Centeral Ethiopia Region Athletics Federation

Centeral Ethiopia Region Athletics  Federation አትሌቲክሱን ለማሳደግ ተግቶ ይሰራል

22/04/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ18 እና 20 ዓመት በታች ወጣቶችና ታዳጊዎች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።በውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል አትሌ...
22/04/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ18 እና 20 ዓመት በታች ወጣቶችና ታዳጊዎች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ እና የፌዴሬሽኑ ሰራ አሰፈፃሚ አባላት ተገኝቷሉ። በውድድሩ መክፈቻ ፕሮግራም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ በክልል ደረጃ እንዲህ አይነት ውድድሮች መዘጋጀቱ የክልሉን አትሌቲክስ ለማነቃቃትና ተተክ አትሌቶችን ለማፍራት ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በውድድሩ ተወዳዳር የሆኑ ዞኖችና ልዪ ወረዳዋች በስፖርቲዊ ጨዋነት በውድድሩ እንድትሳተፉ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋሉ።

አትሌቶች ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ በመግለፅ በቀጣይም ቀናት በሚደረገው ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና ውጤታማ እንዲሆኑ ጠንክረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፈው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት። በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ  የተገኙት የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳ...
23/03/2026

55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፈው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት። በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ በውድድሩ ላይ የክልሉን መልካም ገጽታ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ብርቱ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ሆነው እንድመለሱ መልዕክት አስተላልፏሉ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር ምስረታ ጉባኤ ተካሄደ ። በምስረታ ጉባኤ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ : የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካ...
26/12/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር ምስረታ ጉባኤ ተካሄደ ። በምስረታ ጉባኤ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ : የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካይ እና የሁሉም ዞንና ልዪ ወረዳ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋሉ። ጉባኤው ኢንስትራክተር ጋሻሁን እሳቱን የማህበሩ ፕሬዚዳንት እና ሌሎችን ስራ አስፈፃሚዎችን በመምረጥ ጉባኤው ተጠናቋል ።

03/11/2025
23/10/2025
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 2ተኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል ።
10/10/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 2ተኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል ።

2ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አትሌቲክስ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ማጣሪያ ውድድር በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ተጀመረ ።
10/10/2025

2ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል አትሌቲክስ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ማጣሪያ ውድድር በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ተጀመረ ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ በ2017 ዓ.ም ዕቅድ   አፈፃፀምና በ2018 እቅድ ላይ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ውይይት አደረገ።
10/10/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ በ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና በ2018 እቅድ ላይ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ ውይይት አደረገ።

ለተከታታይ ለአስራ አምስት ቀናት ስልጤ ዞን  በወራቤ ከተማ  ስሰጥ የነበረው የአትሌቲክስ 1ኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ!በመርሃ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮ...
11/08/2025

ለተከታታይ ለአስራ አምስት ቀናት ስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ ስሰጥ የነበረው የአትሌቲክስ 1ኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ!
በመርሃ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንዲህ አይነት ደረጃውን የጠበቀ ሳይንሳዊ ስልጠና መሠጠቱ በክልሉ ታዳጊ አትሌቶችን ለማፍራት ጉልህ ሚና አለው ብለው ስልጠናውን ያዘጋጀውን ስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አመስግነዋሉ።የስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈቱ ኪምባዶ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ስልጠና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ከፍተኛ የክህሎትና ብቃት ለውጥ እንድመጣ የአሰልጣኞች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ስልጠናውን የሰጡት ኢንስትራክተር ጋሻሁን እሳቱ በክልሉ እንዲህ አይነት ስልጠናዋች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋሉ። በመዝጊያ ፕሮግራሙ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዚዳንት አቶ ቡላድ ነሙዝ እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋሉ።

Address

Hawassa
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Centeral Ethiopia Region Athletics Federation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share