Alif Agri Business

Alif Agri Business ...

26/03/2026

"አሰብ የአባቴ የዘላለም ቁጭት፣ የእኔም የታሪክ ውርስ ነው!” - የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ እውነተኛ ታሪክ
********************

አሰብ ሲነሳ ለብዙዎች የካርታ ላይ መስመር ወይም የፖለቲካ መነጋገሪያ ሊሆን ይችላል፤ ለእኔ ግን የደም ስሬ፣ የልጅነት ትውስታዬና የአባቴ የዕድሜ ልክ ናፍቆት ነው።

አባቴ ፈንታው አደም በአሰብ ነጋዴ ሰፈር ስሙ ገዝፎ የሚነሳ፣ በንግዱና በሥራ ወዳድነቱ የሚታወቅ ብርቱ ሰው ነበር። አሰብ ለእሱ መኖሪያ ብቻ ሳትሆን ማንነቱ፣ ሀብቱና ክብሩም ነበረች።

የ1983 ዓ.ም የመለያየት ንፋስ ሲነፍስ ወንድሞቼና እህቶቼ በጅቡቲ በኩል ተሰደዱ፤ አባቴ ግን "ሀገሬን ጥዬ አልወጣም" ብሎ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ከአሰብ ጋር ግብግብ ገጠመ። በ1986 ወይም 87 አካባቢ አሰብን ለቆ የወጣው የመጨረሻው ተፈናቃይ እሱ ነበር።

ከአሰብ ቢወጣም ልቡ ግን እዛው ቀርቷል። ኮምቦልቻ ካምፕ ውስጥ ተጠልሎ ሳለ እንኳ በረሃውና የለመደው የንግድ ግርግር እየመጣ ሲቀሰቅሰው "የአሰብ ተፈናቃይ" የሚለውን ስም ሊለምደው አልቻለም። ናፍቆቱ ሲበዛበት ለአሰብ ቅርብ ወደሆነችው ዲቺኦቶ (በአፋር ክልል በአሁኑ የኤሊዳር ወረዳ ውስጥ የምትገኘ የንግድ ቦታ ነች) ተመልሶ መነገድ ጀመረ፤ ሁሌም ግን ከጓደኞቹ ጋር ቁጭታቸው አንድ ነበር "አሰብ ተመልሰን ሄደን የድሮ ሕይወታችንን በኖርን" የሚል፡፡

አባቴ በ2007 ዓ.ም አላህ ይርሃመውና ከዚህ ዓለም ሲለይ፣ ያንን ትልቅ ተስፋና ቁጭት በእኔ እጅ አስቀምጦ አልፏል። ዛሬ እኔ ጋር የአባቴ ንብረት የሆኑ የቤትና የንግድ ቦታዎች ሕጋዊ ካርታዎችና ሰነዶች አሉ። "ይሄ የእኛ ነው" እያለ ያሳየን የነበረው ያ የንግድ ቦታና የመኖሪያ ቤት ዛሬም በዓይነ ሕሊናዬ ይርመሰመሳል።

አሁን የወደብና የአሰብ ጉዳይ ሲነሳ "የአባቴ ምኞት በእኔ ዘመን እውን ይሆን ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በውስጤ በኃይል ይጮኻል።

አሰብ ለኮምቦልቻ፣ ለባቲና ለአካባቢው ሕዝብ የሕልውና መሠረት፣ የንግድ መፍለቂያና የትልቅ ተስፋ ምድር ነበረች። እኔ የአባቴን ታሪክ የምሸከም፣ ሰነዱን የያዝኩ ሕጋዊ ወራሹ ነኝ።

ያ የቁጭት ታሪክ ተቀይሮ፣ አባቴ በሕይወት እያለ ያላየውን ያንን የወደብ ብርሃን እኔ ሄጄ የማየውና ለእናንተም በደስታ የምነግራችሁ ቀን ቅርብ እንደሆነ አምናለሁ። የታሪክ ፍትህ የአባቴንና የሺዎችን ቁጭት የሚያብስበት ጊዜ ይመጣል።

የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ ሃያት ፈንታው እንደተረከችው

ሙሉ ታሪኩን ለመመልከት በኮሜንት ሴክሽን ስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

#ኢትዮጵያ #አሰብ #የወደብጉዳይ #ቁጭት #ትውስታ

26/03/2026
06/03/2026
28/01/2026
27/01/2026
23/01/2026

Ethiopia 🇪🇹 Makes History!

Addis Ababa is set to host the World Internet Conference (WIC) this September, marking the first time the global tech summit will be held outside China.

With 200+ tech giants expected to attend — including Google and NVIDIA — this is a major milestone for Ethiopia’s growing digital economy and a big boost for tech tourism.

The event places Ethiopia firmly on the global tech map and highlights Africa’s rising influence in the digital future.

19/01/2026
22/12/2025

25/11/2025

⚡ኑ ነገን ዛሬ አብረን እንሥራ!

💡የአገልግሎት አሰጣጥ የፈጠራ ሐሳቦች ጥሪ

የኢፌዴሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን "የሕዝብ አገልግሎት የፈጠራ ማዕከል" (Public Service Innovation Lab) ወደ ሥራ ማስገባቱን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ማዕከሉ ዘርፉን ከግትር ቢሮክራሲ ነጻ በማውጣት፣ ሳይንሳዊ አሰራርንና የፈጠራ ንድፈ-ሐሳቦችን መሰረት አድርጎ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ እንዲተላለፍ በማስቻል፣ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አዳዲስ ሐሳቦችን በነፃነት ለመሞከር የሚያስችል ምቹ መድረክ ለመፍጠር ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡

በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን፤ የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሀሳቦች እና መፍትሄዎች አለን ለሚሉ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ሁሉ ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪውን ያቀርባል።

🎯የጥሪው ዓላማ
👉 የዚህ ጥሪ ዋና ዓላማ፤ ተለዋዋጭ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን እና የልማት አቅጣጫዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ፈጠራና ፍጥነት ማዕከል አድርገው የሚያቃልሉ፣ እንዲሁም የዘርፋችንን አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦችን ማበረታታት ነው፡፡

👉የሚቀርቡ የአገልግሎት አሰጣጥ የፈጠራ ሐሳቦች ትኩረት ለሕዝብ አገልግሎት የፈጠራ ማዕከል የሚያቀርቡት ሀሳብ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል፣

👉ሀሳቦቹ ቅልጥፍናን በማሳደግ፣ ውጤትን በማላቅና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ሆነው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

✅የአገልግሎት ቅልጥፍናን፣ ፍጥነትንና ጥራትን የሚጨምር፣
✅አካባቢያዊ፣ ክልላዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ፣
✅የአሠራር ማነቆዎችን የሚፈታና ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር፣
✅አሁናዊ ሁኔታን ብቻ ሳይሆን መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ፣
✅ግልጽነትና ተጠያቂነትን እውን በማድረግ መልካም አስተዳደርን የሚያሻሽል፣
✅በአገልግሎት ሰጪና በተገልጋይ መካከል ያለውን ግንኙነት በማሳለጥ መተማመንን የሚፈጥር፣ እንዲሁም
✅ሥራዎችን እና አሰራሮችን የሚያዘምን መሆን ይኖርበታል።

🤝ማዕከሉ የሚያደርገው ድጋፍ

✍️ የሚያቀርቡት ሀሳብ በመነሻ (Concept)፣ በናሙና (Prototype) ወይም ለሙከራ ዝግጁ በሆነ ደረጃ ላይ የደረሱ ሊሆኑ ይችላሉ፣
✍️ ሀሳብዎ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢሆን የበለጠ ለማሳደግ፣ ለመሞከር እና ተግባራዊ ለማድረግ በተዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሰረት ማዕከላችን የሚያስፈልጉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

👥የአገልግሎት አሰጣጥ የፈጠራ ሐሳቦችን ማን ማቅረብ ይችላል ?

👉 ማንኛውም ግለሰብ
👉የተለያዩ አደረጃጀቶች እና ማህበራት
👉ኢንተርፕሪነሮች (Entrepreneurs)
👉ማህበራዊ ድርጅቶች
👉መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት
👉የትምህርትና የምርምር ተቋማት
👉በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

📮የአገልግሎት አሰጣጥ የፈጠራ ሐሳቦችን እንዴት ማቅረብ ይቻላል?

በዘርፋችን ያለውን አገልግሎት ለማላቅ የሚያስችሉ ሀሳቦችን ለማቅረብ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሚከተሉት መንገዶች ሀሳባችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ፡-

✅ በኢሜይል: ሙሉ የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን በ [email protected] ላይ በመላክ ወይም
✅ በአካል: ላም በረት አካባቢ በሚገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአካል በመምጣት ሀሳቦን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ህዳር 16/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

29/10/2025

“የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን።” - ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

#የጠሚሩምላሾች

05/09/2025

𝗔𝗳𝗿𝗶𝗰𝗮’𝘀 𝗖𝗹𝗶𝗺𝗮𝘁𝗲 𝗪𝗲𝗲𝗸 𝟮-𝟮𝟬𝟮𝟱 (𝗖𝗪𝟮) 𝘀𝘂𝗰𝗰𝗲𝘀𝘀𝗳𝘂𝗹𝗹𝘆 𝘀𝘁𝗮𝗿𝘁𝗲𝗱 𝘁𝗼𝗱𝗮𝘆 𝗶𝗻 𝗔𝗱𝗱𝗶𝘀 𝗔𝗯𝗮𝗯𝗮 𝘂𝗻𝗱𝗲𝗿 𝘁𝗵𝗲 𝘁𝗵𝗲𝗺𝗲: ❝𝗗𝗶𝗮𝗹𝗼𝗴𝘂𝗲𝘀 𝗳𝗼𝗿 𝗔𝗺𝗯𝗶𝘁𝗶𝗼𝗻 𝗮𝗻𝗱 𝗜𝗺𝗽𝗹𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻.❞

Organized by the UNFCCC and hosted by the Government of Ethiopia, it brought together global policymakers, financiers, international organizations, CSOs, the private sector, and community voices, all engaging in critical dialogues for ambition and implementation, turning ambitions into real action.

Today, for the CW2, the session explores the possible way of enhancing ambitions within the Nationally Determined Contributions (NDCs) through an innovative way of undergoing dialogues named "NDC Clinics". The dialogues on the Just Transitions has drawn a number of participants and hot discussions in finding ways to narrow down differences among parties to the Paris Agreement in defining the best use of opportunities thereon, engaging in Just Transitions across national and global contexts. Dialogues on climate finance is another issued discussed by delegates focusing on the possible ways of addressing the finance gaps existing to implement the NDCs and NAPs.

CW2 is setting the stage for the Second Africa Climate Summit (ACS2), building momentum and highlighting African contexts, opportunities, and solutions that will drive ambitious commitments for global climate action.

Together, these back-to-back events represent a turning point: African leadership shaping climate solutions that inspire action from Addis to COP30 and beyond.

𝐓𝐡𝐞 𝐨𝐟𝐟𝐢𝐜𝐢𝐚𝐥 𝐡𝐢𝐠𝐡-𝐥𝐞𝐯𝐞𝐥 𝐨𝐩𝐞𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐨𝐟 𝐭𝐡𝐞 𝐂𝐖𝟐 𝐰𝐢𝐥𝐥 𝐛𝐞 𝐡𝐞𝐥𝐝 𝐨𝐧 𝟑 𝐒𝐞𝐩𝐭𝐞𝐦𝐛𝐞𝐫 𝐰𝐢𝐭𝐡 𝐭𝐡𝐞 𝐩𝐫𝐞𝐬𝐞𝐧𝐜𝐞 𝐨𝐟 𝐠𝐮𝐞𝐬𝐭 𝐨𝐟 𝐡𝐨𝐧𝐨𝐫 𝐟𝐫𝐨𝐦 𝐭𝐡𝐞 𝐆𝐨𝐯𝐞𝐫𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 𝐨𝐟 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚.

Learn more about the ACS2:

https://africaclimatesummit2.et‬

Address

Afar
Awash

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alif Agri Business posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share