የአማራ ወጣቶች ማህበር /Amhara Youth Association Official

የአማራ ወጣቶች ማህበር /Amhara Youth Association  Official Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአማራ ወጣቶች ማህበር /Amhara Youth Association Official, Youth Organization, Bahir Dar.

የአማራ ወጣቶች ማህበር ለማናቸውም የፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች የማይወግን ፤ ነፃ ማህበር ሆኖ በሚመለከታቸዉ አካላት እዉቅናና ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 194 መሰረት ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በ1995 ዓ.ም የተመሠረተ ማህበር ነው።

በአባላት ገቢ አሰባሰብ የታዩ ክፍተቶችን በቁጭት ለመሙላትና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል የግምገማ መድረክ ተካሄደ።የባህር ዳር ከተማ አማራ ወጣቶች ማህበር የ2018...
19/06/2026

በአባላት ገቢ አሰባሰብ የታዩ ክፍተቶችን በቁጭት ለመሙላትና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል የግምገማ መድረክ ተካሄደ።

የባህር ዳር ከተማ አማራ ወጣቶች ማህበር የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ አድራጎት ስራዎች ዝግጅት እና የአባላት ገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ያተኮረ ሰፊ የግምገማና የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ማዕከል በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የአማራ ወጣቶች ማህበር አመራሮችና፣ አጋር አደረጃጀት አመራሮች የከተማውና የሁሉም ክፍለ ከተማ የወጣቶች መሪዎች ተገኝተዋል።

ማህበሩ በ2018 ዓ.ም ወጣቱን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያከናወናቸውን ተግባራት የገመገመ ሲሆን በሁሉም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የማህበሩ መዋቅሮች እስካሁን ስላላቸው የአባላት ቁጥርና አጠቃላይ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

አመራሮቹ በቀጣይ በተለይም በክረምት ወራት የሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ወጣቱን በንቃትና በባለቤትነት ስሜት ማሳተፍ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ማህበር በአሁኑ ወቅት በከተማ ደረጃ 12,750 የወጣት አባላት መዋቅር እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት ጋሻው አዘነ ባደረጉት ንግግር፤ ከተማዋ ያላትን ሰፊ አቅም ያህል የአባላት ገቢ አሰባሰብ አፈፃፀሙ ከሌሎች የክልሉ ከተሞች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም“ይህ አፈፃፀም ከከተማዋ ስምና ከወጣቱ ቁጥር ጋር የማይመጥን በመሆኑ፣ በቀሪዎቹ ጊዜያት ያሉትን ተግዳሮቶች በቁርጠኝነት በመፍታት እያንዳንዱ መዋቅር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ይኖርበታል” ሲሉ አሳስበዋል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ማህበሩን በፋይናንስና በአደረጃጀት ረገድ ይበልጥ ለማጠናከር በገቢ አሰባሰብ ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠንከር ያለ አቅጣጫና መመሪያ ተቀምጧል። ለዚህም ስራ ስኬታማነት ተደጋጋሚ ድክመት የሚያሳዩና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው የክፍለ ከተማም ሆነ የከተማ ደረጃ አስተባባሪዎች ላይ የአመራር መተካካት እርምጃ እንደሚወሰድ በግልፅ ተመልክቷል።

የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበር ዋና ፀሀፊ ሙላት ባይሌ ለማንኛውም ተቋማዊ ስኬት መሰረቱ ጠንካራ ስራ አስፈፃሚና የማይናወጥ መዋቅር መሆኑን አስገንዝበዋል። ዋና ፀሀፊው “ጠንካራና ቁርጠኛ አመራር ሲኖር ማንኛውንም ዕቅድ አቅዶ ስኬታማ ማድረግ ይቻላል፤ ስለሆነም አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነትና በትጋት መስራት ይጠበቅብናል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ማህበር ዋና አስተባባሪ ወጣት በላይነህ በበኩሉ፣ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተመለከተ ማህበሩ በከተማ ደረጃ ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን ስራዎችና ዝርዝር ዕቅድ አቅርቧል። ዋና አስተባባሪው በአፈፃፀም ዙሪያ የታዩትን ክፍተቶች አስመልክቶ ሲያብራራ፡ “ይህ ዝቅተኛ አፈፃፀም ወድቀን የምንቀርበት ሳይሆን፣ ይበልጥ በቁጭት ተነሳስተን ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን የምንሰራበት ማነቃቂያ ነው፤ በቀሪው ጊዜ የሚጠበቅብንን የአባላት ክፍያ በአግባቡ በማሰባሰብ የማህበራችንን ግብ እናሳካለን” ሲል ተናግሯል።

ዘጋቢ፥ያደለው ጌጡ


አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

"ለሴት ዱላ እንጂ ምክር አይገባትም" "ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ" "ወንድ ባለ በዕለት ሴት ባለች በዓመት" "ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ"እነዚህን እና መሰል አባባሎች ለዘመና...
18/06/2026

"ለሴት ዱላ እንጂ ምክር አይገባትም" "ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ" "ወንድ ባለ በዕለት ሴት ባለች በዓመት" "ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ"
እነዚህን እና መሰል አባባሎች ለዘመናት ስንደጋገም ኖረናል። እንደ ቀልድ፣ እንደ ተረት፣ እንደ ጥበብ ተቀብለናቸዋል። ግን እነዚህ አባባሎች በሴት ልጆች ላይ የፈጠሩትን እውነተኛ ተጽዕኖ ቆም ብለን አስበነው እናውቃለን?

ስንት ሴት ልጆች "ሴት ናት" ተብለው ከትምህርት ገበታቸው ተነስተዋል? ስንቶች ድህነትና ዕድል ማጣት ገፍቷቸው በሌሎች ቤቶች የቤት ሠራተኛ ሆነው ተቀጥረዋል? ስንቶች በሚሠሩበት ቤት ውስጥ ከሚገባቸው ጥበቃና ክብር ይልቅ ጥቃትና ብዝበዛ አጋጥሟቸዋል?
በተለይ በቤት ሠራተኝነት የሚሠሩ አንዳንድ ሴት ልጆች ለወሲባዊ ጥቃት ይጋለጣሉ። አንዳንዶቹ በግዳጅ ይደፈራሉ፣ ድምፃቸውን የሚሰማ አያገኙም፣ ፍትህም ከእጃቸው ይርቃል። አንዳንዶቹ ያልተፈለገ እርግዝና ይገጥማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ ለተለያዩ በሽታዎች እና ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ይሆናሉ።

ከዚያ በኋላ የሚከተለው ከዚህም የባሰ ህመም ነው። ከቤተሰብ ድጋፍ የተለዩ፣ በማህበረሰብ የተገለሉ እና መድረሻ ያጡ አንዳንድ ሴቶች ወደ ጎዳና ይገፋሉ። እዚያም ልጃቸውን ለማሳደግ የሚያስችል መኖሪያ፣ ጤና አገልግሎት ወይም ድጋፍ ሳይኖራቸው በከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ።

እንግዲህ ጥያቄው ይህ ነው፤ የእነዚህ ሴቶች መከራ በአንድ ቀን የተፈጠረ ነው? ወይስ ለዘመናት ሴትን ዝቅ አድርገው በሚመለከቱ አስተሳሰቦችና አባባሎች የተገነባ ማህበራዊ ችግር ነው?
ሴት ልጅን ከትምህርት ስናስቀር፣ ከዕድል ስናርቅ፣ ከክብር ስናጎድል መጨረሻው የአንዲት ሴት ብቻ ጉዳት አይሆንም፤ የማህበረሰብ ጉዳት ይሆናል።

ሴቶችን የሚያዋርዱ አባባሎችን ከመድገም ይልቅ፣ ሴት ልጆች እንዲማሩ፣ እንዲበቁ፣ ከጥቃት እንዲጠበቁ እና ሕልማቸውን እንዲያሳኩ የምንሰራበት ብሩህ የአዕምሮ እሳቤ በሁላችን እንገንባ
ሴትን ማክበር የሰብአዊነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፍትህ፣ የልማት እና የትውልድ ግንባታ ጉዳይ ነው።

አለምነው ጣሰው



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

የአሜሪካዊው ፋንቱ ማንዶዬ ሞርጋን ፍሪማን በጎ ልብ እና የሰብዓዊነት አርአያነትበዓለም ዙሪያ በሚማርክ ጥልቅ ድምፃቸው እና አስደናቂ የትወና ብቃታቸው የሚታወቁት አንጋፋው ተዋናይ ሞርጋን ፍሪ...
17/06/2026

የአሜሪካዊው ፋንቱ ማንዶዬ ሞርጋን ፍሪማን በጎ ልብ እና የሰብዓዊነት አርአያነት

በዓለም ዙሪያ በሚማርክ ጥልቅ ድምፃቸው እና አስደናቂ የትወና ብቃታቸው የሚታወቁት አንጋፋው ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን፣ ከኪነጥበብ ስራቸው ባሻገር በዓለም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚተጉ ታዋቂ የሰብዓዊ መብትና የበጎ አድራጎት አምባሳደር መሆናቸው ይነገራል።

የሳቸው ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች በማህበረሰቡ ውስጥ አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር ያላቸውን ጥልቅ ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው።ከተዋናዩ የጎላ አስተዋፅኦዎች መካከል በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርጉት ድጋፍ በዋናነት ይጠቀሳል። አውዳሚ የሆኑ አውሎ ነፋሶች ባስከተሉት አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን በግንባር ቀደምትነት አስተባብረዋል።

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ አደጋ ለሚጎዱ ሰዎች ፈጣን እርዳታ ለማድረግ "የግሬናዳ የዕርዳታ ፈንድ" (Grenada Relief Fund) የተሰኘ ኢኒሼቲቭ የነበራቸው ሲሆን፣ ይህ ተቋም አሁን ላይ “ፕላን ኢት ናው” (Plan It Now) ወደሚባል ዓለም አቀፍ ድርጅት ተሸጋግሮ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ለትውልድ መቅረጽ ቁልፍ የሆነው ትምህርት የሌላኛው የበጎ አድራጎት ስራቸው የማዕዘን ድንጋይ ነው።

እ.ኤ.አ. በ1991 በሚሲሲፒ ግዛት ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ታዳጊዎች የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማስፋፋትና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ከልጃቸው ጋር በመሆን "የታላሃቺ ሪቨር ፋውንዴሽንን" (Tallahatchie River Foundation) መስርተዋል።

ከዚህም ባሻገር፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለእንስሳት ደህንነት ልዩ ትኩረት የሚሰጡት ፍሪማን፤ እንደ 'ሚሲሲፒ የእንስሳት አድን ማህበር' ያሉ ድርጅቶችን በንቃት በመደገፍ እና በእንስሳት ህክምና ኮሌጆች ውስጥ የጥናትና ምርምር ማዕከላትን በገንዘብ በማገዝ ላይ ይገኛሉ።

በእነዚህና መሰል ሰብዓዊ ተነሳሽነቶች፣ ሞርጋን ፍሪማን ተሰሚነታቸው እና ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ከፊልም ኢንዱስትሪው መድረክ እና ከካሜራ ዕይታ ውጭ ጭምር ለአለም ወጣቶች ትልቅ የማህበረሰብ ተቆርቋሪነት ማሳያ ሆኗል።

ዘጋቢ፥ያደለው ጌጡ


አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://
Youtube:- https:/aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com//www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

አውራ አምባ፡ በእኩልነት፣ በሰላም እና በትጋት የተገነባ ማህበረሰብአውራ አምባ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም፣ በእኩልነት፣ በመተባበር እና በሰብአዊነት እሴቶች ላይ የተመሰረተ ልዩ ማህበረሰብ ነው...
17/06/2026

አውራ አምባ፡ በእኩልነት፣ በሰላም እና በትጋት የተገነባ ማህበረሰብ

አውራ አምባ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም፣ በእኩልነት፣ በመተባበር እና በሰብአዊነት እሴቶች ላይ የተመሰረተ ልዩ ማህበረሰብ ነው። የማህበረሰቡ ጉዞ የጀመረው መሥራቹ ዶክተር ዙምራ ኑሩ በሕፃንነቱ በማህበረሰቡ ውስጥ የተመለከታቸውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊቶች ለመቀየር ባለው ፍላጎት ነበር።

የአውራ አምባ መሠረታዊ እሴቶች መካከል የሴቶችና ወንዶች እኩልነት ቀዳሚ ስፍራ ይይዛል። ማህበረሰቡ ሴቶችና ወንዶች በክብር፣ በመብት እና በኃላፊነት እኩል መሆናቸውን በተግባር ለማሳየት ሲሰራ ቆይቷል።
እንዲሁም ሰላምና አንድነት የሚመጡት ሰዎች እርስ በርስ በአክብሮት ሲኖሩ እና ሌሎችን እንደ ራሳቸው ሲያስቡ መሆኑን ያምናል። ማንኛውም ሰው በራሱ ላይ እንዲደረግ የማይፈልገውን ነገር በሌላ ሰው ላይ እንዳያደርግ የሚገልጸው የመከባበር መርህ የማህበረሰቡ አንዱ መሠረታዊ እሴት ነው።

በአማራ ክልል ውስጥ አውራ አምባን የማያውቅ ሰው አለ ማለት አስቸጋሪ ነው። ማህበረሰቡ በእውነት፣ በፍትህ እና በተግባራዊ ሰብአዊነት የተመሰረተ አኗኗር በመከተሉ ብዙዎች ዘንድ ተከባብሮ ይጠቀሳል። በአውራ አምባ አስተሳሰብ ውስጥ “የኔ” ከሚለው ይልቅ “የእኛ” የሚለው የጋራ ኃላፊነትና መተባበር ይበልጥ ይጎላል። ለሐቅ ታማኝ መሆን፣ ስርቆትን መጠየፍ፣ ለሥራ ክብር መስጠት እና ከጥላቻ የራቀ አስተሳሰብ መኖር ማህበረሰቡ የሚታወቅባቸው መልካም እሴቶች ናቸው።

የአውራ አምባ ማህበረሰብ ጉዞ ቀላል አልነበረም። በብዙ ፈተናዎች፣ ችግሮች እና መሰናክሎች ውስጥ በማለፍ የዛሬውን ደረጃ ደርሷል። ይሁን እንጂ የማህበረሰቡ አባላት በትጋት፣ በጽናት እና በጋራ ሥራ እሴቶቻቸውን ጠብቀው ማህበረሰባቸውን ማጠናከር ችለዋል።
ለወጣቶች ከአውራ አምባ የሚወሰደው ትልቅ ትምህርት የሰላም ባህልን ማጎልበት፣ ለሥራ ክብር መስጠት፣ መተባበርን ማጠናከር፣ እውነትን መከተል እና ሰውን በሰውነቱ ብቻ ማክበር ነው። እነዚህ እሴቶች በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ሲተገበሩ ለልማት፣ ለአንድነት እና ለዘላቂ ሰላም ጠንካራ መሠረት ይሆናሉ።

ወጣቶች ከእንደዚህ ያሉ መልካም ተሞክሮዎች በመማር በማህበረሰባቸው ውስጥ የሰላም፣ የመተባበር፣ የእውነት፣ የፍትህ እና የልማት እሴቶችን እንዲያጎለብቱ ማበረታታት ተገቢ ነው። አውራ አምባ በትጋትና በጋራ ጥረት ማህበረሰብ መቀየር እንደሚቻል የሚያሳይ ሕያው ምሳሌ ነው።


አለምነው ጣሰው



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

በአማራ ክልል የኤች አይ ቪ ስርጭት እያገረሸ በመሆኑ የወጣቶች ግንባር ቀደም ተሳትፎ እንዲጠናከር ተጠየቀበአማራ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭት ባልተጠበቀ ሁኔታ እየተጠናከረ መምጣቱን የ...
16/06/2026

በአማራ ክልል የኤች አይ ቪ ስርጭት እያገረሸ በመሆኑ የወጣቶች ግንባር ቀደም ተሳትፎ እንዲጠናከር ተጠየቀ

በአማራ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭት ባልተጠበቀ ሁኔታ እየተጠናከረ መምጣቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ቫይረሱ በማህበረሰቡ ላይ እየፈጠረ ያለው ስጋት ከፍተኛ መሆኑን ቢሮው በመግለጽ አፋጣኝ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንደሚያስፈልግ አሳሰበ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት እንደገለጹት፣ በበሽታው ማገርሸት ዋና ምክንያት በማህበረሰቡ ዘንድ የታየው መዘናጋት እና የመከላከያ እርምጃዎች በቂ ትኩረት አለመሰጠት ነው። በተለይ የወጣቶች እድሜ ክፍል ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆኑ በንቃት መሳተፋቸው ወሳኝ መሆኑን አመለከቱ።

በዚህ መሰረት የክልሉ ጤና ቢሮ የወጣቶች ንቅናቄ መድረኮችን በማጠናከር በማህበረሰቡ ዘንድ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን ገለጸ። መድረኮቹ በተለይ ወጣቶችን በመምራት የቫይረሱን መከላከል፣ ትክክለኛ መረጃ ማስተላለፍ እና የተሳሳተ አመለካከት መቀነስ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።

በመግለጫው መሠረት፣ ቫይረሱ በክልሉ እየተጠናከረ መምጣቱ ከተቀጠለ ለነገ ትውልድ ከፍተኛ እዳ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። ስለዚህ ሁሉም ባለድርሻ አካላት—መንግስታዊ ተቋማት፣ ማህበረሰብ እና በተለይም ወጣቶች—ኃላፊነታቸውን በትጋት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጀመረው የንቅናቄ እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ በቀጣይ ቀናት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ የወጣቶች ማህበራት እና የወጣት አደረጃጀቶች ዋነኛ ድርሻ እንዲወጡ ተጠይቀዋል።/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

እድሉ እንዳያመልጥዎ🔊🔊🔊📢📢📢📢ነፃ የህክምና አገልግሎት በአፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታልየከንፈርና ላንቃ ቀዶ ህክምና ከSmile Train ጋር በመተባበር ሁልጊዜ በሆስፒታላችን በነፃ እየተሰጠ ሲሆን...
16/06/2026

እድሉ እንዳያመልጥዎ🔊🔊🔊📢📢📢📢
ነፃ የህክምና አገልግሎት በአፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታል
የከንፈርና ላንቃ ቀዶ ህክምና ከSmile Train ጋር በመተባበር ሁልጊዜ በሆስፒታላችን በነፃ እየተሰጠ ሲሆን በልዩ ዘመቻ ከሰኔ 15/2018 እስከ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ህክምናውን ለመሰጠት ሙሉ ዝግጅታችን ጨርሰናል። በመሆኑም ሁሉም ችግሩ ያለባቸው የእድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ላልሰሙ መረጃውን እንድታጋሩ በአደራ እናሳስባለን።

አስቴር መኩሪያው /አወማ



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

https://youtu.be/Ae-s3rI4FTc?si=98eUTXHe5JeZsM8p  ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!website :-https://aya.or...
16/06/2026

https://youtu.be/Ae-s3rI4FTc?si=98eUTXHe5JeZsM8p



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተገኙ ከጥቅም ውጭ የሆኑ መገልገያ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከ 1.3ሚሊ...

በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ847 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸየማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት...
15/06/2026

በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ847 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅድ ትውውቅና የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የዞኑ አመራሮች፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የወጣት አደረጃጀት አስተባባሪዎች እና ሌሎች ተዛማጅ አካላት ተገኝተዋል።
በወቅቱ የተደረጉ ገለጻዎች እንደሚያሳዩት፣ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ለሀገር ልማትና ማህበራዊ አንድነት ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆናቸው በቀጣይነት ተጠናክረው ሊካሄዱ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ለማህበረሰብ ጥቅም በማዋል በልማትና በማህበራዊ ድጋፍ ዘርፎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በ17 የስራ ዘርፎች ከ847 ሺህ በላይ ዜጎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። በመርሃ ግብሩም ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመልክቷል።

በተለይም የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት የማደስና የመገንባት ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ ደም ልገሳ፣ የግብርና ድጋፍ ስራዎች፣ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እና ከዲጂታል መታወቂያ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች ይካሄዳሉ።
በዚህ የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።

የአማራ ወጣቶች ማህበር በበኩሉ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ያላቸውን ተሳትፎ በማጠናከር ለማህበረሰብ አገልግሎትና ለአካባቢ ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንዲያሳድጉ ያበረታታል።

አለምነው ጣሰው



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

ለእኔ ጀግና ማለት ይሄ ነው🙏🙏🙏በኛ ማህበረሰብ በቤት ውስጥ እንደ ቡና ማፍላት፣ እንጀራ መጋገር እና  ወጥ መስራት የመሳሰሉት የማእድ ቤት ስራዎች በተለምዶ የሴቶች ተግባር ተደርገው ይወሰዱ ...
13/06/2026

ለእኔ ጀግና ማለት ይሄ ነው🙏🙏🙏

በኛ ማህበረሰብ በቤት ውስጥ እንደ ቡና ማፍላት፣ እንጀራ መጋገር እና ወጥ መስራት የመሳሰሉት የማእድ ቤት ስራዎች በተለምዶ የሴቶች ተግባር ተደርገው ይወሰዱ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ መንገዶች የመረዳዳቱ ነገር እየተጠናከረ መሄዱን እያስተዋልን ነው፤ ይህም በመልካም ጎኑ የሚታይ መሆኑን ማየት ይገባል።

ሰዎች በተለይ ወንዶች ፆታን መሰረት ያደረጉ አንዳንድ ስራዎችን ገደብ ባለማበጀት ዘመናዊነት እና ጾታዊ እኩልነት እያረጋገጡ ያሳያሉ።ይህም በሴቶች ዘንድ መከባበርን የመሰሉ እሴቶችን የሚያሳይ በመሆኑ አስደሳች ነው።

እስኪ አንድ ጥያቄ ላቅርብ🙏

የጀበና ቡና ሲባል በቶሎ የሚመጣላችሁ ምስል ምንድን ነው?????

"ፈጣን ሽክፍ ያለች ወጣት ሴት" ልትሉኝ የምትችሉበት ይመስለኛል።ነገር ግን ጉዳዩ ከዚህ አለፍ ይላል።

ወጣት ሳሙኤል በቀለ ይህን የቤት ውስጥ በጎ ልምምድ ወደአደባባይ በማውጣት የገቢ ምንጩ አደረገው ይለናል የጀርመኑ ዜና መረብ።

ይህ ግሩም ወጣት አልፎ አልፎ ተጠቃሚዎች ቡና ሲያፈላ ወይም ጀበና ሲያጥብ በሚያሳዩ አንዳንድ ያልተገባ አስተያየት ሳይሸማቀቅ ይልቁንም ጎዳና ላይ ከመውደቅና ከልመና ህይወቱን ታድጎበታል። ወጣቱ በፈተና ውስጥ ቢሆንም ግን እየታገለ መሆኑን ይገልፃል።

የሳሙኤል ህልም ትልቅ ነው። ለግዜው ግን ስራው ከእጅ ወደ አፍ እና ኑሮውን ለማሸነፍ ነው። የሚሰራበት እና የሚኖርበት ቦታ በጣም የተራራቁ ናቸው። በምንም መንገድ ቢሆን ግን ጥረቱን መቀጠሉን እንዲህ ያሳያል።

”የተወሰኑ ደንበኞች አሉኝ። ግን እስከዚህ አይደለም። ከማገኘው ገቢ መልሼ ቡና እገዛለሁ፤ የቤት ኪራይ እከፍላለሁ። ለታክሲ 2000 ብር እከፍላለሁ። የማተርፈው ነገር የለም። በጣም እየታገልኩ ነው። 10 ተኩል እነሳለሁ። 12 ሰዓት ስራ ቦታ እከፍታለሁ። ማታ 2 ሰዓት እዘጋለሁ ከጠዋት እስከማታ ነው የምሰራው። ለስራ ሰንፌ አላውቅም። ግን ይኼን ያክል አይደለም። ” ሲል የገጠመውን የህይወት ፈተና በአሸናፊነት እየተጓዘ ያለበትን መንገድ ይናገራል።

እውነት ለመናገር የስኬት ጉዞን ለመጀመር ከሁሉም የሚቀድመው ካሉበት ነባራዊ ሁኔታ ሀቅምን ያማከለ ተግባርን ለመጀመር አስቦና አቅዶ ከቤት መውጣት ፤ ከሀሳብ አለፍ ብሎም ጉዞን "አንድ" ብሎ መቀጠል ነው ።

ሳሙኤል አዲስ አበባ ውስጥ ጎፋ መብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም የሚባል ቦታ ቡና አፍልቶ መሸጥ ከጀመረ አንድ ዓመት ሆኖታል ይለናል መረጃው።

እንደአንድ ወጣት ከጥገኝነት ለመራቅ፣ ራሱን ለማስተዳደርና ነገ የተሻለ ኑሮን ለመኖር አልሞ ፆታ ሳይገድበው ለሁሉም የሚያስተምረውን መንገድ አሳይቶናልና ሊበረታታ ይገባል።



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication

የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

የደብረ ማርቆስ ከተማ የአየር በረራ መጀመር ለክልሉ ልማት እና ለወጣቶች የስራ እድል የሚያመጣው ፋይዳየደብረ ማርቆስ ከተማ የአየር በረራ አገልግሎት መጀመሩ ለከተማዋ፣ ለአማራ ክልል እና ለኢ...
13/06/2026

የደብረ ማርቆስ ከተማ የአየር በረራ መጀመር ለክልሉ ልማት እና ለወጣቶች የስራ እድል የሚያመጣው ፋይዳ

የደብረ ማርቆስ ከተማ የአየር በረራ አገልግሎት መጀመሩ ለከተማዋ፣ ለአማራ ክልል እና ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትልቅ የልማት እድል የሚፈጥር አበረታች እርምጃ ነው። ይህ የትራንስፖርት አማራጭ የጉዞ ጊዜን በማሳጠር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በረራው መጀመሩ በተለይ ለንግድ እና ለገበያ መነቃቃት አዲስ በር ይከፍታል። ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች እና ተጓዦች ወደ ከተማዋ በቀላሉ መግባት ስለሚችሉ የንግድ እንቅስቃሴው ይጠናከራል። ይህም ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
በተጨማሪም የሆቴል፣ የሬስቶራንት፣ የቱሪዝም እና ሌሎች ከአገልግሎት ዘርፎች ጋር የተያያዙ ስራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል። የጎብኚዎች ቁጥር ሲጨምር አዳዲስ የስራ እድሎች ይፈጠራሉ። ይህም ለከተማው ነዋሪዎች በተለይም ለወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ወጣቶች በተለያዩ የአገልግሎት የንግድ፣ የቱሪዝም እና የቴክኒክ ዘርፎች ውስጥ የስራ እድል ማግኘት ይችላሉ። የበረራ አገልግሎቱ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የስራ ፈጠራ እድል የሚያመጣ በመሆኑ የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ያሻሽላል።
የደብረ ማርቆስ ልምድ በሌሎች ትልልቅ እና ከፍተኛ የህዝብ ፍሰት ባላቸው የአማራ ክልል ከተሞችም ሊደገም የሚገባ ነው። የትራንስፖርት እና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲስፋፉ የክልሉ ኢኮኖሚ ይጠናከራል። ለወጣቶችም ተጨማሪ የስራ እድሎች ይፈጠራሉ።

ስለዚህ መንግስት፣ የግል ዘርፉ፣ የማህበረሰብ ተቋማት እና ህዝቡ በጋራ በመሆን መሰል የልማት ፕሮጀክቶች እንዲስፋፉ መጠየቅ፣ መወያየት እና መደገፍ ይገባቸዋል። የልማት ጥያቄዎች በአንድነት ሲቀርቡ የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል።
ዘላቂ ልማት፣ የስራ ፈጠራ እና የወጣቶች ተጠቃሚነት በመላው አማራ ክልል እውን እንዲሆን ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል።



ዘመን ተሻጋሪ የወጣቶች ደምፅ-አወማ!
አማራ ወጣቶች ማህበር ቤተሰብ ይሁኑ!
website :-https://aya.org.et/
Facebook
amharayouthheadofficehttps://www.facebook.com/
Youtube:- https://www.youtube.com/
Tiktok:-
WhatsApp:- https://whatsapp.com/channel
Telegram :- https://t.me/ayacommunication
የተደራጁ ወጣቶች የልማት አቅም ናቸው!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ወጣቶች ማህበር /Amhara Youth Association Official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share