባም አመላክተዋል ፡፡

የለውጥ መሪ (Transformational Leadership) መሆን፣ ለውጥን በብቃት መምራት እና የተቋሙን ተቋማዊ አቅም ማሳደግ ፣የሰዎችን አመለካከት፣ አሰራር እና ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ መሄድ የአመራሩ ዋና ትኩረት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል ።

ማህበሩ በ2019 በጀት ዓመት የዲጂታል ሽግግርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን መተግበር፣ የአፈጻጸም ጥራትን ማረጋገጥ፣ የተቋሙን ብራንድ መገንባት እና አዳዲስ የገቢ ማመንጫ አማራጮችን በመጠቀም የፋይናንስ አቅምን በዘላቂነት ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል ።

በመድረኩ ማጠቃለያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የዞን አልማ ልማት ልማት ጽህፈት ቤቶች በተቋም ደረጃ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤቶች ፣ከ1ኛ-3ኛ ለወጡ ለወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤቶች ማበረታቻ ሽልማት እና የምስክር ወረቀቶች ተበርክቷዋል።

በተጨማሪም የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤቶች ውስጥ በሴት ሥራ አስኪያጆች 1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ፣አዲስ አባል በማፍራት ግንባር ቀደም ለሆኑ ሰራተኞች ከ1ኛ-5ኛ ለወጡ የማበረታቻ እና የምስክር ወረቀቶች ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

#አልማ
.ም
#አልማ _29_11_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

የፕሮጀክቶችን ወጪ ቆጣቢነት ማረጋገጥ እና የተቋሙን አላማ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ --...
06/08/2026

የፕሮጀክቶችን ወጪ ቆጣቢነት ማረጋገጥ እና የተቋሙን አላማ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ
------------////////---------
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከሐምሌ 28 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በዋናው መሥሪያ ቤት በተካሄደው የምክክር መድረክ፣ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን በስፋት በመገምገም የአዲሱን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አስተዋውቋል።

በውይይቱ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና የተሸለ ተሞክሮ ያላቸው የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ስትራቴጅክና ኢኖቬሽን ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ ማህበሩ የየአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በመዳሰስ ለስራ ምቹ የሆኑ አጋጣሚዎችን በመጠቀም አባላትን ማፍራትና በማስቀጠል በጥሬ ገንዘብ፣ አይነትና ሙያ ከ1ነጥብ 3ቢሊዩን ብር በላይ የልማት ሃብት በመሰብሰብ ፕሮጀክቶችን የመተግበር ስራ ተሰርቷል ብለዋል ፡፡

ከአጋር አካላት ከ29ሚሊዩን ዶላር በላይ የልማት ሃብት ማግኘት በመቻሉ ፕሮጀክቶች በውል ስምምነቱ መሰረት ወደ ትግበራ ምዕራፍ ተገብቷል፡፡ ከገቢ ማስገኛ ተቋማት ያልተጣራ ትርፍ ከ63 ,ሚሊዩን ብር በላይ ሃብት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ከዲያስፖራ ቤተሰብ በአይነት ብር 17ሚሊዩን በላይ የልማት ሀብት መገኘቱን በሪፖርታቸው አብራርተዋል ፡፡

አቶ አበረ አክለውም በተገኘው የልማት ሀብት 196 የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትም/መማሪያ ክፍሎች፣ 837 የ1ኛ ደረጃ ትም/ መማሪያ ክፍሎች እንዲሁም 103 የ2ኛ ደ/ትም መማሪያ ክፍሎች ግንባታ በድምሩ 1,136 መማሪያ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው በሪፖርቱ አመላክተዋል ፡፡

ከ2017 በጀት አመት የዞሩ 17 ጤና ኬላና 22 ጤና ጣቢያ ብሎኮች በድምሩ 39 የጤና ተቋማት ብሎኮች ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት ተችሏል፡፡ቴክኒክ ኮሌጅ ወርክሾፕ 8 ተጠናቋል፤ 15 የማምረቻና መሸጫ ሼዶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተመላክቷል ፡፡

በመድረኩም በአባላት ልማት ስራ ፣በፕሮጀክት አፈጻጸም ፣ከአጋር አካላት የተገኘ ልማት ሀብት ፣በዳታቤዝ እንዲሁም ከአባላት ሀብት አሰባሰብ አንጻር የተመዘገበው ውጤት የሚያበረታታ ቢሆንም የላቀ ፕሮጀክት ለመፈጸም የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከዚህ በላቀ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል ፡፡

ከገቢ ማስገኛ አንጻር የደብረ ማርቆስ G+10 ህንጻ ኮምፕሌክስ ግንባታ ገቢ ወደ ሚያስገኝበት ደረጃ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በአንጻሩ የዋንዛየ ሎጅ ግንባታ በሚጠበቀው ልክ ባለመሄዱ በቀጣዩ በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገምግሟል።

በተጨማሪም በቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ በእለት ደራሽ ድጋፍ እንዲሁም በ"አልማ ብቁ ወጣት" ፕሮግራም በሥራ ዕድል ፈጠራ የተከናወኑ ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

በመድረኩ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች አልማ ልማት ጽ/ቤቶች መልካም ተሞክሯቸውን ያጋሩበት ሲሆን የ2019 በጀት አመት እቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የሚያነሳሳ መሆኑ ተመላክቷል ፡፡

በ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም መድረክን የመሩት የአማራ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ እንደገለጹት፤ ኢን-ካንድ (In-kind) እና ኢን-ካሽ (In-cash) አስተዋጽኦ ከእያንዳንዱ ፕሮጀክት ጋር የሚደረጉ አስተዋጽኦዎችን ለይቶ መመዝገብ፣ ትክክለኛ የገበያ ዋጋቸውን ማሳየት እና የኢን-ካንድ ግምቶችን በጥንቃቄ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች የፕሮጀክት ሲሰሩ የአተገባበርና እና ዳታ አያያዝ ሂደት እንደ ማህበር በጥሩ ሁኔታ እየተተገበረ ቢሆንም የሪፖርት አቀራረብ እና የዳታ ትስስር ክፍተቶች እንዳይኖሩ በጥንቃቄ መስራት ይገባል ብለዋል ።

የተቋሙ አላማዎች የፕሮጀክቶችን ወጪ ቆጣቢነት ማረጋገጥ እና የተቋሙን አላማ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው የግብአት አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች ያለው የግብአት አቅርቦት ሂደት በፋብሪካ ደረጃ ቀጥተኛ ድጋፍ እንዲኖረው እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል ።

#አልማ
.ም
#አልማ _29_11_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

አማራ ልማት ማህበር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ  እና  የ2019 በጀት ዓመት  የእቅድ ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ ------------////////---------የአማራ ልማት...
06/08/2026

አማራ ልማት ማህበር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ
------------////////---------
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከሐምሌ 28 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በዋናው መሥሪያ ቤት በተካሄደው የምክክር መድረክ፣ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን በስፋት በመገምገም የአዲሱን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አስተዋውቋል።

በውይይቱ ላይ የዋና መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ 11 የዞን አልማ ልማት ጽህፈት ቤቶች የተወጣጡ የማኔጅመንት አባላት እና የተሸለ ተሞክሮ ያላቸው የወረዳ አልማ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

አማራ ልማት ማህበር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ ፕሮግራም አስመልክቶ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፍት የስትራቴጅክና ኢኖቬሽም ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበረ መኩሪያ አማራ ልማት ማህበር ከ2017-2021 ዓ.ም የሚቆይ የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ ቀርጾ ወደትግበራ ከገባ ሁለት አመት ማስቆጠሩን ገልጸዋል ፡፡
የመድረኩ ዋና አላማ ባለፈው ዓመት የተከናወኑ የሥራ አፈፃፀሞችን በአግባቡ ለመገምገም፣ የተገኙ ስኬቶችን ለማጠናከር፣ ክፍተቶችን በግልጽ ለመለየት እና ትምህርት በመውሰድ የ2019 በጀት ዓመት እቅድን ለማሳካት በጋራ ለመግባባት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል ።

ይህ ግምገማ ሪፖርት ማቀረቢያ ብቻ ሳይሆን፣ አስቸጋሪ በሆኑ ወቅቶች ውስጥ ሆኖ የተከናወነውን የማህበሩን አፈፃፀም የምንመዝንበት፣ የጋራ ራዕያችንን የምናጠናክርበት እና ለወጤት የሚያበቁ አሰራሮችን የምናሳድግበት ጠቃሚ መድረክ መሆኑንም አቶ አበረ ተናግረዋል ።

አማራ ልማት ማህበር ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰብ ተኮር የልማት እና የሰባዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ላይ ይገኛል ያሉት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚው ተግዳሮቶችን በማሸነፍ በተሻለ ውጤት ለማስቀጠል ከሁሉም በላይ ያደገ እቅድ በማዘጋጀት ለህዝብ ተጠቃሚነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

#አልማ
.ም
#አልማ _29_11_2018_ዓ.ም
በራስ አቅም የመልማት ምልክት- አልማ
የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ ፡ https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052
ቴሌግራም ፡-https://t.me/AmharaDevtAssociation
ዮቱዮብ፡-https://www.youtube.com/
ዋትስ አፕ:https://chat.whatsapp.com/H9JxxgVUcdo5NRENaUCSYK
ቲክቶክ:tiktok.com/.devt.assoc
ዌብሳይት: www.ada.org.et
ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!

Address

K 05
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Development Association- ADA Head office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Development Association- ADA Head office:

Shortcuts

Share