SRCA - South Region Contractors Association

SRCA - South Region Contractors Association ማህበሩ ለትርፍ ያልቆመ፣ ከፖለቲካ ወይም ከሀይማኖት ወይም ከ

09/01/2024

የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በከተማ ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች መካከል አንዱ የቄራ አገልግሎት ለሚያሰራው የከብት በረት የግንብና የእርድ ክፍል ጥገና ሥራ ግዥ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ተቋራጮች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ GC-6/ BC-6 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፡፡

2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የ2016 ዓ.ም የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤

4. የቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (cpo) ወይም Bid Bond በባንክ የተመሰከረውን 40,000 (አርባ ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 ( አስር) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብር 500 አምስት መቶ ከፍላችሁ ሰነድ በመውሰድ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡

7. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት ፋይ/ ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኮሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲከ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡

12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ [ 046-220-99-63/046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ ሀዋሳ

Second Round Electrical Instalation Training Workshop held on 01 to 05, Jan., 2024 at Hawassa Poly Technic College is st...
01/01/2024

Second Round Electrical Instalation Training Workshop held on 01 to 05, Jan., 2024 at Hawassa Poly Technic College is started today. The opening speech presented by Zrkarias Chetto, president of SRCA and Zelalem Amberibir, Higher Expert from BAUVERBANDE

የደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ▪️ነጭ ሄልሜት፦ ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች▪️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች▪️ቀይ ሄልሜት፦...
28/12/2023

የደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ

▪️ነጭ ሄልሜት፦ ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች
▪️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች
▪️ቀይ ሄልሜት፦ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች
▪️አረንጓዴ ሄልሜት፦ ለሴፍቲ ሠራተኞች
▪️ግሬይ ሄልሜት፦ ለሳይት ጎብኚዎች
▪️ቢጫ ሄልሜት፦ ለጉልበት እና ለግንባታ ማሽን ኦፕሬተር ሠራተኞች
▪️ ብራዎን ሄልሜት፦ ለበያጆችና ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ቦታ ለሚሰሩ ሠራተኞች

ሠራተኞች በሥራ ወቅት በደህንነት ጉድለት ምክንያት የተለያዩ አደጋዎች እና ጉዳቶች ሲያጋጥሟቸው ይሰተዋላል፡፡ ይህንንም ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የሕግ፣ የህብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ ግንዝቤ ሥራዎች ሲሞከሩ ይታያል፡፡

በተለይም እኤአ ከ1919 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (International Labour Organization/ILO) መቋቋምን ተከትሎ በርካታ ከሠራተኛ የሥራ ደህንነት ጋር የተያያዙ መርሆዎች እያደገ መምጣቱ አይዘነጋም፡፡

ይህንንም ተከተሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ጠቅላላ ጉባዔ እኤአ በ1948 ዓ.ም ባወጣው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights-UDHR) የሥራ ላይ ደህንነት አንዱ የሠራተኞች መብት እነደሆነ ደንግጓል፡፡

የግንባታ ሥራ በራሱ እጅግ ውስብስብ ከመሆኑ ባሻገር በርካታ ሥራዎች በጉልበት የሚከናወኑ (labour intensive) በመሆናቸው ብሎም ከሥራው ባህሪ አንጻር ፈረጅ ብዙ የሥራ ክንውን የሚካሄድበት ስለሆነ በደህንነት ጉደለት ምክንያት በርካታ አደጋ እና ስጋት ሲያጋጥም ይሰታዋላል፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ሪፖርት ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በግንባታ ወቅት ቢያንስ 60ሺ ሠራተኞች ከደህንነት ጉደለት ጋር በተያየዘ ለሞት የሚዳረጉና ከባድ የአካል ጉዳት አደጋዎች እንዳሚያጋጥማቸው ጠቁሟል፡፡ ይህም ማለት በየአስር ደቂቃው ውስጥ አንድ ከባድ አደጋ ይደርሳል እንደ ማለት ነው፡፡ ሪፖርቱም በተለይ ከአጠቃላይ የሥራ ላይ አደጋዎች ውስጥ 17 ፐርሰንት ይህም ከስድስት አደጋዎች ውስጥ አንዱ የሚሆነው ገዳይ አደጋ በግንባታ ዘርፍ እንደሆነ ያትታል፡፡

የግንባታ ደህንነት ሲባል አንድ የግንባታ ፕሮጀክት ከጥንስሱ እስከ ፍጻሜው ድረስ በሚካሄዱ መጠነ ሰፊ የግንባታ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊደረጉ የሚገባቸው እንዲሁም ሊወሰዱ የሚችሉ ጥንቃቄዎች የሚይዝ አሰራር ነው፡፡

የግንባታ ደህንነትን በተመለከተም በ2005 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ደህንነት ጉዳይ ከኢንዱስትሪው ዕድገት ጋር ተያይዞ በትይዩ ትኩረት የሚሠጠው ቁልፍ ስራ መሆን እንዳለበት ይናገራል፡፡ በፈጻሚ አካላት የሚስተዋለው በፕሮጀክት ሳይቶች የሥራ አካባቢ ደህንነት ፖሊሲ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ የሚወጣው ወጪና የሚመደበው ጊዜ እንደተጨማሪ ወጪ አድርጐ የመመልከት እሳቤ በመሠረታዊነት መቀየር እንዳለበትና ለስራ አካባቢ ሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት ጥበቃ የሚወጣ ወጪ የግንባታ ወጪ በመሆኑ ትርፍ እንዳልሆነ አጥብቆ ያሳስባል፡፡

በኮንስትራክሽን ሥራ አካባቢዎች መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ባለመወሰዳቸው ምክንያት የሚደርሱ ከቀላል እስከ ከባድ የንብረትና ህይወት መጥፋት ጉዳቶች መከላከል ያሻል፡፡ እነዚን የመሰሉ አደጋዎች ለመከላለል የሚያስችል በግንባታ ሂደት መወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ በቂ ስልጠናና አፈጻጸሙን መከታተል የዋናው ሥራ አካል ተደርጎ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

የኮንስትራክሽን አካባቢ ደህንነት (Construction Site safety) የግንባታ ሂደቱ ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት መረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ተደርጐ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የኮንስትራክሽን ሥራ እንቅስቃሴ ደህንነት ማስፈን ፖሊሲው አጉልቶ ያስቀመጠበትን ሁኔታ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡

15/12/2023

በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

🚧 “በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

ባዮቴክኖሎጂ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ  ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ነው__▪️በኢትዮጵያ  የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ  ውስጥ ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚካሄደው ጥናት ውጤት እያሳየ ነው።የኮንስት...
13/12/2023

ባዮቴክኖሎጂ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ነው
__▪️
በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም የሚካሄደው ጥናት ውጤት እያሳየ ነው።

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (ASTU) ጋር በቅንጅት እየሠራ ያለውን የባዮቴክኖሎጂ የምርምር ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ በዩኒቨርስቲው ማዕከል አካሂዷል፡፡

የጥናትና የምርምር ሥራው የሚካሄደው ስነ- ህይወትን ( ባክቴሪያን) መሠረት ባደረገ ባዮቴክኖሎጂ የግንባታ ግብአቶችን ለማምረት እንዲሁም የመሰነጣጠቅ ችግር የሆነውን የግንባታ ፈተና ለማዳን እና ለማስወገድ ነው፡፡

ጥናቱ የሚካሄደው በዩኒቨርስቲው በተዋቀረ የጥናት ቡድን አማካኝነት ሲሆን፣ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለጥናቱ በጀት መድቦ ውጤቱን እየተከታተለ ይገኛል፡፡

ጥናቱ እየተካሄደ ያለው Microbial Bio-cement, Bio- blocks, Bio- enzyme and Brick -making machine በሚሉ አራት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

በጉዳዮቹ ላይ የጥናት ቡድኑ አባላት ዶ/ር መስፍን ታፈሰ፣ አቶ ዳንኤል ሙሉ እንዲሁም ዶ/ር ኃይሉ ሽመልስ ዝርዝር ገለፃ አቅርበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት ሙሉ ስሜ እንደተናገሩት፣ አማራጭ የግንባታ ግብአቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ፣ ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገር፣ የፈጠራ ሥራዎችን መደገፍና ማበረታታት የኢንስቲትዩቱ ስልጣን እና ተግባር በመሆኑ በእነዚህ ሥራዎች ዙሪያ በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህ በASTU በኩል የሚካሄደው የባዮቴክኖሎጂ ጥናት እጅግ ጠቃሚ እና አዋጭ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ የሆኑት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ ጥናቱ ከሂደት ወጥቶ በቶሎ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፣ በሁሉም ጥናት ውጤቶች ሠርቶ ማሳያ በቅርቡ ማየት እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች ይህ ባዮቴክኖሎጂ ላይ የሚደረገው ጥናት የሀገሪቱን የኮንስትራክሽን ችግር የሚፈታና ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ፣ አቅምን ያገናዘበ መኖሪያ ቤት ለማግኘት እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በሚደርስባቸው መሰነጣጠቅና በሚፈጥሩት ክፍተት በቶሎ ስለማይጠገኑ በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ኪሳራ ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል።

የASTU ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው፣ የተሰጡ ጠቃሚ አስተያየቶችን በግብአትነት በመውሰድ ጥናቶቹን ተግባራዊ በማድረግ ሥራ ላይ ለማዋል የበለጠ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና የጥናቶቹን የምርምር ውጤቶች በቅርብ እንደሚያሳዩ ቃል ገብተዋል፡፡

በዕለቱ Brick- making machine እና በዚህ ማሽን በተመረተ ብሎኬት የሚሠራ ቤት የሚታይበት መስክ በተሳታፊዎቹ ተጎብኝቷል።

13/12/2023

በፕሮጀክቶች ላይ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶች አማራጭ የግጭት አፈታት አገልግሎትን ያግኙ

“በብዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች አለመግባባት ተፈጥሮአዊ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለፅ እውነታ ነው፡፡ በህግ ወይንም በውል የተገለፁ መብቶች ያለመከበር እና የይገባኛል ጥያቄዎች ለእነዚህ አለመግባባቶች መፈጠር መሰረታዊ ምክንያት ናቸው፡፡ መሰል ይገባኛል ጥያቄዎችን በአግባቡ መፈታት ያልተቻለ እንደሆነ ጉዳዩ ወደ አለመግባባት ደረጃ የማደግ እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም ያለመግባባቶች ከፍ ወዳለ ደረጃ ከማደጋቸውና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት መታረም መቻላቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ ያጋጠሙ አለመግባባቶችን መፍታት አሁን አሁን ይበልጥ እየታመነበት የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የግንባታ ዘርፉም ከግጭቶች/ ካለመግባባቶች የፀዳ ባለመሆኑ በተመሳሳይ ዕይታ የሚታይ እና መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

የግንባታ ሂደት በውስጡ ከሚሳተፉ ባለድርሻዎች፣ ከሚፈስበት መዋዕለ ነዋይ እንዲሁም ከሚወስደው ጊዜ ውስብስብነት ወዘተ አንፃር አለመግባባት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን መፍታት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች በስፋት ይገልጻሉ፡፡

ስለሆነም ግጭቶች/ አለመግባባቶች/ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አለመግባባቶችን መፍታት በተከራካሪ ወገኖች መካከል መልካም ግንኙነትን ከማስቀጠል አኳያ፣ ከህግ ሙያ ውጪ ያሉ ሌሎች ባለሙያዎችን ከማሳተፍ በተጨማሪ ጊዜን፣ ወጪን እና በዳኝነት ተቋማት ላይ የሚፈጥረውን ጫና የሚቀንስ በመሆኑ ይህ አሰራር በግንባታ ዙሪያ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተቋቋመ እና ስልጣኑንና ተግባሩንም ለመወሰን እንደዚሁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 524/2015 መሰረት አድርጎ መቋቋሙ ይታወቃል፡፡
ይህን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ የዳኝነት እና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013ን መሠረት በማድረግ እና በደንብ ቁጥር 524/2015 አንቀጽ 5 (16) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በሚዘረጋው አሰራር ስርዓት ፕሮጀክቶች/ ተዋዋዮች በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መነሻነት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት ኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚፈጠሩ የውል አለመግባባቶች በዘረጋው የአሰራር ስርዓት በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም የህንጻና የመሠረት-ልማት ፕሮጀክቶችን የሚያስገነቡ እና እያስገነቡ ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አለመግባባቶችን በአማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎች መፍታት የሚፈልጉ የመንግስት ተቋማት ወይም ግጭቶችን በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎች ለመፍታት የህግ ስልጣን ያላቸው ተቋማት አገልግሎቱን ከባለስልጣን መ/ቤቱ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

(የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን)

ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ...
27/11/2023

ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓቱን የማብላላት ተግባር ያለውን የፋብሪካው ክፍል እና ወደ ቀጣዩ ሂደት ማስተላለፊያ ቱቦ መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር በመሆን እየተገነባ ያለውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ቀንና ማታ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ሂደትን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

(FBC)

የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ተመለከተበሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገለጹ፡፡ፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬ...
11/11/2023

የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ተመለከተ

በሲሚንቶ፣ በብረትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ገለጹ፡፡

ፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ የሲሚንቶና የብረት ማምረቻ ፋብሪካዎችና የንግድ ሱቆች ላይ ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጓል፡፡

በተደረገው ምልከታም የ1 ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከ800 ብር እስከ 500 ብር ቅናሽ እንዲሁም 1 ቤርጋ ፌሮ በኪሎ የ15 ብር ቅናሽ ማሳየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የሲሚኒቶና ብረት ግብይት በሚደረግባቸው አካባቢዎች በተደረገው ምልከታም የሲሚኒቶ፣ የብረት እና ሌሎች የኮንስትራክሽን እቃዎች ቅናሽ ማሳየታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ቀደም ሲል ግብይቱ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተመን ወጥቶለት ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም ከታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም ወዲህ ግን በነጻ ገበያ መርህ ፋብሪካዎች ባቀረቡት ዋጋ ግብይትት መካሄድ መቀጠሉን በቅኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 800 እስከ 2 ሺህ ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ኢትዮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 250 እስከ 1 ሺህ 270፣ ሀበሻ ሲሚንቶ በ1 ሺህ 300 ብር እና ሙገር ሲሚንቶ በ1 ሺህ 350 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል÷ የብረት ገበያም በተመሳሳይ ምልከታ የተደረገበት ሲሆን በተመሳሳይ ቅናሽ የታየበት መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡

ለአብነትም 10 ቤርጋ ብረት 1 ሺህ 332 ሲሸጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 36 ብር፣ 14 ቤርጋ ፌሮ ብረት 3 ሺህ 412 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 2 ሺህ 654 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

በዘርፉ ላይ የተሰማሩት አምራቾችና ነጋዴዎች ሲሚንቶ፣ ብረትና ሌሎችም የግንባታ እቃዎች ሸማቾች ቁጥር መቀነሱንም አመላክተዋል።

በሜሮን ሙሉጌታ
ምንጭ፡ (ፋና ብሮድካስቲንግ)

ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆ...
11/11/2023

ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ 1 ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች መገንባትን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ሪቪዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል፡፡

በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አመላክቷል።

ምንጭ፡ (አዲስ ማለዳ)

ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ አውደ ጥናት ተጠናቀቀጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአለም ባ...
06/11/2023

ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ አውደ ጥናት ተጠናቀቀ

ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአለም ባንክ ባገኘው ድጋፍ ዳር አልሀንዳስ ከተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጋር በሚያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ የመንገድ መሰረተ-ልማት ማኑዋሎች ማሻሻያ ላይ ለ7 ቀናት ሲመክር የሰነበተው አውደ ጥናት ተጠናቀቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ወደ ላቀ የአፈፃፀም ደረጃ ለማሸጋገር እገዛ የሚያደርጉ 28 ማንዋሎች እየተዘጋጁ ነው፡፡

በአውደ ጥናቱ መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡእንደገለፁት የማኑዋል ጥናቱ ዘመናዊ፣ ወጪ እና ጊዜን ቆጣቢ እንዲሁም ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ምቹ የሆኑ የመንገድ መሰረተ-ልማት ለማስፋፋት ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በጥናት ላይ የሚገኙት ማኑዋሎች ተጠናቀውና ፀድቀው በሥራ ላይ ሲውሉ፣ ከዚህ ቀደም በመንገድ ግንባታ ወቅት የሚያጋጥሙ የተለያዩ ችግሮችን ለመቅረፍና አዳዲስ አሰራሮችን በማካተት በከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡

ለሰባት ቀናት በተካሄደው በዚህ አውደ ጥናት ላይ ከተሳታፊ አካላት ጠቃሚ የሆኑ ግብአቶች እንደተገኙ ገልጸው፣ ለማኑዋሎቹ መዳበር ፋይዳ ያላቸውን ሃሳቦች በመሰንዘር በውይይቱ ላይ ለተሣተፉ የባለድርሻ አካላትና የአማካሪ ድርጅቱ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌደኦ ዞን የቡሌ ወረዳ አስተዳደር በቁጥር BRG/01/4210/2015 በቀን 30/2/2015 የቡሌ ወረዳ ፋይናንስ በተጠየቁት ጥያቄ መሰረት የ...
30/10/2023

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌደኦ ዞን የቡሌ ወረዳ አስተዳደር በቁጥር BRG/01/4210/2015 በቀን 30/2/2015 የቡሌ ወረዳ ፋይናንስ በተጠየቁት ጥያቄ መሰረት የአስተዳደር አጥር ዙሪያ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታ ሠነድ ጋር

1. በዘመኑ በመንገድ ሥራ የታደሰ እና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ 2015/2016/ ዓ.ም ያለው /ላት፣

2. የግብር ከፋይነት የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፊከት እና ቲን ነምበር ያለው /ላት፣

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ትችል 4.በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ማስረጃ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤቱ ማቅረብ የሚችል/ትችል 5 በዘርፉ በግንባታ ሥራ ፍቃድ ደረጃ 6 በላይ ማቅረብ የሚችል /ትችል 6.በዶክመንቱ ላይ የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት የሚችል/የምትችል

* ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከቡሌ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ለየአንዳንዱ ሎት 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ኦርጅናል ፍቃድ በመያዝ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

* ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት ዋጋ 1.5%/ሃያ በፖስታ በማሽግ ከኦርጅናል ሠነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡

* ተጫራቾች ስፔስፊኬሽን ላይ በመሙላትን የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ ማሳረፍ ይኖርባቸዋል::

* ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሁለት ፖስታ አንድ ኦርጅናልና ሁለት አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በስም በማሸግ ከ7 የተዘረዘሩትን የህጋዊነት ማረጋገጫ መረጃዎችን አሟልተው በአንድ እናት ፖስታ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡

* ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ለ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ6 ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽገው በ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን በ8፡ዐዐ ሰዓት ታሽገው በ8:30 የሚከፈት ይሆናል፡፡

* ተወካዮች ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ይዘው መቅረብ አለባቸው:: ማስረጃ ካልያዙ መሳተፍ አይችሉም፡፡

* ተጫራቾች ጨረታ ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ 10% እና የቅድመ ክፍያ 30% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገ በስስከ ቁጥር፡-0910583598/0916330435
በደ/ኢት/ክልላዊ መንግሥት የቡሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

30/10/2023

በመንገድ ግንባታ ዲዛይን ዝግጅት ወቅት ለአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለፀ

🌟የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዳር አልሀንዳስ በተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት አማካኝነት የከተማዋ የመንገድ መሠረተ-ልማት ግንባታ ስራዎች የሚመሩበትን ልዩ ልዩ ማንዋሎች ለማዘጋጀት ጥናት እያካሄደ ይገኛል።

🚧በዚህ ሣምንት አጋማሽ ላይ በተጀመረው እና ለተከታታይ ሰባት ቀናት በሚዘልቀው የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ እንደቀጠለ ነው። በመንገድ ዲዛይን ማኑዋልና ስፔስፊኬሽን ዝግጅት ላይ ትኩረት አድርጎ በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ እንደተገለፀው፣ በመንገድ ዲዛይን ዝግጅት ወቅት ለአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

🚧በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ በርካታ ባለድርሻ አካላት እየተሣተፉ የሚገኙ ሲሆን፤ በአዲሱ የመንገድ ግንባታ ማንዋል ዝግጅት ውስጥ አካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች፣ እንዲሁም የስራ ላይ ደህንነት እና የፆታ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊካተቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

🚧አዲሱ የዲዛይን ማንዋልና ስፔስፊኬሽን ዝግጅት፤ በመንገድ ግንባታ ስራ ላይ በግልፅ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለበትም አስተያየት ሰጭዎቹ አሳስበዋል፡፡

🚧በተለይም በስራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመከላከል፣ የስራ ተቋራጮች እና የግንባታ ባለቤቶች ለስራ ላይ ደህንነት ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩ ለማስቻል የግንባታ ማኑዋሎችና መመሪያዎች አስገዳጅ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ተግባራዊ መድረግ እንዳለባቸውም በውይይቱ ተሳታፊዎች ተንፀባርቋል፡፡

Address

Awassa

Telephone

+2510462121556

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SRCA - South Region Contractors Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to SRCA - South Region Contractors Association:

Share