Christian Abrham

Christian Abrham Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christian Abrham, Bahir Dar.

▹ከዚህ እርካሽ ዓለም ቅዱስ ካልሆነ ግንኙነት እምነት ከሌለብት ንግግር እግዚአብሄር ከማይክበርብት እሩጫ ፍቅር ከሌለበት ስጦታ ተመስጦ ከሌለው ዝማሬ ምፅዋት ከሌለበት ሃብት እንድንርቅ እግዚአብሄር ይርዳን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች!! 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀-🟩🟨🟥 እዳ ከፋይ የሔዋን እዳ ከፋይ=
_
በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ ዳግመኛም ስለድንግል ማርያም ተከፈተልን፣ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን።
_
▹ሔዋን እጸ በለስ ከበላች በኋላ ርግማንን ለመሸከም ተገደደች ከገነት እንድትወጣም ተፈረደባት፣በዚህም ምክንያት የምድረ ፋይዳ እዳ ባለቤት ሆነች፣
▹የውርስ ሐጥያት ያልነካት እመቤታችን ቅድስ ድንግል

ማርያም የሔዋንን እዳ አስወገደች፣የሔዋንን እዳ ትከፍል ዘንድ እናቱን መረጠ፣አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው እውነተኛ የሕይዎት መብልና መጠጥ ናት ስለወለድሽልን ድንግል ማርያም ሆይ እንወድሻለን፣ብሎ እንደተናገረው ይህ ምግብና መጠጥ፣የሔዋንን እዳ ከንቱ አደረገው።
▹እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በመሕጸን እያለች ነበር የሔዋንን እዳ መክፈል የጀመረችው።
▹ሐና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጸንሳ እያለች ነበር ወደሊባኖስ የተሠደደችው።
▹እመቤታችን በቤተ መቅደስም ጠላትቿ ነበሩ ልጇ እስከሚያሳርጋት ድረስ በመከራ ውስጥ ሆና የሔዋንን እዳ ትከፍል ነበር።
▹ኢየሱስን ክርስቶስን ጸንሳ እስክትወልድ ድረስ ወልዳም መከራ አልተለያትም።
▹ጨካኙ ከሐዲው ዳቢሎስ አዳምና ሔዋንን ወደገነት ይመልስብኛል ብሎ ሔሮድስን አስነስቶ በስደት መከራን እንድትቀበል አደረጋት፣አይሁድን አስነስቶ ክርስቶስ ልጇን አሠቀለ ምን ያልወጠነው ነገር ነበር ዳቢሎስ? ነገር ግን መለኮትን ይቃወመው ዘንድ አልቻለምና ተሸነፈ።
▹የአዳም ዘር በሙሉ ተነስቶ ከሲኦል ወደገነት ገባ የሔዋን እዳም በዚህ የመከራ ጉዞ ውስጥ ተከፈለ።
በድንግል ርሐብና ጥም እንባና ሐዘን ሔዋንን ከእዳ ተገላገለች እናታችን ሔዋን ከእባብ ጋር የተረገመችው እርግማን ጸጋ ወይም ስጦታ ሆኖ ተሠጣት፣የተዘጋው በር ተከፈተልን።
▹ከፋይ እዳ ፍዳን
ድንግል እናታችን
ለአዳምና ለሔዋን።

ድንግል ማርያም ህይወታችንንቤታችንን ትባርክልን።
27/04/2026

ድንግል ማርያም ህይወታችንን
ቤታችንን ትባርክልን።

 #ሼር ሚፈልግ ፖስት።የእርዳታ ጥሪ እህታችን ትግስት አጉማስ በደረሰባት የጡት ካንሰር በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ስትረዳ ብትቆይም ከህመሟ ልታገግም ባለመቻሏ ወደ አዲስ አበባ ጥቁር ...
27/04/2026

#ሼር ሚፈልግ ፖስት።

የእርዳታ ጥሪ እህታችን ትግስት አጉማስ በደረሰባት የጡት ካንሰር በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ስትረዳ ብትቆይም ከህመሟ ልታገግም ባለመቻሏ ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ሪፈር ስለተባለች የህክምናዋን ወጭ መሸፈን ስላልቻለች የእናንተ የደጋግ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ትሻለች ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው እና እባካችሁን የቻላችሁትን እህታችንን እንድረስላት።🙏

ንግድ ባንክ 𝟏𝟎𝟎𝟎𝟑𝟒𝟕𝟗𝟐𝟎𝟏𝟑𝟖
አባይ ባንክ 𝟒𝟕𝟐𝟗𝟏𝟏𝟗𝟏𝟏𝟑𝟗𝟗𝟔𝟎
እባካችሁን እርዷት።

"በጣናዋ ገነት በባህር ዳር ከተማ የወራሚት ቅዱስ ገብርኤል በአማረ ቦታ ላይ ድንቅ የሆነዉ ታላቁ ቤተክርስትያን ይህ ታላቅ የእግዚአብሔር አምላክ ቤተመቅደስ ከጣና ሐይቅ በቅርብ እርቀት የሚገ...
27/04/2026

"በጣናዋ ገነት በባህር ዳር ከተማ የወራሚት ቅዱስ ገብርኤል በአማረ ቦታ ላይ ድንቅ የሆነዉ ታላቁ ቤተክርስትያን ይህ ታላቅ የእግዚአብሔር አምላክ ቤተመቅደስ ከጣና ሐይቅ በቅርብ እርቀት የሚገኝና ከባህር ዳር አየር መንገድ መሄጃ ገባ ብሎ ይገኛል አስደናቂ ቤተመቅደስ ነዉ፣እናም በተሻለ መንገድ መልማትና ማደግ የሚችል ስለሆነ ሁላችንም በንፁህ ሃሳብም ሆነ በገንዘብ መደገፍ ብንችል ታላቅ የበረከት እና የፅድቅ ሥራ ነዉና እንበርታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ከወዳጅህና ከባለሟልህ ከቅዱስ ገብርኤል ፀጋና በረከቱን አብዝተህ አድለን።

"ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር አጭሩ ዮሐንስ በመባል የሚታወቀው ፃድቅ አንድ ሰው ኅጢአት ሲፈጽም ባየ ቁጥር ያለቅስ ነበር፥ሰይጣን የሰው ልጆችን በኅጢአት ለመጣል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እያሰበም ዘ...
27/04/2026

"ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር አጭሩ ዮሐንስ በመባል የሚታወቀው ፃድቅ አንድ ሰው ኅጢአት ሲፈጽም ባየ ቁጥር ያለቅስ ነበር፥ሰይጣን የሰው ልጆችን በኅጢአት ለመጣል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እያሰበም ዘወትር ያነባ ነበር፥ሁልጊዜ ወንድሜ ዛሬ፥በኅጢአት ወደቀ ምናልባት እኔ ደግሞ ነገ እወድቅ ይሆናል እርሱ ከወደቀ በኋላ በንሰሓ ሊነሳ ይችላል እኔ ግን እዚያው ወድቄ ልቀር እችላለሁ ይል ነበር።

ዮሐንስ የታዛዥነት ምልክት ነው ገዳም ውስጥ ሳለ የገዳሙ አበምኔት አባ ባይሞን ደረቅ እንጨት በትር ሰተውት ተክለህ ውሃ አጠጣ ቢሉት በቀን ሁለቴ በእግሩ እረጅም መንገድ በመመላለስ በቀን ሁለቴ ያጠጣ ነበር ከ ከ3 ዓመት በኋላም ደረቁ እንጨት ለምልሞ ፀደቀ ፍሬም አፈራ አባ ባይሞይም የታዛዡን እና የትሁቱን ፍሬ ቅመሱ እያሉ ለገዳም ዓባቶች ሰጡ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።

በክርስቶስ ፊት ተንበርክካችሁ የምታቀርቡት ምስጋናና ጸሎታችሁ አይቋረጥ የማለዳውን ብርሃን የምናይ የነገ ሰዎች ይበለን ሰላም እደሩ!!
26/04/2026

በክርስቶስ ፊት ተንበርክካችሁ የምታቀርቡት ምስጋናና ጸሎታችሁ አይቋረጥ የማለዳውን ብርሃን የምናይ የነገ ሰዎች ይበለን ሰላም እደሩ!!

"የጣናዋ ንግስት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን የአምሳለ ገነትዋ ባህር ዳር ከተማና እንዲሁም የኢትዮጵያዉያን በሙሉ ልዩ ዓርማና ምልክት}" የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እና ምድራዊም ቤተ...
26/04/2026

"የጣናዋ ንግስት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን የአምሳለ ገነትዋ ባህር ዳር ከተማና እንዲሁም የኢትዮጵያዉያን በሙሉ ልዩ ዓርማና ምልክት}" የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እና ምድራዊም ቤተመንግስቱ የሆነችዋ "(የቀበሌ 14 ቷ)" ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን በህዝበ ክርስትያኑ ፅኑ ህምነትና ቁርጠኝነት እንዲህ የተዋበና ያማረ ህንፃ ቤተመቅደስ ሠርቶ በማጠናቀቅ ይህዉ ዛሪ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ በዚዕች ቅድስት ዕለት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ታላቁ ብፁህ አባታችን አቡነ አብርሃም በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ የምርቃ ስነስርዓቱ ሊጠናቀቅ ችሎአል እንኳንም ደስ አላችሁ እንኳንም ደስ አለን እናም እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ታላቅ በዓል የተገኘነዉንም ሆነ በተለያየ ምክንያት ያልተገኙትን ወንድም እህቶችን የእናትነትዋን ፍቅር በሁላችንም ላይ ያሳድርብን ፀጋና በረከትዋንም አብልጦ በእኛ በምድራዊ ልጆቹ ላይ አብዝቶ ያድለን!

በዛሬው እለት በስርዓተ ቤተክርስቲያን ጋብቻችሁን የፈፀማችሁ እህት ወንድሞቼ በእግዚአብሔር ፊት የገባችሁት ቃል ኪዳን ለዘላለም የጸና፣ በፍቅርና በትዕግስት የታጀበ ይሁንየአብርሃምና የሳራን፣ ...
26/04/2026

በዛሬው እለት በስርዓተ ቤተክርስቲያን ጋብቻችሁን የፈፀማችሁ እህት ወንድሞቼ በእግዚአብሔር ፊት የገባችሁት ቃል ኪዳን ለዘላለም የጸና፣ በፍቅርና በትዕግስት የታጀበ ይሁን
የአብርሃምና የሳራን፣ የይስሐቅና የርብቃን ጋብቻ ያርገው። እንኳን ደስ አላችሁ!

ፍቅራችሁ እንደ ቤተክርስቲያን መሠረት የጸና፣ ቤታችሁም የምስጋና መገኛ ይሁን ወንድዬ።

ቅዱስ ገብርኤል ቸር ወሬ ያሰማን።
25/04/2026

ቅዱስ ገብርኤል ቸር ወሬ ያሰማን።

"ድንቅ አድባር ባህር ዳር ከተማ አርማና ልዩ ምልክት የሆነችዉ የቀበሌ 14 ቷ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን የጣናዋ ንግስት ድንቅ ቤተመቅደስ የእግዚአብሔር አምላክ ማደርያዉ እና ምድ...
25/04/2026

"ድንቅ አድባር ባህር ዳር ከተማ አርማና ልዩ ምልክት የሆነችዉ የቀበሌ 14 ቷ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስትያን የጣናዋ ንግስት ድንቅ ቤተመቅደስ የእግዚአብሔር አምላክ ማደርያዉ እና ምድራዊ ቤተመንግስቷ የባህር ዳር ህዝበ ክርስትያን በሙሉ እንዲሁም በዉጭም ያላችሁ በገንዘባችሁ በጉልበታችሁ በንፁህ አሳባችሁ አግዛችሁ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ህንፃ ቤተመቅደስ በዘመኑ ጠቢባንና መሐንዲሶች በአማረ ኪነ ጥበብ ተሰርታ በመጠናቀቅዋ ዛሬ በቀን 17/08/2018 ታቦተ ህጉ ወደ አዲሱ ቤተመቅደስ በአባቶች ታጅቦ ስለገባ እንኳንም ደስ አላችሁ ደስ አለን ነገም በቀን 18/08/2018 በደመቀ እና በአማረ ክብር የእግዚአብሔር አምላክ ታቦተ ህግ ከመንበረ ህጉ ወጦ ይከበራል እኛም በቦታዉ ተገኝተን ከእመቤታችን ክብርና ፅድቅን እናግኝ።

አሰብን አስመልሳለሁ እያለ የሚፎክር መሪ  የስቲዲዮ ዕቃ ሰርቋል ጊታርም አስበረግገው   ነው፥የምትሉት 🤭
24/04/2026

አሰብን አስመልሳለሁ እያለ የሚፎክር መሪ የስቲዲዮ ዕቃ ሰርቋል ጊታርም አስበረግገው ነው፥የምትሉት 🤭

"በጣናዋ ገነት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 በዘመኑ የአሰራር ጥበብ በአማረ ሁኔታ እየታነፀች የምትገኘዋ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን የእናትነት ፍቅርዋ አይለዬን።
24/04/2026

"በጣናዋ ገነት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 በዘመኑ የአሰራር ጥበብ በአማረ ሁኔታ እየታነፀች የምትገኘዋ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን የእናትነት ፍቅርዋ አይለዬን።

‹‹ቂርቆስ›› ማለት የስሙ ትርጓሜ ጣፋጭ ሽቶ፤ ጥዑም መአዛ፤ ያማረ ሽቶ ማለት ነው።ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሚስ ፣ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ። ሀገራቸውም ሮም ነበር። ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅ...
23/04/2026

‹‹ቂርቆስ›› ማለት የስሙ ትርጓሜ ጣፋጭ ሽቶ፤ ጥዑም መአዛ፤ ያማረ ሽቶ ማለት ነው።

ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሚስ ፣ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ። ሀገራቸውም ሮም ነበር።

ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ ለክርስቶስ ፍቅር ራሳቸው ያስገዙ እናትና ልጅ ክርስቲያኖች ነበሩ

የሦስት ዓመት እድሜ ያለው ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ በጣኦት አምላኪዎች ተይዘው ተሰቃዩ

ለሃይማኖታቸው መጽናት እንዳለባቸው፣ ከአምላካቸው ውጪ ለጣኦት እንደማይሰግዱ አበርትተው ለሚያሰቃዩዋቸው ተናገሩ

በፈላ ውሃ ሊከቷቸው ሲሉ እናትየው ፈራች፤ በዚህን ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ አበረታት
"እናቴ ሆይ አትፍሪ አናንያ ዓዛርያና ሚሳኤልን ከእሳት ነበልባል ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ የፈላ ውሃ ያድነናል" እያለ አጠነከራት

ያመኑትን የማይከዳው አምላካችን መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አዳናቸው

ዛሬም እኛ በአምላካችን አምነን በክርስትናችን ፀንተን በእምነት ብንኖር እግዚአብሔር አይተወንም።

የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን! Christian Abrham

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christian Abrham posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Christian Abrham:

Share