AB Business

AB Business Business channel

 #ማስታወቂያየዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት የምትችሉ መሆኑነ እንገልጻለን።Website:  https://student....
08/10/2025

#ማስታወቂያ
የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት የምትችሉ መሆኑነ እንገልጻለን።
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot:

Enkuan Aderesachihu!
28/09/2025

Enkuan Aderesachihu!

 #የ2017 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የተጠቃለለ መረጃ።==========================በሀገር ደረጃ 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50% በላይ በማምጣት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፏል...
14/09/2025

#የ2017 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የተጠቃለለ መረጃ።
==========================
በሀገር ደረጃ 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50% በላይ በማምጣት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፏል። ፈተናውን ከወሰዱ 585086 ተማሪዎች ውስጥ 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል።

የት ተመዘገበ ?

በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፦

➡️ 591 ወንድ ተማሪ ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት

➡️ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ ፦

➡️ 562 ወንድ ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት

➡️ 548 ከሴት ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት

1,249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል። ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 114 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በማሳለፍ መሻሻል ታይቷል።

መቶ በመቶ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉት 50 ትምህርት ቤቶች ናቸው።
ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር የት አለፈ ?

" ዘንድሮ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።

በዘንድሮ አመት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል ተብሏል።

ክልሎች ፦
- አዲስ አበባ፣
- ሐረሪ
- አማራ ክልል ናቸው።

ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው አመት ያለፈው ተማሪ ቁጥር 36,409 ነበር።

በጾታ ስብጥር ፦
30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል።
18,478 ሴት ተማሪ አልፏል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት

ወንድ 591/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
ሴት 579/600 ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ
ወንድ 562/600 አምቦ አምቦ ቦርዲንግ ስኩል።
548 /600 ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት።

አማካይ ውጤት
87 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
86 በመቶ ዓለማቀፍ ትምህርት ቤቶች
5.4 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች
51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት
በሀገር አቀፍ ደረጃ 2,384 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።
አዲስ አበባ ከተማ 888 ተማሪዎች ከ500 በላይ በማስመዝገብ ከሁሉም ክልሎች አንደኛ ደረጃ መያዝ ችላለች። ኦሮሚያ 794 እና አማራ 385 በመያዝ ይከተላሉ።

ውጤት መቼ ይለቀቃል ?

" ውጤት እስከ ነገ መስከረም 5/2018 6:00 ሰዓት ይለቀቃል "
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

መልካም አዲስ ዓመት!
10/09/2025

መልካም አዲስ ዓመት!

  በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ...
15/11/2024


በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

  በ2017 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣች...
15/11/2024


በ2017 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 12 እና 13/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች በነበራችሁበት ካምፓስ ብቻ የምትስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ

በ2017 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

የጥሪ ማስታወቂያለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉበ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪ...
14/11/2024

የጥሪ ማስታወቂያ

ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የገባችሁና ወደ Freshman Program መግቢያ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ፤
የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በሰላም ግቢ (Selam Campus) የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች በፔዳ ግቢ (Peda Campus) የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 16 - 18 ቀን 2017 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

#ማሳሰቢያ፤
1. ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣
ብርድ ልብስ፤ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፤
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፤ አራት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

2. በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ህዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

3. በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደ ፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ201...
12/11/2024


በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
- የስፖርት ትጥቅ።

 በ2017 የትምህርት ዘመን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደተቋም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለ...
11/11/2024


በ2017 የትምህርት ዘመን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደተቋም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ!፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተ...
10/11/2024

ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

የሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎችና የ2016 ሪሜዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ሕዳር 12 እና 13/ 2017ዓ.ም ሲሆን የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ትምህርት ሕዳር 16/2017ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

ጥቆማ!ወቅቱ የ ኦንላይን ስራ ነው። በሀገራችንም እየተለመደ መጥቷል ትክክለኛ ስራወችን ከሀሰተኞች መለየት ከባድ ቢሆንም። ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ባ 35 ሴኮንድ አጫጭር ፊልሞችን በማየት ዶ...
08/11/2024

ጥቆማ!
ወቅቱ የ ኦንላይን ስራ ነው።
በሀገራችንም እየተለመደ መጥቷል ትክክለኛ ስራወችን ከሀሰተኞች መለየት ከባድ ቢሆንም።
ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ባ 35 ሴኮንድ አጫጭር ፊልሞችን በማየት ዶላር የሚሰበሰብበት ነው አግኝቼበታለሁ ብሎ አንድ ወዳጀ የላከልኝ ነው።
እናንተም ሞክሩት።
ታዲያ ውጤቱን መፃፍ እንዳትረሱ።

Earn Money by Watching Youtube Videos. Withdraw Money Instantly via Paypal,Cahapp etc..

 #አጠቃላይየትምህርትአቂቅአዋጅበአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የሚመለከታቸው ፦➡️ የፌደራል፣ ➡️ የክልል➡️ ...
06/11/2024

#አጠቃላይየትምህርትአቂቅአዋጅ
በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የሚመለከታቸው ፦
➡️ የፌደራል፣
➡️ የክልል
➡️ የአካባቢ የትምህርት አስተዳደር ኃላፊዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀርቧል።

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ ተመርቷል፡፡

ረቂቁ ምን ይዟል ?

🟢 የትምህርት ደረጃና ጥራት ከሚጠበቀው በታች የወረደ መሆኑ ሲረጋገጥ የትምህርት ተቋሙ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን፣ ሌሎች ለችግሩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትና ግለሰቦች ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡

🟢 በሒደቱ የትምህርት ደረጃና ጥራት መርማሪዎችን ሥራ ለማሰናከል የሚደረጉ ተግባራት የተከለከሉ መሆናቸው ተደንግጓል።

🟢 የአጠቃላይ የትምህርት ደረጃ ጥራትን በባለቤትነት የሚያስጠብቅ የትምህርት ቁጥጥርና ክትትል አገልግሎት የሚሰጥ መንግሥታዊ ተቋም በትምህርት ሚኒስቴር ሥር እንደሚቋቋም ተካቶበታል፡፡

🟢 የመንግሥት ዋነኛ ተግባር ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ሕፃን ለአጠቃላይ ትምህርት ያለውን መብት ተግባራዊ ማድረግ፣ ተማሪውም የአንደኛና መለስተኛ ትምህርቱን ለመከታተል ያለበትን ግዴታ መወጣቱን ማረጋገጥ ያስችላል።

🟢 በትምህርት ዘርፍ ለሚሳተፉ ባለሀብቶችና ሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት፣ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግና አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ማበረታቻ ይሰጣል።

🟢 ስለትምህርት ክፍያ አለመኖር በሚያብራራው አንቀጽ በማንኛውም የመንግሥት አጠቃላይ የትምህርት ተቋም ውስጥ በመደበኛው የትምህርት መርሐ ግብር ከሚማር ተማሪ ከወላጆች ወይም ከአሳዳሪዎች የትምህርት ክፍያ፣ የመማርያ መጻሕፍት ዋጋ ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ መቀበል ክልክል ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡

🟢 ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ድንጋጌው ቢኖርም ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ አይቻልም።

🟢 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መግቢያ ከአራት ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ሲሆን፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜ ደግሞ ሰባት ዓመት ተደርጓል፡፡

🟢 ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ተደንግጓል። እንግሊዝኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይሰጣል። እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሉ በሚመርጠው መሠረት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት እንዲሰጥ ይደረጋል።

🟢 ማንኛውም ሰው ተገቢው የማስተማር ሥራ ፈቃድ ሳይኖርው በአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመምህርነት ሊሠራ እንደማይችል የተደነገገ ሲሆን፣ ለዚህ የሚረዳና የሥራ ፈቃድ አሰጣጥን የተመለከተ ስታንዳርድ መመርያ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይወጣል።

🟢 ከቅድመ ሥራ ሥልጠና በኋላ በመምህርነት የሚመደብ ሰው በቅድሚያ የሁለት ዓመት የትውውቅ ሥልጠና የመከታተልና ለዚህም የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና የማለፍ ግዴታ አለበት። ይህን ግዴታ ከተወጣ በኋላ በዚህ አንቀጽ የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጠው ተደንግጓል፡፡

🟢 የመምህራን የሙያ ፈቃዱ በየሁለት ዓመቱ መታደስ ያለበት ሲሆን፣ ዕድሳቱ ከማንኛውም የፈቃድ ክፍያ ነፃ ተደርጓል፡፡ ይህ ዕድሳት ለመምህራን ደረጃ ዕድገት እንደሚረዳ ተቀምጧል፡፡

🟢 በውጭ አገር ማኅበረሰቦች የሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በጀት በአገራቸው መንግሥት 30 በመቶ የሚደገፉ እንደሆኑ፣ ቀሪውን 70 በመቶ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማምጣት አለባቸው።

🟢 ኢትዮጵያ ውስጥ በሚቋቋሙ የውጭ አገር ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶችና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከሚመለከተው አገር የሥራ ፈቃድ ማምጣት እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

Address

143
Bahir Dar
196

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AB Business posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share