Sidama Development Association-SDA

Sidama Development Association-SDA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidama Development Association-SDA, Community Service, Bahil-Adarash sub-city by the Hawassa post office, Awassa.

Sidama Development Association (SDA) is an independent, non-political, non-religious, not-for-profit, non-governmental member-based organization established in July 1993 Registered and licensed by FDRE Civil Society Organizations Authority.

ትክክለኛ የግብርና ገበያ መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ በመጠቀም ውጤታማነት ማሳደግ እንደሚቻል ተገልፀ።     **"""""""""""""""**"የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን ሰኔ 9/2018 ዓ.ም...
16/06/2026

ትክክለኛ የግብርና ገበያ መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ በመጠቀም ውጤታማነት ማሳደግ እንደሚቻል ተገልፀ።
**"""""""""""""""**"
የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ሰኔ 9/2018 ዓ.ም ሀዋሳ

ይህ የተገለፀው የሲዳማ ልማት ማህበር ከሲ/ብ/ክ/መንግሥት ግብርና ቢሮ ISVCD ፕሮጀክት ጋር ትብብር በማድረግ በልማት ማህበሩ በተቋቋመው AgriCONNECT Hub ሥር የበለፀገውን AgriDiko ዌብሳይት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በአስር ወረዳዎች ለተሰማሩ የግብርና ገበያ መረጃ ሰብሳቢዎች የሚሰበስቡትን መረጃ ለዌብሳይቱ ግብዓት እንዲያውሉ ለማስቻል በተዘጋጀው ስልጠና ላይ ነው።
ስልጠናውን የልማት ማህበሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ያለው ተከስተ መልዕክት አስተላልፈው ያስጀመሩት ሲሆን የልማት ማህበሩ ማኔጅመንት አባላት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=1

የሲዳማ ልማት ማህበር ማኔጅመንት በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ አለም አቀፍ እና ሀገር በቀል አጋር አካላት ጋር ለወደፊት በትብብር ሊሰራ በሚቻልባቹው ጉዳዮች እና የተጀመሩ ፕሮግራሞች ቀጣይ...
11/06/2026

የሲዳማ ልማት ማህበር ማኔጅመንት በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ አለም አቀፍ እና ሀገር በቀል አጋር አካላት ጋር ለወደፊት በትብብር ሊሰራ በሚቻልባቹው ጉዳዮች እና የተጀመሩ ፕሮግራሞች ቀጣይነት ላይ ለአንድ ሳምንት የቆየ ውጤታማ Patnership and Networking) አደረገ።

የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ሰኔ/2018 ዓ.ም

ህብረተሰቡን እና በጤናው ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን ያጣመረ የጤና አገልግሎት አስጣጥ ይበልጥ ውጤታማ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ *******"""""""""""********የሲዳማ ልማት ማህበር ...
05/06/2026

ህብረተሰቡን እና በጤናው ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን ያጣመረ የጤና አገልግሎት አስጣጥ ይበልጥ ውጤታማ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
*******"""""""""""********
የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ሀዋሳ

ይህ የተገለፀው የሲዳማ ልማት ማህበር ከ (JSI IPHCSD Project) ጋር በመተባበር በአለታ ወንዶ ወረዳ ህብረተሰብንና የጤና ድርጅቶችን ያጣመረ ጥራት ማሻሻያ (Community combined facility quality improvement, (CCFQI) በተመለከተ በአለታ ወንዶ ከተማ በተዘጋጀው የአፈፃጸም ግምገማ እና የመማማሪያ መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻ ልማት ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የልማት ሥራዎች የሰራ መሆኑንና በዚህ ጊዜ በአምስት አንኳር ጉዳዮች ማለትም በዘለቂ የኑሮ መሰረቶችና ግብርና፤ በትምህርት እና ጤና፤ በሴቶችና ወጣቶች አቅም ማጎልበትና የሕፃናት ጥበቃ በመሰረተ ልማት እና ንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም በሰብአዊ ድጋፎች ላይ በተጠናከረ መልኩ እየሰራ መሆኑንና የጤናውም ሥራ የዚሁ የትኩረት አቅጣጫ አንዱ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ በአሁን ጊዜ በስድስት ወረዳዎች እየተሰራ ይገኛል ብለው ህብረተሰብንና የጤና ድርጅቶችን ባጣመረ መልኩ እየተሰራ ያለው ጥራት ማሻሻያ ሥራ ዉጤት ላይ ባተኮረ መልኩ እንደሚገመገም እና ክፍተቶችን በመለየት አስቸኳይ ማስተካከያ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበው ይህን ስራ እንድንሰራ ከፍተኛ እገዛ እያደረገልን የምገኘዉን አጋር ድርጅት JSI አመስግነው ተሳታፍዎች መማማሪያ መድረኩን እንደመልካም አጋጣሚ እንዲጠቀሙና የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ሥራ አስፈፃሚዋ በመልዕክታቸው ለልማት ማህበሩ አባላት የጀርባ አጥንት በመሆናቸው ሁሉም አባል በመሆን የበኩሉን እንዲወጣ ለተሳታፊዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማርም አቶ ዘማች ከበደ የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፍ ፤ እና የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የክልሉ በበበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይረክቶረት ስር የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ክፍል ባለሙያ አቶ ተገኝ ዋጊሶ በበኩላቸዉ፤ የሲዳማ ልማት ማህበር ከJSI IPHCSD & SSD Project ጋር በመተባበር እየተገበረ የሚገኘው የጤና ፕሮጀክቶች በአለታ ወንዶ ወረዳ እንዲሁም በሲዳማ ክልል በስድስት ወረዳዎች እያካናወነ ስላለዉ ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ከፍተኛ ዕዉቅና በመስጠት አመስግነዋል፡፡

በተጨማርም በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል JSI አሰተባባር ወ/ሮ ምንትዋብ ዘነበ የተገኙ ሲሆን ህብረተሰብንና የጤና ድርጅቶችን ያጣመረ ጥራት ማሻሻያ (Community combined facility quality improvement, (CCFQI) በተመለከተ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ችግር ፈች ዉይይት በማድረግ በተለዩ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር የመማሪያ መድረኩ በነገዉም ቀን የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ የቀኑ የመማሪያ መድረክ ተጠናቋል፡፡

!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=1

Yirgaalamete Gidaaawu Iibballichonna Gangalatu Mereershi gaabiyonete loosi noo deerra. የይርጋአለም ጊዳቦ ፍል ውሃና  መዝናኛ ማዕከል የጋቢ...
30/05/2026

Yirgaalamete Gidaaawu Iibballichonna Gangalatu Mereershi gaabiyonete loosi noo deerra.

የይርጋአለም ጊዳቦ ፍል ውሃና መዝናኛ ማዕከል የጋቢዎን ሥራ ያለበት ደረጃ.

Sidaamu Latishshu Maamari Kominikeeshine onkolessa 22/ 2018 M. D Hawaasa:

የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሸን ግንቦት 22/2018 ዓ.ም ሀዋሳ:

በራስ አገዝ በመርፌ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ (DMPA-SC-SI) በተመለከተ የአፈፃጸም ግምገማ  እና የመማማሪያ መድረክ በይርጋአለም  ከተማ  ተካሄደ።የልማት ማህበሩ የ(IPHCSD & SSD...
29/05/2026

በራስ አገዝ በመርፌ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ (DMPA-SC-SI) በተመለከተ የአፈፃጸም ግምገማ እና የመማማሪያ መድረክ በይርጋአለም ከተማ ተካሄደ።

የልማት ማህበሩ የ(IPHCSD & SSD) ፕሮጀክቶቸ አስተባባሪ አቶ ተረፈ ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት ልማት ማህበሩ በስድስት ወረዳዎች ላይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ያለ ሲሆን ከJSI ጋር በመተባበር በዳሌ ወረዳ የራስ አገዝ በመርፌ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ (DMPA-SC-SI) እየተሰራ ያለዉ ስራ እንደሚገመገም እና ክፍተቶችን ለይቶ የድርጊት መርሃ-ግብር እንደሚዘጋጅ ገልጸዉ ተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል አቶ መለሰ አህመድ የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የጤና ዘርፍ ዳይረክተር እና የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የክልሉ በእናቶች እና ህጻናት ዳይረክቶሬት ስር የቤተሰብ እና የአፍላ ወጣቶች ስነ-ተዋልዶ አስተባባሪ አቶ አብርሃም አናን በበኩላቸዉ፤ በክልሉ የቤተሰብ ዕቅድ መከላከያ መድኃንቶችን በተመለከተ የክልሉ ጤና ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እና እደገፈ እንዳለ እንዲሁም በአቅም ግንባታ፤ በግብዓት አቅርቦት፤ እና ድጋፍና ክትትል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም ድጋፉና ክትትሉ እንደምቀጥል ገልጸዋል፡፡

በተጨማርም በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል JSI አሰተባባሪ ወ/ሮ ምንትዋብ ዘነበ የተገኙ ሲሆን የራስ አገዝ በመርፌ የሚሰጥ የወሊድ መከላከያ (DMPA-SC-SI) በተመለከተ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከJSI ፤ከልማት ማህበሩ ከክልሉ ጤና ቢሮ፣ ከዞን እና ወረዳ ጤና ጽ/ቤት፣ የጤና አጤባበቅ ጣብያዎች እና የጤና ኤክስቴንሽ ሠራተኞች በተገኙበት የዳሌ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ላማሎ ሶንባሎ ባደረጉት ንግግር የተደረገዉ ዉይይት ዉጤታማ መሆኑን በመግለጽ ፤ በቀጣይ ክፍተት በታየባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዉ፤ የሲዳማ ልማት ማህበር ከJSI ጋር በመተባበር እያደረገ ስላለዉ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በመጨረሻም ችግር ፈች ዉይይት በማድረግ በተለዩ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የድርጊት መርሃ-ግብር በማዘጋጀት የመማማሪያ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=1

የሲዳማ ልማት ማህበር በጤናው ዘርፍ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ሥራ አካል የሆነው የክትባት መርሃ-ግብር በተመለከተ የአፈፃጸም ግምገማ እና የክትባት የዕቅድ ስልት ግንዛቤ (EPI-consulta...
27/05/2026

የሲዳማ ልማት ማህበር በጤናው ዘርፍ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ሥራ አካል የሆነው የክትባት መርሃ-ግብር በተመለከተ የአፈፃጸም ግምገማ እና የክትባት የዕቅድ ስልት ግንዛቤ (EPI-consultative meeting) የመማማሪያ መድረክ በደራራ ወረዳ ተካሄደ።

የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም ሀዋሳ

ልማት ማህበሩ JSI ከተበለ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በሚተገብረው ፕሮጀክት አማካኝነት በተዘጋጀው የመማማሪያ መድረክ ላይ የተገኙት የሲዳማ ልማት ማህበር የሁለቱ ፕሮጀክቶቸ (IPHCSD & SSD project coordinator) አስተባባሪ አቶ ተረፈ ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት ልማት ማህበሩ በስድስት ወረዳዎች ላይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝና በደራራ ወረዳ የክትባት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሻሻል በአግልግሎት አሰጣጥ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት (SSD project) እየተሰራ ያለዉ ስራ አካል የሆነዉን የክትባት መርሃ-ግብር አፈጻፀም እንደሚገመገም እና ክፍተቶች ካሉ ለይቶ የድርጊት መርሃ-ግብር እንደሚዘጋጅ ገልጸዉ ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የክትባት መርሃ-ግብር አስተባባሪ አቶ አድማሱ አርሲቻ በበኩላቸዉ፤ በክልሉ ክትባትን በተመለከተ የክልሉ ጤና ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየደገፈ እንዳለ እና በአቅም ግንባታ፤ በግብዓት አቅርቦት እና ድጋፍና ክትትል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም ድጋፉ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ተወካይ፣ የማከላዊ ሲዳማ ዞን የጤናዉ ዘርፍ አሰተባባሪ እና ማናጅመንት፣ የዳራራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ማናጅመንት፣ የጤና አጠባበቅ ጣብያ ኃላፊዎች እና ማናጅመንት እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የማከላዊ ሲዳማ ዞን የጤናዉ ዘርፍ አሰተባባሪ አቶ መለሰ አህመድ እና የዳራራ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ማርማራ የየበኩላቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ችግር ፈች ዉይይት በማድረግ በተለዩ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የድርጊት መርሃ-ግብር በማዘጋጀት የመማማሪያ መድረክ ተጠናቋል፡፡
!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=10

የሲዳማ ልማት ማህበር መላውን የእስልምና እምነት ተከታዮች  እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል-ዓድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የስኬት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እ...
27/05/2026

የሲዳማ ልማት ማህበር መላውን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል-ዓድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የስኬት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የመትረፍረፍ እንዲሆን ይመኛል።
************""""""""""""""*************
የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን ግንቦት 19/2018 ዓ.ም ሀዋሳ
ዒድ ሙባረክ!.

JSI ኢትዮጵያ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመቀናጅት እያከናወነ ለሚገኛቸው የጤና ፕሮጀክት ከጤና ጣቢያ ወደ ጤና ኬላ ግብዓት ለማድረስ እና ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ የሚረዱ ሁለት ሞተር ሳይ...
16/05/2026

JSI ኢትዮጵያ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመቀናጅት እያከናወነ ለሚገኛቸው የጤና ፕሮጀክት ከጤና ጣቢያ ወደ ጤና ኬላ ግብዓት ለማድረስ እና ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ የሚረዱ ሁለት ሞተር ሳይክሎችን ለክልሉ ጤና ቢሮ አስረከበ::
***""""""""""""""""******
የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 8/2018 ሀዋሳ

ድጋፉ የተደረገው በወንዶገነት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሥር ለሚገኙ ሁለት ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች (አሩማ እና ባቦ ጮሮሮ ) በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ፕሮጀክት (strengthen service delivery project (SSD) ነው።

በርክክቡ ወቅት የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ እና የJSI የሲዳማ ክልል IPHCSD እና SSD አስተባባሪ ወ/ሮ ምንትዋብ ዘነበ፣ የሲዳማ ልማት ማህበር ም/ስራስካጅ አቶ ያለዉ ተከስተ እንዲሁም የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የማኔጅመነት አባላት እና የሁለቱም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በርክብክቡ ወቅት የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት JSI ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመቀናጅት በክልሉ በስድስት ወረዳዎች ላይ የእናቶችን፤ የህጻናትን እና የጨቅላ ህጻናትን ሞትና ህመም ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየራ ከመሆኑም በላይ የግብዓት መቆራረጥን ለማስለጥ በሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ሁለት የሞተር ሳይክሎች ድጋፍ በጣም አስፈላጊ መሆናቸዉን ገልጽዉ፣ ግብዐትን ከጤና ጣብያ ወደ ጤና ኬላ ግብዕት ከማድረስ በተጨማሪ ከጤና ኬላ ወደ ክትባት ጣብያዎቻችን እና የዉሎ ገብ ስራዎችን ለማሳለጥ ከፍተኛ አሰተዋዖ እንደሚኖራቸዉ በመግለጽ በአግባቡና በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲሰራ መመርያ ሰተዋል፡፡
የJSI የክልሉ ኘሮግራም አስተባባሪ ወ/ሮ ምንትዋብ ዘነበ በበኩላቸዉ JSI በክልሉ ዉስጥ ብዙ ተግባራትን እየስራ መሆኑን ገልጸዉ በተለይም የእናቶችን፤ የህጻናትን እና የጨቅላ ህጻናትን ሞትና ህመም ለመቀነስ፤ በጤና ኬላ አእና በማህበረስብ ውስጥ አግልግሎቱን ተድራሽ ልማደረግ ከፍተኛ አሰተዋጾ እንዳለዉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማርም የልማት ማህበሩ ም/ሥራ አሰፈፃሚ አቶ ያለዉ ተከስተ የልማት ማህበሩ ከJSI ጋር ለመተግበር እንዲያመች አንድ በክልል ደረጃ የፕሮጅከቶች አሰተባባሪ እና አምስት ወረዳ ኦፊሰሮችን በመቅጠር ስራዉን እየሰራ ሲሆን የዛሬዉ ድጋፍ ግባትን ለማሳለጥ ከJSI የተገኘ ተጨማር ድጋፍ መሆኑን በመግለፅ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ መሰል ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

!
!

~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=10

የትውውቅ፣ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና ለዲጅታል የግብርና መረጃ ማሳለጫ የሚያገለግል 31 የዘመናዊ ስልኮች ከአመታዊ የኢንተርኔትና የመልዕክት ጥቅል ጋር  የማስራጨት እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበ...
13/05/2026

የትውውቅ፣ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ እና ለዲጅታል የግብርና መረጃ ማሳለጫ የሚያገለግል 31 የዘመናዊ ስልኮች ከአመታዊ የኢንተርኔትና የመልዕክት ጥቅል ጋር የማስራጨት እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር ተካሄደ::
**********""""""""""""""**********
የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 5/2018 ይርጋአለም

የሲዳማ ልማት ማህበር ከሲ/ብ/ክ/መንግሥት ግብርና ቢሮ ISVCD ፕሮጀክት ጋር የእስትራቴጅክ አጋርነት ሥምምነት መነሻ በማድረግ በልማት ማህበሩ በተቋቋመው AgriCONNECT Hub ሥር የበለፀገውን AgriDiko ዌብሳይት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ለመፍጠርና ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ ያለመ መርሃ-ግብር ነው።

በመድረኩ ተገኝትው መልዕክት በማስተላለፍ ስልጠናውን ያስጀመሩት የልማት ማህበሩ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ያለው ተከስተ በመልዕክታቸው ልማት ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በግብርናው ዘርፉ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱን ገልፀው የዛሬው መርሃ-ግብር ወቅቱ የዲጅታላይዜሽን መሆኑን በመረዳት በግብርናው መስክ የተሰማሩ አካላት ወቅታዊ የግብርና ገበያ መረጃን ስትክክለኛ ምንጮች እንዲያገኙ በማስቻል በዘርፉ ከመረጃ እጥረት የተነሳ የሚያጋጥሙ ዘርፉ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስል ሥርዓት በመዘርጋት የገበያ መረጃ ሰብሳቢዎችን በመቅጠርና በማስልጣን እንዲሁም መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዳ Smart Phone በመስጠት በ10 ወረዳዎች የሥራ ስምሪት ተሰቷል::
በዛሬው እለት ሁሉም የሚመለከተው አካል በተገኘበት 2ዐ ለሚሆኑ መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት የመረጃ ግብይቶች እንዲመግቡ የሚያስችላቸውን Smart Phone በልማት ማህበሩ የሚበረከትላቸው ሲሆን ለወደፊት በቅንጅት ለመስራት የሚያችልም ነው ብለዋል::
ከሲብ/ክ/መንግሥት እርሻና ተፈ/ሀ/ል/ቢሮ ከአካታችና ቀጣይ የግብርና እሴት ሰንሰለት ልማት /ISVCD/ ፕሮጀክት ማኔጀር አቶ ምትኬ ሙሉጌታ ለተሳታፊዎች በአካታችና ቀጣይ የግብርና እሴት ሰንሰለት ልማት /Inclusive and Sustainable Value chain Development/ ፕሮጀክት እና በግብርና ገበያ መረጃ ላይ ሰፊ ግንዛቤ የፈጠሩ ሲሆን የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ላይ ግብርናን ከተለመደው አምርቶ ገበያ ከሚፈለግበት አስቀድሞ ወስኖ እና ሸጦ ወደማምረት በዚህም አርሶአደሮችም ሆኑ የእሴት ሰንሰለት ተዋናዮች ሁሉ በተገቢው ተጠቃሚ ሊሆኑ ስለሚችሉበት እና በቅንጅት መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ግንዛቤ አስጨብጠዋል::

የሲዳማ ልማት ማህበሩ የዕቅድ ክትትል ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ ግሩም ሹኔቴ ልማት ማህበሩ እያከናወነ ስለሚገኘው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ከመርሃ- ግብሩ ተሳታፊዎች አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አላማ እና የሚጠበቁ ውጤቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።

የልማት ማህበሩ የIG Department ኃላፊ በሌላ በኩል በሲዳማ ልማት ማህበር በተቋቋመው AgriCONNECT Hub ሥር የበለፀገውን AgriDiko ዌብሳይት ላይ ግብአት ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ድህረ ገፁ ዘመኑን የዋጀና የግብርና መረጃ ሥርዓትን የሚያዘምን እንደሆነ ገልፀው የሥርዓቱን ተደራሸነት ለማስፋት ከተጀመሩ ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሆነ እንቅስቃሴ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨረሻም የውይይት ከተሳታፊዎች ሀሳብ፤ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረኩ ምላሽ በተሰጠ በኋላ ለመሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራት እና ለመረጃ ስብሳቢ ኦፊሰሮች smart phone With Annual internate packege በመስጠት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል::

!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=10

በጤናው ዘርፍ እየተተገበረ የሚገኘውን ፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ የክልሉ ጤና ቢሮ እና ገንዘብ ቢሮ በተገኙበት ተካሂዷል። የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽንግንቦት 4/2018 ዓ.ም ሀዋሳ ፕሮጀ...
12/05/2026

በጤናው ዘርፍ እየተተገበረ የሚገኘውን ፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ የክልሉ ጤና ቢሮ እና ገንዘብ ቢሮ በተገኙበት ተካሂዷል።

የሲዳማ ልማት ማህበር ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 4/2018 ዓ.ም ሀዋሳ

ፕሮጀክቱ በዋናነት የሲዳማ ልማት ማህበር JSI ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በስድስት ወረዳዎች በሁለት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማለትም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ማሻሻያ (Improve primary health care service delivery project, IPHCSD) እና የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማጎልበት (strengthen service delivery, SSD) ላይ የሰራ የቆየ ሲሆን የልማት ማህበሩ የሁለቱም ፕሮጀክቶች የክልል አስተባባሪ አቶ ተረፈ ሙሉጌታ በፕሮጀክቱ በሲዳማ ክልል ባለፉት ሶስት አመታትና ከዚያ በላይ የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማጣቀስ እስካለፈው አመት 2025 ድረስ የተከናዎኑ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ፣ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ከክልሉ ገንዘብ ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ዴስክ ኃላፊ አቶ ሳሙአል ተካ ብሎም የልማት ማህበሩ ማኔጅመንት አባላት እና የሁሉም ወረዳ የፕሮጀክት ኦፊሰሮች ተገኝተዋል፡፡
የግምገማ መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልከዕክት ያስጀመሩት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻ በመልዕክታቸው ልማት ማህበሩ በአምስት ቴማቲክ አቅጣጫዎች እያከናወናቸው ከሚገኙ ሥራዎች ውስጥ አንዱ የጤናው ዘርፍ ሲሆን JSI ከጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በሀገር አቀፍ ደረጃ በገባው የፕሮጀክት ስምምነት መነሻነት በሲዳማ ክልል በIPHCSD ፕሮጀክት በበንሳ ወረዳ ተጀምሮ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ SSD ፕሮጀክት ተጨምሮ በሁለቱም ፕሮጀክቶች በስድስት ወረዳዎች ውስጥ የሚታይ ለውጥ ማምጣት የተቻለ ሲሆን የተመዘገበውን ውጤት ተከትሎ C-RMNCH የተባለ ሶስተኛ ፕሮጀክት በተለዩ ወረዳዎች ለመጀመር ዝግጅቱ ተጠናቆ ስምምነት መፈራረም ብቻ ቀርቶናል ብለው የዛሬው የግምገማ መድረክ የሥራው ባለቤቶች ባሉበት ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በመለየት ለወደፊት በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የውይይት መድረኩን የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ እና የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እየመሩ ከተሳታፊዎች ሀሳብ፤ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረኩ ምላሽና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
!
!


~Follow us on~
🌎website:https://sida.org.et/
🌎 telegram:https://t.me/+l9A1rzxwsCgzMTQ0
🌎 YouTube:https://www.youtube.com/
🌎 TikTok:-https://www.tiktok.com/?_t=8n5NdDvxjvh&_r=10

Address

Bahil-Adarash Sub-city By The Hawassa Post Office
Awassa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+251916586048

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Development Association-SDA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidama Development Association-SDA:

Share