ARCCA - Amhara Region Construction Contractors Association

ARCCA - Amhara Region Construction Contractors Association Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ARCCA - Amhara Region Construction Contractors Association, Nonprofit Organization, Bahirdar, Ethiopia Kebele 14, Chulfit Building, 4TH FLOOR, ROOM NUMBER 403, Bahir Dar.

09/01/2024

በ97 ቢሊየን ብር ወጪ 61 የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም የተመለከተ ግምገማ እና ውይይት የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አመራሮች የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው።

• ባለስልጣኑ የጎንጂ-ቆለላን ጨምሮ አራት የመንገድ ፕሮጀክቶችን ውል ተፈራረመ፡፡

• “በክልሉ ከ4ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ ነው”…
• የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ትኩረት ሠጥቶ…
• "በ2015 በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 541 ፕሮጀክቶች…

የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር በአማራ ክልል በአጠቃላይ 61 የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል። የመንገዶቹ አጠቃላይ ድምር ርዝማኔ 3 ሺህ 658 ኪሎ ሜትር ነው።

የመንገድ ግንባታዎቹ በ97 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነቡ ስለመሆናቸው የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ገልጿል።

በአዲስ ከሚሠሩ መንገዶች በተጨማሪ 3 ሺህ 664 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶችም እየተጠገኑ መኾኑ ተጠቁሟል። ከ2 ቢሊዮን 166 ሚሊዮን 529 ሺህ በላይ ብር ለመንገዶች ጥገና ተመድቦ እየተሠራ ስለመሆኑም ተነግሯል።

ውይይቱ በክልሉ የሚከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ወደ ጠንካራ አፈጻጸም ለማስገባት እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ስለመሆኑ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል።

(አሚኮ)

የደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ▪️ነጭ ሄልሜት፦ ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች▪️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች▪️ቀይ ሄልሜት፦...
28/12/2023

የደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ

▪️ነጭ ሄልሜት፦ ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች
▪️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች
▪️ቀይ ሄልሜት፦ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች
▪️አረንጓዴ ሄልሜት፦ ለሴፍቲ ሠራተኞች
▪️ግሬይ ሄልሜት፦ ለሳይት ጎብኚዎች
▪️ቢጫ ሄልሜት፦ ለጉልበት እና ለግንባታ ማሽን ኦፕሬተር ሠራተኞች
▪️ ብራዎን ሄልሜት፦ ለበያጆችና ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ቦታ ለሚሰሩ ሠራተኞች

ሠራተኞች በሥራ ወቅት በደህንነት ጉድለት ምክንያት የተለያዩ አደጋዎች እና ጉዳቶች ሲያጋጥሟቸው ይሰተዋላል፡፡ ይህንንም ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የሕግ፣ የህብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ ግንዝቤ ሥራዎች ሲሞከሩ ይታያል፡፡

በተለይም እኤአ ከ1919 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (International Labour Organization/ILO) መቋቋምን ተከትሎ በርካታ ከሠራተኛ የሥራ ደህንነት ጋር የተያያዙ መርሆዎች እያደገ መምጣቱ አይዘነጋም፡፡

ይህንንም ተከተሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ጠቅላላ ጉባዔ እኤአ በ1948 ዓ.ም ባወጣው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights-UDHR) የሥራ ላይ ደህንነት አንዱ የሠራተኞች መብት እነደሆነ ደንግጓል፡፡

የግንባታ ሥራ በራሱ እጅግ ውስብስብ ከመሆኑ ባሻገር በርካታ ሥራዎች በጉልበት የሚከናወኑ (labour intensive) በመሆናቸው ብሎም ከሥራው ባህሪ አንጻር ፈረጅ ብዙ የሥራ ክንውን የሚካሄድበት ስለሆነ በደህንነት ጉደለት ምክንያት በርካታ አደጋ እና ስጋት ሲያጋጥም ይሰታዋላል፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ሪፖርት ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በግንባታ ወቅት ቢያንስ 60ሺ ሠራተኞች ከደህንነት ጉደለት ጋር በተያየዘ ለሞት የሚዳረጉና ከባድ የአካል ጉዳት አደጋዎች እንዳሚያጋጥማቸው ጠቁሟል፡፡ ይህም ማለት በየአስር ደቂቃው ውስጥ አንድ ከባድ አደጋ ይደርሳል እንደ ማለት ነው፡፡ ሪፖርቱም በተለይ ከአጠቃላይ የሥራ ላይ አደጋዎች ውስጥ 17 ፐርሰንት ይህም ከስድስት አደጋዎች ውስጥ አንዱ የሚሆነው ገዳይ አደጋ በግንባታ ዘርፍ እንደሆነ ያትታል፡፡

የግንባታ ደህንነት ሲባል አንድ የግንባታ ፕሮጀክት ከጥንስሱ እስከ ፍጻሜው ድረስ በሚካሄዱ መጠነ ሰፊ የግንባታ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊደረጉ የሚገባቸው እንዲሁም ሊወሰዱ የሚችሉ ጥንቃቄዎች የሚይዝ አሰራር ነው፡፡

የግንባታ ደህንነትን በተመለከተም በ2005 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ደህንነት ጉዳይ ከኢንዱስትሪው ዕድገት ጋር ተያይዞ በትይዩ ትኩረት የሚሠጠው ቁልፍ ስራ መሆን እንዳለበት ይናገራል፡፡ በፈጻሚ አካላት የሚስተዋለው በፕሮጀክት ሳይቶች የሥራ አካባቢ ደህንነት ፖሊሲ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ የሚወጣው ወጪና የሚመደበው ጊዜ እንደተጨማሪ ወጪ አድርጐ የመመልከት እሳቤ በመሠረታዊነት መቀየር እንዳለበትና ለስራ አካባቢ ሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት ጥበቃ የሚወጣ ወጪ የግንባታ ወጪ በመሆኑ ትርፍ እንዳልሆነ አጥብቆ ያሳስባል፡፡

በኮንስትራክሽን ሥራ አካባቢዎች መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ባለመወሰዳቸው ምክንያት የሚደርሱ ከቀላል እስከ ከባድ የንብረትና ህይወት መጥፋት ጉዳቶች መከላከል ያሻል፡፡ እነዚን የመሰሉ አደጋዎች ለመከላለል የሚያስችል በግንባታ ሂደት መወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ በቂ ስልጠናና አፈጻጸሙን መከታተል የዋናው ሥራ አካል ተደርጎ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

የኮንስትራክሽን አካባቢ ደህንነት (Construction Site safety) የግንባታ ሂደቱ ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት መረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ተደርጐ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የኮንስትራክሽን ሥራ እንቅስቃሴ ደህንነት ማስፈን ፖሊሲው አጉልቶ ያስቀመጠበትን ሁኔታ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በበጀት አመቱ ከሚያሰራቸው ፕሮጀከቶች መካከል1ኛ. ከፖሊሴንተር እስከ አየርጤና አስፓልት, 4 መንገዶች...
18/12/2023

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በበጀት አመቱ ከሚያሰራቸው ፕሮጀከቶች መካከል

1ኛ. ከፖሊሴንተር እስከ አየርጤና አስፓልት, 4 መንገዶች ደቡብ አዋሳኝና ምስራቅ ምዕራብ አዋላኝ

2ኛ. ከአያሌው ጎበዜ ሰፈር እስከ ሶማት/ቤት

3ኛ. ከመድሃኒያለም አስፓልት እስከ ታክሲ ማዞሪያ

4ኛ. ከአማኑኤል ማድለቢያ ሱዲሰፈር አማኤልይሃ አለም፤ ሠዋለ ጥጋብ፤ ኡመር አለምፀሃይ ይበልጣል እና ታደለ ሙሃመድ ያሉ መንገዶችን የመሬትና የተፋሰስ ስራ ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ-5 እና በላይ የሆኑ፣

5ኛ. ክፍል ሁለት ዲፖ ግሪነሪያ ስራ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ ሁለት /2/ እና በላይ የሆነ

1. የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣

2. ከላይ የተጠቀሰውን ፕሮጀከት ለማሰራት አስፈላጊውን ሁሉ የሰው ሃይል፣ የማቴርያል እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን የሚያሳይ በስማቸው የታሸገ የፋይናንሽያል እና የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳቦችን ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 205 ስልክ 0582201693 ፓ.ሳ.ቁ 49 አድራሻ የማይመለስ 1500 ብር /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ማንኛውም ተጫራች የተጫራቹንና የኘሮጀክቱን ስም በግልፅ ተቀባይነት ባለው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ 21.1 ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ

6. ፐሮጀክቶች የሚጠናቀቅበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ዉ.ሁ 72.1 ላይ በተገለጸው ቀን መሰረት ይሆናል።

7. ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል/ እና ጨረታ ዋጋ/ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፖች ማህተም ማድረግ መታሸግ ይኖርባቸዋል። (አንድ ኦርጅናል እንድ ኮፒ)

8. ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል። የመጀመሪያው ሃደት/ደረጃ የቴከኒካል ሰነዶች ግምግማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴከኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብከመ ገ/ቢ/ኮቢ-01/02 በቀን 15/09/2014ዓም በተሻሻለው መመሪያ መሰረት የጨረታ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ ይህን መመሪያ በደንብ ያንብቡት።

9. የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚቀርቡት ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ የግዥና ፋይናንስ የስራ ሃደት ሆኖ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ከ2፡ 30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 21ኛ ቀን 11፡00 ታሽጎ የሚዘጋ ሲሆን ጨረታው በይፋ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ በግዢና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 205 ውስጥ ይሆናል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

10. ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ ፖ.ሳ.ቁ. 49 ቴሌ 0582206124 ፋክስ 058-222-16-26 ማግኘት ይችላሉ።

11. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በባለፈው ዓመት ውስጥ ፕሮጀከት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።

12. ማንኛውም ተጫራች ከስራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ የስራ አይነቶች ላይ የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ስራውን እንዲሰራው ይገደዳል።

13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል። ስለዚህ አሰሪ መስሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም።

14. ማንኛዉም ተጫራች በሚሞላዉ ሰነድ ላይ የሚፈጠር ስርዝ ድልዝ ከዉድድር ዉጭ የሚያደርግ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ።

15. ማንኛውም ተጫራች ከቴክኒካል ሰነዱ ውስጥ ከጠቅላላ ውሉ 10% ያህሉን ለስራ እድል ፈጠራ ለማዋል መስማማቱን የሚገልፅ ህጋዊ ማረጋገጫ ደብዳቤ አብሮ ማያያዝ አለበት። ካልሆነ ግን በጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የስራ እድል አማራጮችን ለማስፋትና ለማበረታታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር27/2009 ዓ/ም,, መሰረት ተጫራቹ ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።

16. ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17.ማንኛውም ተጫራች የመሬትና የተፋሰስ ስራ ላይ ከሁለት ፕሮጀከት በላይ መወዳደር አይችልም፡ ከሁለት በላይ ተወዳድሮ ቢገኝ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

15/12/2023

በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

🚧 “በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

ባዮቴክኖሎጂ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ  ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ነው__▪️በኢትዮጵያ  የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ  ውስጥ ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚካሄደው ጥናት ውጤት እያሳየ ነው።የኮንስት...
13/12/2023

ባዮቴክኖሎጂ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ነው
__▪️
በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚካሄደው ጥናት ውጤት እያሳየ ነው።

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (ASTU) ጋር በቅንጅት እየሠራ ያለውን የባዮቴክኖሎጂ የምርምር ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ በዩኒቨርስቲው ማዕከል አካሂዷል፡፡

የጥናትና የምርምር ሥራው የሚካሄደው ስነ- ህይወትን ( ባክቴሪያን) መሠረት ባደረገ ባዮቴክኖሎጂ የግንባታ ግብአቶችን ለማምረት እንዲሁም የመሰነጣጠቅ ችግር የሆነውን የግንባታ ፈተና ለማዳን እና ለማስወገድ ነው፡፡

ጥናቱ የሚካሄደው በዩኒቨርስቲው በተዋቀረ የጥናት ቡድን አማካኝነት ሲሆን፣ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለጥናቱ በጀት መድቦ ውጤቱን እየተከታተለ ይገኛል፡፡

ጥናቱ እየተካሄደ ያለው Microbial Bio-cement, Bio- blocks, Bio- enzyme and Brick -making machine በሚሉ አራት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

በጉዳዮቹ ላይ የጥናት ቡድኑ አባላት ዶ/ር መስፍን ታፈሰ፣ አቶ ዳንኤል ሙሉ እንዲሁም ዶ/ር ኃይሉ ሽመልስ ዝርዝር ገለፃ አቅርበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት ሙሉ ስሜ እንደተናገሩት፣ አማራጭ የግንባታ ግብአቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገር፣ የፈጠራ ሥራዎችን መደገፍና ማበረታታት የኢንስቲትዩቱ ስልጣን እና ተግባር በመሆኑ በእነዚህ ሥራዎች ዙሪያ በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህ በASTU በኩል የሚካሄደው የባዮቴክኖሎጂ ጥናት እጅግ ጠቃሚ እና አዋጭ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ የሆኑት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ ጥናቱ ከሂደት ወጥቶ በቶሎ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፣ በሁሉም ጥናት ውጤቶች ሠርቶ ማሳያ በቅርቡ ማየት እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች ይህ ባዮቴክኖሎጂ ላይ የሚደረገው ጥናት የሀገሪቱን የኮንስትራክሽን ችግር የሚፈታና ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ፣ አቅምን ያገናዘበ መኖሪያ ቤት ለማግኘት እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በሚደርስባቸው መሰነጣጠቅና በሚፈጥሩት ክፍተት በቶሎ ስለማይጠገኑ በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ኪሳራ ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል።

የASTU ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው፣ የተሰጡ ጠቃሚ አስተያየቶችን በግብአትነት በመውሰድ ጥናቶቹን ተግባራዊ በማድረግ ሥራ ላይ ለማዋል የበለጠ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና የጥናቶቹን የምርምር ውጤቶች በቅርብ እንደሚያሳዩ ቃል ገብተዋል፡፡

በዕለቱ Brick- making machine እና በዚህ ማሽን በተመረተ ብሎኬት የሚሠራ ቤት የሚታይበት መስክ በተሳታፊዎቹ ተጎብኝቷል።

13/12/2023

በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

“በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

(የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን)

Invitation to BiddersTender No. RFQ ESLSE/COR/NEG/PRF/2022/00940Ethiopian Shipping and Logistics would like to invite in...
04/12/2023

Invitation to Bidders
Tender No. RFQ ESLSE/COR/NEG/PRF/2022/00940

Ethiopian Shipping and Logistics would like to invite interested and eligible bidders for New Ware House Construction and Terminal Rehabilitation for kombolcha port and terminal branch office. upon fulfilling of the following terms and conditions.

1. Bidders who engaged in the sector shall present renewed trade license, trade registration certificate, VAT registration, current tax clearance certificates, TIN certificate, supplier list registration certificate and renewed and relevant registration on ministry of construction certification of competency for categories GC-6/BC-5 and above.

2. To access the tender document bidders shall register on ESL supplier list by using the link https://ehog.fa.em2.oraclecloud.com/fscmUI/faces/PrcPosRegister Supplier?prc Buld-300000003585149 or register at Head Office in person 10th floor at procurement department upon fulfilling trade license certificate and TIN (Taxpayer Registration Certificate) starting from the date of this announcement.

3. The bid shall be valid for the period of 45 days after the system bid closing date.

4. Bidder shall submit bid security in person at Head Office of the enterprise 10th floor procurement department and the amount of the bid security 500,000 (five hundred thousand) birr. The type of acceptable bid security is: unconditional bank guarantee or cash payment order (CPO). The bid security shall be valid for twenty-eight days (28) beyond the end of the validity period of the Bid Proposal. Which shall be remained valid for a period of 45 days +28=73

5. To create better understanding on the bid document ESL will hold pre bid conference with all bidders on the 10th date of the floating of the bid by the newspaper or by next working day at ESL head office 10th floor procurement department.

6. The deadline for bid submission is date and time of ERP System.

7. Ethiopian Shipping & Logistics Services Enterprise reserves the right to accept or reject the bids partially or totally.

Ethiopian Shipping & Logistics Services Enterprise
Tele. 011-554-9781/86

Web site www.eslse.et

ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ...
27/11/2023

ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓቱን የማብላላት ተግባር ያለውን የፋብሪካው ክፍል እና ወደ ቀጣዩ ሂደት ማስተላለፊያ ቱቦ መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር በመሆን እየተገነባ ያለውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ቀንና ማታ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ሂደትን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

(FBC)

የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ተመለከተበሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገለጹ፡፡ፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬ...
11/11/2023

የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ተመለከተ

በሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገለጹ፡፡

ፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ የሲሚንቶና የብረት ማምረቻ ፋብሪካዎችና የንግድ ሱቆች ላይ ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጓል፡፡

በተደረገው ምልከታም የ1 ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከ800 ብር እስከ 500 ብር ቅናሽ እንዲሁም 1 ቤርጋ ፌሮ በኪሎ የ15 ብር ቅናሽ ማሳየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የሲሚኒቶና ብረት ግብይት በሚደረግባቸው አካባቢዎች በተደረገው ምልከታም የሲሚኒቶ፣ የብረት እና ሌሎች የኮንስትራክሽን እቃዎች ቅናሽ ማሳየታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ቀደም ሲል ግብይቱ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተመን ወጥቶለት ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም ከታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም ወዲህ ግን በነጻ ገበያ መርህ ፋብሪካዎች ባቀረቡት ዋጋ ግብይትት መካሄድ መቀጠሉን በቅኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 800 እስከ 2 ሺህ ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ኢትዮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 250 እስከ 1 ሺህ 270፣ ሀበሻ ሲሚንቶ በ1 ሺህ 300 ብር እና ሙገር ሲሚንቶ በ1 ሺህ 350 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል÷ የብረት ገበያም በተመሳሳይ ምልከታ የተደረገበት ሲሆን በተመሳሳይ ቅናሽ የታየበት መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡

ለአብነትም 10 ቤርጋ ብረት 1 ሺህ 332 ሲሸጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 36 ብር፣ 14 ቤርጋ ፌሮ ብረት 3 ሺህ 412 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 2 ሺህ 654 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

በዘርፉ ላይ የተሰማሩት አምራቾችና ነጋዴዎች ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎችም የግንባታ እቃዎች ሸማቾች ቁጥር መቀነሱንም አመላክተዋል።

በሜሮን ሙሉጌታ
ምንጭ፡ (ፋና ብሮድካስቲንግ)

ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆ...
11/11/2023

ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ 1 ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች መገንባትን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ሪቪዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል፡፡

በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አመላክቷል።

ምንጭ፡ (አዲስ ማለዳ)

ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ አውደ ጥናት ተጠናቀቀጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአለም ባ...
06/11/2023

ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ አውደ ጥናት ተጠናቀቀ

ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአለም ባንክ ባገኘው ድጋፍ ዳር አልሀንዳስ ከተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጋር በሚያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ ላይ ለ7 ቀናት ሲመክር የሰነበተው አውደ ጥናት ተጠናቀቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ወደ ላቀ የአፈፃፀም ደረጃ ለማሸጋገር እገዛ የሚያደርጉ 28 ማንዋሎች እየተዘጋጁ ነው፡፡

በአውደ ጥናቱ መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡእንደገለፁት የማኑዋል ጥናቱ ዘመናዊ፣ ወጪ እና ጊዜን ቆጣቢ እንዲሁም ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ምቹ የሆኑ የመንገድ መሰረተ-ልማት ለማስፋፋት ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በጥናት ላይ የሚገኙት ማኑዋሎች ተጠናቀውና ፀድቀው በሥራ ላይ ሲውሉ፣ ከዚህ ቀደም በመንገድ ግንባታ ወቅት የሚያጋጥሙ የተለያዩ ችግሮችን ለመቅረፍና አዳዲስ አሰራሮችን በማካተት በከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡

ለሰባት ቀናት በተካሄደው በዚህ አውደ ጥናት ላይ ከተሳታፊ አካላት ጠቃሚ የሆኑ ግብአቶች እንደተገኙ ገልጸው፣ ለማኑዋሎቹ መዳበር ፋይዳ ያላቸውን ሃሳቦች በመሰንዘር በውይይቱ ላይ ለተሣተፉ የባለድርሻ አካላትና የአማካሪ ድርጅቱ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያበአማራ ብሄራዊ ክልላዊ ምንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ህትመቶችን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በማወዳደር ማሳተም ይ...
30/10/2023

ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ ምንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ህትመቶችን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በማወዳደር ማሳተም ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ዘመናዊ ሽንት ቤት ለማስገንባት ደረጃ 8/ስምንት /እና ከዚያ በላይ የሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ ኮንትራክተሮችን በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት ጋር ውል በመፈጸም ለበጀት አመቱ ማሳተም እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

1ኛ. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2ኛ. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው/

4ኛ. የግዢው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

5ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ለህትመት 5000/አምስት ሺህ ብር እና ለዘመናዊ ሽንት ቤት ግንባታ 10,000/ አስር ሺህ ብር) በመሀል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6ኛ. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና አስር ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በመሀል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ማስያዝ እና መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. በእያንዳንዱ ህትመቶች እና የዘመናዊ ሽንት ቤት ግንባታ ስራዎች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክክል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦርጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማ እና ማህተም አድራሻ ተጽፎበት ለህትመት ስራው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 1፡30 ድረስ በስራ ሰአት ከጨረታ ሰነዱን ከመሀል ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመግዛት በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት እና እንዲሁም ለመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ዘመናዊ ሽንት ቤት ግንባታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ2 ቀን ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 1፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዢ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመምጣት ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመግዛት በ22ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሉ ስራአስኪያጅ ቢሮ ይከፈታል፡፡

9ኛ. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡

10ኛ. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓላት፣ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

11ኛ. የሚገነባው ዘመናዊ ሽንት ቤት ሙሉ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች በአሸናፊው የሚቀርቡ የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡

12ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13ኛ. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 6 85 00 85 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ ምንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል

Address

Bahirdar, Ethiopia Kebele 14, Chulfit Building, 4TH FLOOR, ROOM NUMBER 403
Bahir Dar

Telephone

+251930296525

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ARCCA - Amhara Region Construction Contractors Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ARCCA - Amhara Region Construction Contractors Association:

Share