Gudumale Sustainability Initiative-GSI

Gudumale Sustainability Initiative-GSI Gudumale Sustainability Initiative (GSI) aims to create thriving, healthy, diverse and resilient communities for this generation and generations to come.

ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ?  *******ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ ያስቀጣል። ታዲያ ለገበያ ምን ...
30/01/2026

ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ?
*******

ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ ያስቀጣል።

ታዲያ ለገበያ ምን ይዘን እንውጣ? ከቤትዎ ሲወጡ የጨርቅ ከረጢት ወይም ዘላቂ የሆኑ የሸመታ ከረጢቶችን መያዝዎን ያረጋግጡ።

ይህ አዲስ መመሪያ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትልቅ እርምጃ ነው።

የፕላስቲክ ከረጢቶች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የሚደነቅ ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት በቂ ተኪ ምርቶች ተዘጋጅተው ይሆን?

በዚህ ጉዳይ ምላሽ የሰጡት በፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን አለሙ እንደገለጹት ፤ መንግሥት እና የግል ባለሀብቶች ፕላስቲክ ከረጢትን ተኪ ምርቶች ላይ እየሰሩ ስለመሆናቸው ነው ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሱት ።

ያቀረቧቸውን ነጥቦች መሠረት በማድረግ፣ ስለ ተኪ ምርቶቹ እና ስለ ሕጉ አፈጻጸም ዝርዝር መረጃዎችን በሚከተለው መልኩ ማጠቃለል ይቻላል፦

✅ ከጥጥ ጨርቅ የሚሰሩ ከረጢቶች፦ እነዚህ ከረጢቶች ታጥበው ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ለዘላቂነት ተመራጭ ናቸው።

✅ ከካኪ (ወረቀት) የሚሰሩ ምርቶች፦ በተለይ ለደረቅ ዕቃዎች እና ለምግብ ነክ ግብይቶች ውጤታማ ናቸው።

✅ የማምረት አቅም፦ በአሁኑ ወቅት ሶስት ትላልቅ ተቋማት በቀን እስከ 55,000 የሚደርሱ የጨርቅ ከረጢቶችን እያመረቱ ሲሆን፣ በርካታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የመንግሥት ድጋፍ እና ማበረታቻ

ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት የሚከተሉትን ማበረታቻዎች እያቀረበ ይገኛል፦

✅ከቀረጥ ነፃ መብት፦ ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከቀረጥ ነፃ መብት ተሰጥቷል።

የፋይናንስ ድጋፍ፦ አምራቾች ካፒታል እንዲያገኙ ከባንኮች እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የውይይት መድረኮች ተመቻችተዋል።

ጥሬ ዕቃ፦ ምንም እንኳን በጥሬ ዕቃ ላይ የተወሰነ ቀረጥ ቢኖርም፣ ምርቱን ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

✅ሊታረሙ የሚገባቸው የተሳሳቱ አመለካከቶች

ባለሙያው እንደገለጹት፣ "ያልተሸመነ ጨርቅ" (Non-woven fabric) ከፕላስቲክ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው እና ለረጅም ጊዜ ስለማያገለግል፣ አምራቾችም ሆኑ ሸማቾች ከዚህ ምርት ይልቅ ዘላቂ የሆኑ የጨርቅ ከረጢቶችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።

✅የሸማቹ ሚና

ሕጉ ውጤታማ እንዲሆን የሸማቹ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

✅ከቤት ይዞ መውጣት፦ እያንዳንዱ ሸማች ለገበያ ሲወጣ የራሱን ዘላቂ ከረጢት (Reusable bag) የመያዝ ልምድ ማዳበር ይኖርበታል።

✅ግንዛቤ፦ ፕላስቲክ የሚያስከትለውን የጤና እና የአካባቢ ጉዳት በመገንዘብ ሕጉን ማክበር።

መልካም አዲስ አመት 2018Happy Ethiopian 🇪🇹 New Year
11/09/2025

መልካም አዲስ አመት 2018
Happy Ethiopian 🇪🇹 New Year

Day 2 – Africa Climate Summit 2Our Deputy Director, Betel Melaku, is actively engaging in meaningful networking on clima...
09/09/2025

Day 2 – Africa Climate Summit 2
Our Deputy Director, Betel Melaku, is actively engaging in meaningful networking on climate financing, building connections that strengthen our mission and contribute to advancing sustainable solutions.

08/09/2025
Betel Melaku, Deputy Director of Gudumale Sustainability Initiative (GSI), is taking part in the African Climate Summit ...
08/09/2025

Betel Melaku, Deputy Director of Gudumale Sustainability Initiative (GSI), is taking part in the African Climate Summit 2 at the Addis Ababa Convention Center.
As GSI continues its mission in climate change adaptation, ecosystem restoration, and youth-led environmental action, participating in such a high-level summit is vital for strengthening collaboration, sharing solutions, and ensuring local voices contribute to Africa’s climate future.

28/08/2025
Recap the international youth day - Hawassa In Hawassa, we witnessed that youth are not just the future—they are the pre...
25/08/2025

Recap the international youth day - Hawassa

In Hawassa, we witnessed that youth are not just the future—they are the present force shaping our community.

24/08/2025
Hawassa' Youth led Organizations Celebrate International Youth Day warmly! For the 25th time globally and the 22nd time ...
24/08/2025

Hawassa' Youth led Organizations Celebrate International Youth Day warmly!

For the 25th time globally and the 22nd time nationally, International Youth Day was colorfully celebrated in Hawassa City under the global theme “Local Youth Actions for the SDGs and Beyond”

The event brought together government leaders, inspiring young change-makers, youth-led organizations, and invited guests who marked the day with enthusiasm and solidarity.

Delivering a message on the occasion, Mrs Frewoit W/tsadik, Head of Hawassa City Women and Youth Social Affairs Bureau, congratulated the youth on their special day. She emphasized that by participating in such platforms, young people can share experiences, build skills, and strengthen their competitiveness on the global stage.

Similarly, Mr Kifle Ware, Deputy Head of the Bureau and Youth Affairs Coordinator, highlighted that the deep potential of youth must be fully utilized to achieve the SDGs. He also announced that more youth-centered forums will be organized in the near future.

The program featured:

Awareness-raising on the Sustainable Development Goals (SDGs)

የሀዋሳ ከተማ የወጣት አደረጃጀቶች ወጣት መር ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ዓለም የወጣቶች ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ25ኛ ጊዜ በሀገር ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ "የተደመረ የወጣቶች አቅም ለዘላቂ ልማት ግቦች" በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ የመንግስት አመራሮች፣ ተፅኖ ፈጣሪ ወጣቶች፣ የወጣት መር ድርጅት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በዝግጅቱ መልዕክት ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ መምርያ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬዎት ወ/ፃዲቅ እንኳን ለወጣቶች ቀን አደረሳችሁ በማለት ወጣቶች እንዲህ አይነት መድረኮች ላይ በመሳተፍ ልምድ እና ተሞክሮዎችን በመቅሰም አለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ መምርያ ም/ሀላፊ እና የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ክፍሌ ዋሬ የወጣቶችን እምቅ አቅም ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ በማብራራት በቀጣይ መሰል የወጣቶች መድረክ እንደሚዘጋጁ ገልፀዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦችን ዙሪያ ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም
በጎ-ተፅኖ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶች ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች አገርተዋል።

በመጨረሻም ወጣት ተኮር በሆኑ ስራዎቻቸው እና በወጣትነት እድሜያቸው ውጤታማ ከሆኑ ወጣቶች የተገባዙበት "ዘላቂ የልማት ግቦች እና የወጣቱ ሚና" በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

የዝግጅቱም ተሳታፊዎች ተመሳሳይ መድረኮች በከተማ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስታየታቸውን በመግለፅ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘታቸው ልምድ እና ተሞክሮ መቅሰማቸውን ገልፀዋል።

ዝግጁን የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር፣ የሀዋሳ ከተማ ክበባት ጥምረት፣ የባህል አዳራሽ ክ/ከተማ የወጣቶች ክንፍ፣ የሲዳማ ክልል የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ጤና ካውንስ፣ መቅረዝ የተቀናጀ የወጣቶች ልማት ድርጅት፣ ሀ-ግዕዝ ሐበሻ የበጎ-አድራት እና የኪነ-ጥበብ ማህበር፣ ጉዱማሌ ሰስተነብሊቲ ኢንሼቲቭ በጋራ አሰናድተውታል

Our Panelist for
22/08/2025

Our Panelist for

🌍✨ ወሳኝ ማስታወቂያ ለሀዋሳ ወጣቶች! ✨🌍የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተሳታፊዎች ምዝገባ  አሁን በይፋ የተዘጋ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። ለተመዘገባችሁ ሁሉ እናመሰግናለን! በዚህ ል...
21/08/2025

🌍✨ ወሳኝ ማስታወቂያ ለሀዋሳ ወጣቶች! ✨🌍

የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተሳታፊዎች ምዝገባ አሁን በይፋ የተዘጋ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

ለተመዘገባችሁ ሁሉ እናመሰግናለን!

በዚህ ልዩ ቀን የወጣቶች አቅምን እና ለዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ያለንን የጋራ ቁርጠኝነታችንን በማሳየት ለማክበር ተዘገጅተናል።
ከልብ እናመግናለን

የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል! 📅 ቀን፡ቅዳሜ ነሀሴ 17🕗 ሰዓት፡ 8፡00 📍 ቦታ፡ ሌዊ ሆቴል ፒያሳ ሀዋሳየወጣቶች እምቅ ችሎታ በሚንጸባረቅበት  በዚህ ደማቅ መርሀ ግብር ...
20/08/2025

የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል!

📅 ቀን፡ቅዳሜ ነሀሴ 17
🕗 ሰዓት፡ 8፡00
📍 ቦታ፡ ሌዊ ሆቴል ፒያሳ ሀዋሳ

የወጣቶች እምቅ ችሎታ በሚንጸባረቅበት በዚህ ደማቅ መርሀ ግብር ላይ ይሳትፉ፡፡ የዚህ አመት መሪ ቃል “የተደመረ የወጣቶች አቅም ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት” በሚል ይከበራል፡፡

አዘጋጆች፡

የሀዋሳ ከተማ የወጣቶች ማህበር፣ Sidama Region Adolescent & Youth Health Council, Ha geez Habsha Volunteers & Art Association, Hawassa City Art & volunteers Conjunction, የባህል አዳራሽ ክ/ከተማ ወጣቶቸ ክንፍ
Meqrez Integrated Youth Development Organization, Gudumale Sustainability Initiative, እና ሌሎች የወጣት መር ድርጅቶች

ዕለቱ ፡
✨ የመንግስት አካላትና ወጣት ተወካዮች ንግግሮች
✨ በዘላቂ የልማት ግቦች እና የወጣት ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት
✨ የመዝናኛ ፕሮግራም
✨ ትውውቅ እና ኔትዎርኪንግ

🚀 የመሳተፍ ፍላጎት ካለዎት፣ አሁን ይመዝገቡ! https://forms.gle/FEBgBpobSFx335rP7

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gudumale Sustainability Initiative-GSI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gudumale Sustainability Initiative-GSI:

Share