Nigat Corporate

Nigat Corporate NIGAT Corporate was established in 1995 as an Endowment Organization registered in ANRS, Ethiopia.

06/04/2026
ማዕድ ምግብ ኮምፕሌክስ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረማዕድ ምግብ ኮምፕሌክስ በደብረማርቆስ ከተማ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን የተቋቋመውም በንጋትና በ3 ኩታ ገጠም ዞኖች በሚገኙ ...
16/03/2026

ማዕድ ምግብ ኮምፕሌክስ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ
ማዕድ ምግብ ኮምፕሌክስ በደብረማርቆስ ከተማ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን የተቋቋመውም በንጋትና በ3 ኩታ ገጠም ዞኖች በሚገኙ አርሶ አደሮች ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት የፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ብስኩት እና የዱቄት ፋብሪካ የያዘ ትልቅ ፋብሪካ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የብስኩት ማምረቻ ፋብሪካው የማሽነሪ ተከላውን በማጠናቀቅ የሚከራ ምርት ማምረት ችሏል፡፡ በዚህም እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ፋብሪካው በቀጣይ የፓስታና መኮረኒ እንዲሁም የዱቄት ፋብሪካው ተከላው ተጠናቆ ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ እምነታችን የፀና ነው፡፡

የኮምቦልቻ  ጨርቃጨርቅ አክስዮን ማህበር  ቦርድ ስብሰባ አካሄደየኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ቦርድ በስብሰባው ወቅት የኩባንያውን የ2025 እ.አ.አ. ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽ...
26/02/2026

የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክስዮን ማህበር ቦርድ ስብሰባ አካሄደ
የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ቦርድ በስብሰባው ወቅት የኩባንያውን የ2025 እ.አ.አ. ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን የየ2026 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በመወያየትና በማፅደቅ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስተዳደር ማንዋል እና የመሳሰሉት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ የቦርዱ ሰብሳቢ እና የንጋት ኮርፖሬት ማኑፋክቸሪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ዳዊት ዋለ ገልፀዋል፡፡

አዚላ ኤሌክትሮኒክስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ2025 እ.ኤ.አ.ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ገመገመበደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው እና የሳምሰንግ ፍሪጅ በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ ገበያ ለ...
27/01/2026

አዚላ ኤሌክትሮኒክስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ2025 እ.ኤ.አ.ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ገመገመ
በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው እና የሳምሰንግ ፍሪጅ በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ ገበያ ለሽያጭ በማቅረብ የሚታወቀው የንጋት ኮርፖሬት ኩባንያ የሆነው አዚላ ኤሌክትሮኒክስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እ.ኤ.አ.የ2025 ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም በመገምገም የ2026 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ማድረጉን የኩባንያው ሥራአስኪያጅ አቶ እየበሩ ፈንታሁን ገልፀዋል፡፡
እንደ ሥራአስኪያጁ ገለፃ የኩባንያው ከ2024 በጀት ዓመት አፈፃፀም አንፃር የተጣራ የሽያጭ ገቢ አፈፃፀሙ በ156% እና የተጣራ ትርፍ በ197% ብልጫ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ለዚህ አፈፃፀም ስኬት ኩባንያው ከሳምሰንግ ፍሪጅ መገጣጠም በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ የፍሪጅ የምርት ግብዓቶችን ከውጭ በማስመጣት መገጣጠምና መሸጥ በመቻሉ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህንን የስራ አፈፃፀም ለማስቀጠል ከሳምሰንግ ፍሪጅ መገጣጠም ስራ በተጨማሪ ሌሎች የጀመራቸውን የአዳዲስ የፍሪጅ ምርት ግብዓቶችኝን በዓይነትና በመጠን በማስፋትና ከውጭ በማስመጣት እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ የምርት ዓይነቶችን መገጣጠም መጀመርና በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ፍሪጅን ከመገጣጠም ባለፈ በአገር ውስጥ ማምረትና ለተጠቃሚው ማህበረሰሰብ ለማድረስ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን የማምረቻ ማሽኖችን የመትከል ስራ ማጠናቀቅና የማምረት ስራ መጀመር የኩባንያው አመራርና ሰራተኞች ቁልፍ ስራ መሆኑን መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

By Wudneh Gezahegne፡

By Wudneh Gezahegnግሪን ፓኬጅንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተሸለ አፈፃፀም ላይ እንዳለ ተገለፀግሪን ፓኬጅንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2025 እኤአ መከናወን የሚገ...
26/01/2026

By Wudneh Gezahegn
ግሪን ፓኬጅንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተሸለ አፈፃፀም ላይ እንዳለ ተገለፀ
ግሪን ፓኬጅንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2025 እኤአ መከናወን የሚገባቸው የዝግጅት ተግባራት በወቅቱ ማከናወን መቻሉን የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክንዴ ዓለማየሁ ገለፁ፡፡ ከዝግጅት ምዕራፍ በኃላ በተግባር ምዕራፍ የፕሮጀከቱ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆኑ የፋብሪካው የፊዚካል ግንባታ አፈፃፀም 99.65% እንዲሁም የስቲል ስትራክቸሩ አፈፃፀም 100% ላይ ደርሷል፡፡
ለፋብሪካው የመብራት መሰረተ ልማት መሟላትን በተመለከተ ባለ1600KVA እና ባለ 3500KVA ትራንስፎርመሮችን በቦታቸው የማስቀመጥ ስራ ተፈፅሟል፤ ለፋብሪካው አገልግሎት የሚውሉ የግብዓት /የክራፍት ወረቀት/፤ ኬሚካል እና ቀለሞች ግዥ ተፈፅሟል፡፡
በአጠቃላይ ከፊዚካል ተግባራት አፈጻፀም አኳያ ማሽነሪ ለመትከል የሚያስችል ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቀዋል ያሉት ሥራ አስኪያጁ የማሽነሪ ተከላ ስራውን ለማከናወን አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅቶች ቢጠናቀቅም ከክልሉ የሰላም ሁኔታ ጋር በተያያዘ ማሽነሪ የሚተክለው ድርጅት ወደ ባህር ዳር ባለመምጣቱ የተከላ ስራውን ማከናዎን ያልተቻለ ሲሆን ጉዳዮን በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት ተደርጎ ስራውን ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ጥረትና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የኩባንያው 2024እ.ኤ.አ. የፋይናንስ እንቅስቃሴ በተመለከተ በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ተደርጓ ውጤቱም Unqualified በመሆኑ በኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እንዲመዘገብ ተደርጓል፤
ከዚህ በተጨማሪ የኩባንያው የተሻሻለ ድርጅታዊ መዋቅር ተዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለንጋት ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም በአጠቃላይ ከላይ በተገለፀው መሠረት ኩባንያውን የገጠመው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር መፍታት ከተቻላ በአጭር ጊዜ ወደ ምርት እንደሚሸጋገር ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ንጋት ኮርፖሬት በጥጥ ምርት የኮንትራት ፋርሚነግ ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት (MOU) ተፈራረመጥጥ በዋነኛነት ለጨርቃ ጨርቅ፣ ለምግብ እና ለመዋቢያዎች ኢንዱስትሪዎች የሚመረት የኢንዱስትሪ ሰብ...
05/12/2025

ንጋት ኮርፖሬት በጥጥ ምርት የኮንትራት ፋርሚነግ ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት (MOU) ተፈራረመ
ጥጥ በዋነኛነት ለጨርቃ ጨርቅ፣ ለምግብ እና ለመዋቢያዎች ኢንዱስትሪዎች የሚመረት የኢንዱስትሪ ሰብል ነው። በሞቃታማ እና ሞቃታማ አካባቢዎች ውስጥ የግብርና ስርዓቶች ቁልፍ አካል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ጥጥ፣ ከጥጥ ምርትና ማቀነባበሪያ ጋር በተያያዙ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች እያደገ ላለው ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የስራ እድል በመፍጠር በብሔራዊ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ጥጥ ከኢትዮጵያ ዋና የገንዘብ ሰብሎች አንዱ ሲሆን በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ እና በዝናብ በሚመገብ የግብርና ሥርዓት ውስጥ በሰፊው ይመረታል። ሀገሪቱ ከ3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ለጥጥ እርሻ ተስማሚ የሆነ መሬት አላት።
በአማራ ክልል እና በአገር አቀፍ ደረጃ በጥጥ ምርት ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ NIGAT ኮርፖሬት በኢትዮጵያ መንግስት አዋጅ ቁጥር 1289/2023 የግብርና ምርት ኮንትራት እርሻን ለማካሄድ በወጣው አዋጅ መሠረት የኮንትራት ጥጥ ማምረትን ጀምሯል። እ.ኤ.አ. በ 2025 NIGAT ኮርፖሬት በገንዳውሃ ጂኒንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በኩል ሁለት ፕሮጀክቶችን ጀምሯል፡፡ በ 380 ሄክታር ላይ የተሻሻለ የጥጥ ዘር ማባዛት እና በ 670 ሄክታር ላይ የሀገር ውስጥ ዘሮችን በመጠቀም የኮንትራት ጥጥ ማምረት ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ምዕራባዊ ጎንደር ዞን በመተማ አካባቢ በድምሩ 1,050 ሄክታር ይሸፍናል።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት (MOU) ከታህሳስ 3 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ከዚህ በታች በአማራ ፕሬዝዳንታዊ ርክክብ ክፍል ("የመጀመሪያው ወገን")፣ NIGAT ኮርፖሬት ("ሁለተኛ ወገን") እና በግብርና ቢሮ (BOA) ("ሦስተኛ ወገን") መካከል በተዘረዘሩት ውሎች እና ሁኔታዎች መሠረት ወደዚህ ስምምነት ለመግባት ተስማምተዋል ።
የዚህ መግባቢያ ስምምነት ዓላማ ተዋዋይ ወገኖች የኮንትራት እርሻ ስርዓትን በመተግበር በግብርና አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን የጥጥ ምርት ክልላዊ አቅም ከፍ ለማድረግ በጋራ ተስማምተዋል። ይህ ስርዓት በሦስቱ ወገኖች (APDU፣ NIGAT እና BOA) በጋራ የሚመቻች ሲሆን ለምርቱ የገበያ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ፣ ለአነስተኛ ገበሬዎች ግብአት፣ ቴክኖሎጂ እና ብድር እንዲያገኙ፣ አደጋዎችን (ምርትም ሆነ ዋጋን) ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ስምምነቱን የተፈራረሙት በንጋት ኮርፖሬት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ቺፍ ኦፊሰር አቶ ዳዊት ዋለ ገልፀዋል።

Address

ADDIS ABABA
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigat Corporate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Nigat Corporate:

Share

TIRET OFFICIAL

TIRET was established in 1995 as an Endowment Organization registered in Amhara National Regional State. The initial capital of Birr 26,173,813.00 which was equivalent to US$969,400.48 dollar was contributed by the founders.

As an endowment organization TIRET has been engaged in profitable businesses whose profits and assets are to be used for the rehabilitation and Social-Economical development of Amhara National Regional State and its people.

Our present total assets valuation inclusive of shares and stocks in other companies estimated above 9.8 billion birr /USD $460 million, TIRET is set to become the biggest social Endowment business in the whole of East Africa.