የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማኅበር-ዐክሥመማ- Amhara Unemployed Engineers Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማኅበር-ዐክሥመማ- Amhara Unemployed Engineers Association

የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማኅበር-ዐክሥመማ- Amhara Unemployed Engineers Association ይህ ገጽ በምህንድስና ተመርቀው ወደስራ ያልገቡና በተቀጠሩበት ስራ ተመጣጣኝ ክፍያ ያላገኙ መሃንዲሶች ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ልሳን ነው።

09/11/2025

መማር ውግዘት የሆነባትን ሀገር መሃይምነት ሲኦል እንዲሆን አናደርጋታለን።

Yes we can did it!

14/10/2025

We need justice???
17 years of education out of use!

14/10/2025
best of the day!
01/11/2024

best of the day!

ቦንድ ምንድን ነው?ቦንድ ማለት ግለሰቦች ለተወሰነ ጊዜ በተወሰነ የወለድ ተመን ለመንግስት ወይም ለኩባንያ /ድርጅቶች/ ገንዘብ የሚያበድሩበት ቋሚ ገቢ ያለው መሳሪያ እና የኢንቨስትመንት ዓይነ...
17/08/2024

ቦንድ ምንድን ነው?
ቦንድ ማለት ግለሰቦች ለተወሰነ ጊዜ በተወሰነ የወለድ ተመን ለመንግስት ወይም ለኩባንያ /ድርጅቶች/ ገንዘብ የሚያበድሩበት ቋሚ ገቢ ያለው መሳሪያ እና የኢንቨስትመንት ዓይነት ሲሆን ማህበሩ ለግለሰቦች ማስያዣ ወይም መተማመኛ የቦንድ ሠርተፍኬት አዘጋጅቶ ከዋናው የፊት ዋጋ በተጨማሪ ወለድ የሚከፍልበት የብድር ሥርዓት ነው ።
ቦንዶች በድርጅቶችና በመንግስታት ፕሮጀክቶችን እና ስራዎችን በገንዘብ ለመደገፍ በማሰብ የቦንድ ባለቤቶች የቦንድ ሻጩ አበዳሪዎች ናቸው። ድርጅቶችና መንግስታት ብዙውን ጊዜ ንግዳቸውን ለማሳደግ፣ ንብረት እና መሳሪያ ለመግዛት፣ ትርፋማ ፕሮጀክቶችን ለመስራት፣ ለምርምር እና ልማት ወይም ሰራተኞችን ለመቅጠር በቦንድ መልክ ገንዘብ ከግለሰቦች ይበደራሉ ።
በዓለማችን ውስጥ በጣም በርካታ የግል ድርጅቶችና ሉዓላዊ መንግስታት(አሜሪካ 39% ፣ ቻይና 16%፣ ጃፓን 8%፣ ፈረንሳይ - 3%) የቦንድ ሽያጭ ሥርዓትን በመከተል ለመተግበር ያሰቧችውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ስኬታማ ማድረግ ችለዋል ፡፡
በሀገራችንም የቦንድ ሽያጭ ብዙ ሰፊ ታሪክ ያለውና የተለመደ ባይሆንም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ህዝቡንና ባለሃብቱን በንቃት በማሳተፍ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማው በማድረግ እየተተገበረ ይገኛል ፡፡
የቦንድ ሽያጭ ማካሄድ ለማህበራችን ዐክሥመማ አስፈላጊ የሚሆንበት ዓብይ ምክንያት የማህበሩን የፋይናስ አቅም ከማነቃቃቱም በተጨማሪ አባላትን በንቃት በማሳተፍ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ እና ከቦንድ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ አጭነታቸው ለተረጋገጡ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ ነው ፡፡
ቦንዱ የራሱ የሆነ የአሻሻጥ ሥርዓት ያለው እና ህጋዊነትን የተላበሰ ተጣቂነትና ኃላፊነትን በተላበሰ አኳኋን የመነሻ እና መድረሻ ሁኔታዎች አስቀድመው ተወሰነው ተግባራዊ የሚደረግ አሰራር ነው ፡፡
ቦንድን ከአክሲዮን ምን ይለየዋል
1. ቦንድ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለአንድ በህግ ሰውነት ላገኘ ድርጅት ወይም ተቋም በውል የሚሰጥ ብድር /ትውስት/ ሲሆን አክሲዮን ግን በድርጅቱ ውስጥ ባወጣነው መጠን ባለድርሻ /ባለሃብት/ የምንሆንበት አሰራር ነው ፡፡
2. ቦንድ ለገዙት ሰዎች /ድርጅቶች/ ዋና ገንዘቡ የብድር ወለድ ጨምሮ ወይም ሳይጨምር (እንደውሉ ሁኔታ) የሚመለስላቸው ሲሆን አክሲዮን ግን
3. ቦንድ አሰራር ውስጥ ትርፉ የድርጅቱን ፕሮጀክት በጋራ ሰርቶ ያበደሩትን ገንዘብ ማስመለስና ድርጅቱን ማገዝ ሲሆን አክሲዮን ውስጥ ግን በድርሻው ልክ የድርጅቱን ትርፍና ኪሳራ ይጋራሉ ፡፡
4. ቦንድ የመመለሻ ቀነ ገደቡ ሲያልቅ የዋጣነው ዋና ገንዘብ ሙሉ በሙሉ (ትርፍ ጨምሮ) ለመመለስ ቦንድ ሻጭ ድርጅቱን የሚያስገድድ ሲሆን አክሲዮን ድርጅቱ ካለፈረሰ በስተቀር ዋና ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ የለበትም ፡፡
5. አክሲዮን የንግድ ተግባር ሲሆን ቦንድ ሽያጭ የንግድ ስራ አይደለም ፡፡
6. ሌሎችም ልዩነቶች አሏቸው ።
/ከማህበሩ የቦንድ ሽያጭ ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ የተወሰደ//
የማህበሩ ቦንድ ሽያጭ ኮሚቴ፣ ባህር ዳር።

እናመሰግናለን !የቦንድ ሽያጭ ማስታወቂያውን ጥሪ ተከትሎ የቦንድ ግዥ የፈጸሙትን አባላት መረጃ እናደርሳለን።1. አበባው ገድፍ = 1,500 ብር2. ዘመነ ብሩ = 1,500 ብር ቦንድ ገዝተው ...
16/08/2024

እናመሰግናለን !
የቦንድ ሽያጭ ማስታወቂያውን ጥሪ ተከትሎ የቦንድ ግዥ የፈጸሙትን አባላት መረጃ እናደርሳለን።
1. አበባው ገድፍ = 1,500 ብር
2. ዘመነ ብሩ = 1,500 ብር ቦንድ ገዝተው ሰርተፍኬታቸውን ወስደዋል።
የቦንድ ሽያጩ ዓላማ የዐክሥመማ ቢዝነስ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ሙሉ በሙሉ የሚውል ነው ።
የቦንዶችን ለመግዛት CBE 1000298424103 የማህበሩ አካውንት ተጠቀሙ።
"እኛ መሃንዲሶች ሁሌም መፍትሔ አለን!"
//የማህበሩ የቦንድ ሽያጭ ኮሚቴ//

ቀን፡ 09/12/2016 ዓ.ምለሁሉም የማህበራችን አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቦንድ ሽያጭ በይፋ ተጀምሯል!ማህበራችን የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃ...
15/08/2024

ቀን፡ 09/12/2016 ዓ.ም
ለሁሉም የማህበራችን አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቦንድ ሽያጭ በይፋ ተጀምሯል!

ማህበራችን የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማህበር /ዐክሥመማ / የተለያዩ የቢዝነስ ፕሮጀክቶችን ማስፈፀሚያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን (በቦንድ ሽያጭ ማስፈጸሚያ መመሪያው መሠረት) ለማስጀመር በቀን 14/11/2016 ዓ.ም በነበረው ልዩ የምክክር ጉባኤ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ የቦንድ ሽያጬ ኮሚቴ የተዋቀረ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም ሁሉም የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በቦንድ ሽያጭ መመሪያው መሠረት የቢዝነስ ፕሮጀክቶቹ ላይ ከ09-30/12/2016 ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ከ500-10,000 ብር ቦንዶችን በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000298424103 በመግዛት ደረሰኛችሁን ወደ ጽ/ቤት በማምጣትና በስማችሁ የግዥ ሠርተፍኬት በማሰራት ማህበራችንና እራሳችሁን እንድትጠቅሙና እንድትጠቀሙ እያሳወቅን ጥያቄና ማብራሪያዎች ለሚፈልጉ 0967146114 /0913401497/0931548985 ደውላችሁ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
የማህበሩ ቦንድ ሽያጭ ኮሚቴ ፤ ባህርዳር ።

ለልባሞች ወደ ሀገረ  #ሲዊዲን  የስራ ዕድል ስምሪት እየተመቻቸ ነው!!ብዙዎች እንደቀልድ ያልተጠቀሙበት የሃገር ወስጥና ውጭ ሥራ ዕድል ቀድመው በትኩረት ለተመዘገቡት ዕድሉን እያመቻቸላቸው ነ...
12/08/2024

ለልባሞች ወደ ሀገረ #ሲዊዲን የስራ ዕድል ስምሪት እየተመቻቸ ነው!!
ብዙዎች እንደቀልድ ያልተጠቀሙበት የሃገር ወስጥና ውጭ ሥራ ዕድል ቀድመው በትኩረት ለተመዘገቡት ዕድሉን እያመቻቸላቸው ነው።
አሁንም ቀነ ገደቡ ከማለቁ በፊት በonline ለመመዝገብ ለምትፈልጉ ሁሉ አመዘጋገቡን የሚከተለውን መስፈንጠሪያ (link) https://lmis.gov.et በመጫን መመዝገብ ትችላላችሁ።

የበይነ መረብ ውይይት ጥሪ !ማህበራችን ዐክሥመማ ከአባላት ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የብነ መረብ ውይይቶች ማድረግ ይፈልጋል። በመሆኑም በሚከተሉት የማህበሩ የመወያያ በይነ መረብ ማስፈን...
09/08/2024

የበይነ መረብ ውይይት ጥሪ !
ማህበራችን ዐክሥመማ ከአባላት ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የብነ መረብ ውይይቶች ማድረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም በሚከተሉት የማህበሩ የመወያያ በይነ መረብ ማስፈንጠሪያዎች ብቻ በመግባት ሀሳብ አስተያዬት እንዲሰጡ፣ ጥያቄዎች እንዲያቀርቡ፣ መረጃዎችን እንዲያገኙ፣ ለሌሎችም እንድታጋሩ እና እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል።
(የመወያያ አጀንዳዎችንና አወያዮችን ይዘን እንመጣለን፤
እርስዎም እንድንወያይበት የሚፈልጉት አጀንዳ ካለ ቀድመው ያስይዙን፣ በቅርብ ቀን ይጠብቁን!)
"እኛ መሃንዲሶች ሁሌም መፍትሔ አለን!"
1. የፌስቡክ ፔጃችን፡https://www.facebook.com/ARUEA2012
2. የቴሌግራም ቻናላችን፡
https://t.me/Amhaunemployedengassochannel
3. የቴሌግራም ግሩፖቻችን፡
https://t.me/amharaunemployedengineer
https://t.me/arueagroupdiscusion
4. ስልክ ቁጥሮች፡
+251918584573 = ፕሬዝዳንት
+25193 154 8985 = ጽ/ቤት ኃላፊ
+251588223434 = የጽ/ቤቱ ቢሮ ስልክ

የዐክሥመማ ፕርጀክቶች ማስፈጸሚያ ቦንድ ሽያጭ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል!!!ገንዘቡን በቦንድ ሽያጭ ለማሰባሰብና ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡እርስዎስ ?!“እኛ መ...
08/08/2024

የዐክሥመማ ፕርጀክቶች ማስፈጸሚያ ቦንድ ሽያጭ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል!!!
ገንዘቡን በቦንድ ሽያጭ ለማሰባሰብና ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡
እርስዎስ ?!
“እኛ መሃንዲሶች ሁሌም መፍትሔ አለን!”

በየአካባቢያችሁ በስራና ስልጠና 1ለ5 ተደራጅታችሁ እስካሁን ምንም ዓይነት ፕሮጀክቶችን ያልሰራችሁና ህስካሁን ያልተደራጃችሁ አባላት ብቻ በተጠቀሱት ቀናትና ፎርም መሠረት ተመዘጋባችሁ በየአካባ...
08/08/2024

በየአካባቢያችሁ በስራና ስልጠና 1ለ5 ተደራጅታችሁ እስካሁን ምንም ዓይነት ፕሮጀክቶችን ያልሰራችሁና ህስካሁን ያልተደራጃችሁ አባላት ብቻ በተጠቀሱት ቀናትና ፎርም መሠረት ተመዘጋባችሁ በየአካባቢያችሁ ለሚገኙ የማህበሩ ቅርንጫፎች እንድታሳውቁ እናሳስባለን።

Address

Abbaymado, Kebele 11
Bahir Dar

Telephone

+251915258181

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማኅበር-ዐክሥመማ- Amhara Unemployed Engineers Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የዐማራ ክልል ሥራ አጥ መሃንዲሶች ማኅበር-ዐክሥመማ- Amhara Unemployed Engineers Association:

Share