21/02/2026
“እውነተኛ ጀግኖች ሰላምን ይመርጣሉ”
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ጦርነት ከጥፋትና ከስቃይ ውጭ የሚያመጣው ውጤት እንደሌለ በመግለጽ የሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ።
ዋና ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጦርነት የሚያስከትላቸውን አስከፊ ጠባሳዎች በዝርዝር አስፍረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ የጦርነት ትርፍ “ሞት፣ ጥፋት፣ መፈናቀልና ረሃብ ብቻ” መሆኑን አሳስበዋል።