15/08/2026
Kebede Sele Dafursa ❤🥰❣️👏
የዞናችን ምክትል አስተዳዳሪና የኢኮኖሚያዊ መምሪያ ኃላፊ የተከበሩ ከበደ ሴለ ዳፉርሳ በአመራር ሚናቸው የፋይናንስ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በመርህ ደረጃ በመከተል ለዞኑ ልማት አሻራቸውን እያኖሩ ያሉ አመራር ናቸው።
ከቤን ልዩ የሚያደርጋቸው ነገር በእምነታቸውና በሃይማኖታቸው ለሚያምኑት እሴት ቅድሚያ መስጠታቸውም ከሚገልፃቸው የግል እሴቶች አንዱ ነው። ነገር ግን አመራርን በግል ምርጫ ሳይሆን በሥራ፣ በውጤት፣ በግልፅነትና በተጠያቂነት መመዘን ይገባል።
በሌላ በኩል፣ ከዞኑ ሠራተኞች የሥራ ማስኬጃና የውሎ አበል ክፍያ በጀቱ በታዛቢነት የሚጠቀሙበት ጊዜ ስለመሆኑ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ በቸልታ ሊታዩ የሚገባቸው አይደሉም። እነዚህ ክፍተቶች በግልፅ ውይይት፣ በትብብርና በተቋማዊ አሠራር መፍትሔ ሊያገኙ ይገባል።
ስለዚህ ለሥራ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የዞኑ አስተዳዳሪ፣ አመራሩም ሆነ አስተዳደሩ ከሠራተኞች ጋር በመናበብ፣ በመስማትና በመፍታት መስራት ይገባቸዋል።
አንድን አመራር ብቻውን ነጥሎ በአሉባልታና በአሉታዊ ወሬ መተቸት መፍትሔ አይደለም። ችግሩን በማወቅ፣ በመነጋገርና በጋራ በመፍታት የተሻለ አሠራር መፍጠር ነው ትክክለኛው አቅጣጫ ሚሆነው።
አመራርን ስንደግፍ ችግርንም በግልፅ እንጠቁም። ችግርን ስንጠቁምም መፍትሔውን አብረን እንፈልግ። የሚያስፈልገን የግል ጥላቻ ሳይሆን የጋራ ሥራ፣ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና በውጤት ነው።
Ararso Kia Hankamo Jr.
#እወዳችኋለሁ ❣️👏