11/01/2023
የውስጥ ቀጋ ለውጭ አልጋ በአልጋ የሆኑ አመራሮች ፋኖን ማሳደድ ሊያቆሙ ይገባል‼️
***
የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አኩሪ ጀብድን በጋሸና ግንባር ፈፅሞ የተለመለሰ ፋኖ ጌታቸው ደሴ በግፍ እስር ላይ ነው ።
የአማራ ፋኖ በባሀር ዳር የህውሃት ሀይል የአማራን ርሰት በመውረር ፣ህዝባችንን ለማዋረድ በሶስት ዙር ወረራ ባካሄደበት ወቅት በቀደምት አማራ አባቶቻችን የፋኖነት ታላቅ እሴት ፣ ወኔ እና አልበገር ባይነት በመሰባሰብ የመጣውን ሀይል በመጣበት መንገድ ያናገረ የፋኖ ተቋም ነው ።በዚህ ታላቅ አማራዊ ተጋድሎ ሶስት ጓዶቹ የከበረ መስዕዋትነት የከፈሉ ሲሆን ፤አስራ ሰባት ጀግና አባላቱ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው የሚታወስ ነው ።
ነገር ግን ይህ ሁሉ ለአማራ ህዝብ የተከፈለ ታላቅ መስዕዋትነት ተረስቶ ፤ትላንት እያለ በእዬ ቀኑ ሲያውጅ የነበረ መንግስታዊ ስርዓት ፤ያለህ ይዘህ ውጣ የአማራ ህዝብ አድን ሲል የነበረ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮሽ ባለ ቁጥር የአማራ ፋኖን በማሰር ፣በማሳደድ እንዲሁም በማዋከብ ላይ ይገኛሉ ።የዚህ መንግስታዊ አፈና ሰለባ የሆነው ፋኖ ጌታቸው ደሴ ነው ።
በመሆኑም መንግስታዊ ስርዓቱ ከዚህ አስነዋሪ ተግባሩ እንዲቆጠብ እንዲሁም ጓዳችን ፋኖ ጌታቸው ደሴ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀው እናሳስባለን ።
በመጨረሻም ለመላው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት እና የፋኖ ደጋፊዎች ፋኖ ጌታቸውን ደሴ በዘጠነኛ ፓሊስ ጣቢያ በመገኘት ያለንን አጋርነት ፣አብሮነት እና አንድነት እንዲሁም በፍ/ቤት ቀጠሮው ቀን ማለትም ጥር 9/2015 ዓ.ም የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመገኘት ያለንን ፍፁም አንድነት እንገልፅ ዘንድ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጥሪውን ያስተላልፋል ።
ፋኖነት የአማራ ህዝብ ዋስትና ነው ።
ፋኖነት ይፋፋም ፤ፋኖነት ይለምልም ‼️