Amhara Nursing Association

Amhara Nursing Association We are a community of nurses dedicated to quality care, professional growth, and improving health for all.

17/04/2026
20/02/2026

Blessed Day!

 #እድሜን የሚጨምር መድኃኒት=====የአሜሪካ ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ ቢያንስ እስከ 150 ዓመት በምድር ላይ መኖር የሚያስችል መድኀኒት በምርምር  መገኜቱ ተገለጸ። #መረጃው AFP News
02/02/2026

#እድሜን የሚጨምር መድኃኒት
=====
የአሜሪካ ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ ቢያንስ እስከ 150 ዓመት በምድር ላይ መኖር የሚያስችል መድኀኒት በምርምር መገኜቱ ተገለጸ።

#መረጃው AFP News

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማርበርግ ቫይረስን በመቆጣጠርና በመከላከል እረገድ ላበረከተው አስተዋጽዎ እውቅና ተሰጠው ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን አስመል...
29/01/2026

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማርበርግ ቫይረስን በመቆጣጠርና በመከላከል እረገድ ላበረከተው አስተዋጽዎ እውቅና ተሰጠው

ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን አስመልክቶ በተዘጋጀ የእውቅና መርሀግብር ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለነበረው የማይተካ ሚና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አመስግነዋል::

ኢንስቲትዩቱ ቫይረሱ በሀገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ የቫይረሱን አይነት መገምገም፣ እንዴት እንደሚተላለፍ መረጃ ማግኘት፣ የቫይረሱን ፣ ባህሪ እና የጂኔቲክ ልዩነት ማረጋገጥ ወይንም ሞሎኪውላር ልየታ እና ምርመራዎችን ከማከናወን ጀምሮ የበሽታ ቅኝቶችን በማከናወን እና ፈጣን ምላሽ በመስጠት ከፍተኛ ድርሻ እንደተወጣ የገለጹት ሚኒስትሯ በዘርፉ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ፣ የህብረተሰብ ጤና አደጋ በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም የህብረተሰብ ግንዛቤ በመፍጠርና በማሳተፍ ስራዎች (Risk Communication & Community Engagement) ፣ አቅምን በመገንባት ፣ ግብአትበማቅረብ፣ የሰው ኃይል በመመደብ፣ የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ላደረገው አስተዋጾ እውቅና መሰጠቱን ተናግረዋል::

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመቶ ዓመታት በጤናው ዘርፍ ሕብረተሰቡን ሲያገለግል የቆየ እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ማርበርግን የመሰሉ በሽታዎችን ከፊት በመቅደም ከክልል ጤና ቢሮዎችና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር በቅንጅት በመስራት ትልቁን ሚና የተጫወተ ተምሳሌት ነው ብለዋል::

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉን ጨምሮ ከፍተኛ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ዳይሬክተሮች የህዝብ ተወካይች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ በተገኙበት የተቀበሉ ሲሆን ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እውቅናውን ተከትሎ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ እንደ ማርበርግ እና ኮቪድ የመሳሰሉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካራ ስርዓት መዘርጋቱንና የተለያዩ ቫይረሶችንም ለመለየት የሚያስችል የላብራቶሪ አቅም መገንባቱን ገልጸው ከከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ መላው ሰራተኞችን፣ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶችን በማሳተፍና ከአጋሮች ጋር በቅንጅት በመስራት የማርበርግ ቫይረስ በህብረተሰባችን ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲቀለበስ በከፍተኛ ኃላፊነት መወጣቱን አስረድተዋል::
@መረጃው የኢት.ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱይት ነው!

ኢትዮጵያ የ 2030 የጤና ግቦችን አፈጻጸም የሚገመግም ከፍተኛ የዉይይት መድረክ አዘጋጀች December 24, 2025 የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የ.....

12/11/2025

ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

08/11/2025

African Union Commission Welcomes and Congratulates the Republic of South Africa as G20 Chair and Host.

1. The African Union Commission (AUC) warmly expresses its support for the Republic of as G20 Chair and welcomes the country for hosting the G20 Summit in Africa for the first time. This milestone reflects South Africa’s growing role in global governance.

2. As the current Chair of the G20, South Africa has shown exceptional leadership in promoting the priorities of the Global South, advancing sustainable development, and strengthening inclusive global governance.

3. The Republic of South Africa is a vibrant democracy that upholds equality, human rights, and the rule of law. Its Constitution and policies reflect values aligned with the African Charter on Human and Peoples’ Rights.

4. South Africa is a nation rich in diversity, home to people of many races, cultures, languages, and faiths living together in unity. This inclusivity is a source of national strength and global admiration.

5. The African Union encourages all international partners to engage with South Africa and the wider African continent on the basis of mutual respect, truth, and constructive cooperation, supporting Africa’s continued contribution to global peace, development, and prosperity.

Read @ https://au.int/en/pressreleases/20251108/auc-welcomes-congratulates-republic-south-africa-g20-chair-and-host

https://www.facebook.com/100052404860987/posts/1024876955935790/
11/08/2024

https://www.facebook.com/100052404860987/posts/1024876955935790/

አዲስ ምዕራፍ...

የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር ተገብቷል። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው።

1- ካርዲዬሎጂስት
2- የማርኬቲንግ ባለሙያ
4- ኬሚካል ኢንጅነር
5- ባስ ድራይቨር
6- አርክቴክት
7- አካውንታን
8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ
9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን
10- የአይ ቲ ባለሙያ
11- የፋርማሲ ባለሙያ
12- የሽያጭ ባለሙያ
13- የሶፍትዌር ባለሙያ
14- ሜዲካል ዶክተር
15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ
16- ነርስ
17- ግራፊክስ ዲዛይነር
18- የፀጉር ባለሙያ
19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ

በመሆኑም አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et) በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆን ጥሪ እናቀርባለን።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

24/07/2024

"ባለፈው ወድቄ፣ ስርሽ ዞሯል አሉኝ"... ስር ወዴት ይሆን የሚዞረው?እርግጥ ነው አንዳንዴ በቋንቋ ግድፈትም ይሁን ምትክ የአማርኛ ቃል በማጣት፤ ለህመሞች የምንሰጠው ስያሜ ህመሙን የማይወክል...
27/04/2024

"ባለፈው ወድቄ፣ ስርሽ ዞሯል አሉኝ"... ስር ወዴት ይሆን የሚዞረው?

እርግጥ ነው አንዳንዴ በቋንቋ ግድፈትም ይሁን ምትክ የአማርኛ ቃል በማጣት፤ ለህመሞች የምንሰጠው ስያሜ ህመሙን የማይወክል ለባለሙያም ግር የሚያሰኝ ነው።

ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ከምሰማቸውና ፈገግም ከሚያደርጉኝ አንዱ፡ "ባለፈው ወድቄ፣ ስርሽ ዞሯል አሉኝ" የሚለው ነው። ኧረ "ጅማትህ ዞሯል" የተባለም አለ። ወዴት ነው ሚዞረው?

እንደው "ስር" ሳሳ ብሎ ስለሚታይ እና ከሰው ሰው ልዩነት ሊኖር ስለሚችል እንደው ያሳስት ይሆናል፤ ግን እንደው "ከፊት የነበረው ጅማትህ ወደ ኃላ ዞሯል" ስትባል እንዴት አትልም? ስለኸዋል? የቤትህ ጣራ ተገልብጦ ከኮርኒሱ ስር ሆኗል ብትባል ታምናለህ? እንደው የሆነ ነገር ቢወድቅበት እንኳን ሙሉ ለሙሉ ይወድማል እንጂ።

ምንም ነገር መሄድ ከሚችለው በላይ ርቀት እንዲሄድ ሲገደድ እንደሚጎዳው፤ ጡንቻም ሌሎች አያያዥ የሰውነት ክፍሎችም [Ligaments and Tendons] መለጠጥ ወይንም መሰንጠቅ [complete or partial tear] ሊደርስባቸው ይችላል። እና ደሞ በፈጣሪ፣ በጭራሽ አይታሽም! ወጌሻ ጋር አትሩጥ። በተቻለ እንቅስቃሴውን ገድበህ ወደ ሀኪም ቤት ሂድ፤ ቀላል ነው።

እረ ስንት አይነት የተሳስተ ግንዛቤ ሚፈጥሩ አባባሎች አሉ ይሄማ እንደው ደና ነው ይቀራረባል።

የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ ላይ ቀርቦ፤ ከህፃናት አእምሮ ክፍል ጉዳት ጋር ተያይዞ የሚመጣን የሚጥል በሽታ [seizure] በማሸት እንደሚፈውስ ሲያወራ ሰማሁ፤ በውነት ታመምኩ😮😬 ጋዜጠኛውም እንዴት ብሎም አይጠይቅም፤ [ወላጅስ ጭንቅ ላይ ነው] ሚስኪኑን ጨቅላ ይፈትገዋል!😞 አይ ምስራቅ አፍሪካ😞

ሶሻል ሚዲያ ላይማ ተረከዝን እያዩ የዲስክ ህመምን መተንበይም ተጀምሯል፤ እግዚዮ

ኧረ ወገን እንጠይቅ! "ምክንያቱ ምንድነው?" እንበል! ህክምናው እንዴት እንደሚያሽል አብራሩልን እንበል።
እኛም ፈጣሪን እንፍራ፤ ያልተረጋገጠ መላ ምት!? ለራሳችን እንኳን ያልገባንን ህክምና!? አማኝ ህዝቦች አልነበርን እንዴ ቆይ?🤔🤔

ለመረጃው(ሀኪም ፔጅን ተጠቅመናል)

References
https://www.physio-pedia.com/Ankle_Sprain
https://www.ncbi.nlm.nih.gov/books/NBK459212/

Abel Fekadu: Physical Therapist
Telegram: t.me/HakimEthio

Original Editor - Dale Boren, Michael Kauffmann, Pieter Jacobs as part of the Vrije Universiteit Brussel Evidence-Based Practice Project

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Nursing Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Nursing Association:

Share