Youth Sound Of Awash Fanti Qale

Youth Sound Of Awash Fanti Qale Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Youth Sound Of Awash Fanti Qale, Community Organization, Awash.

03/01/2026
03/01/2026
14/11/2025

20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአፋር ክልል ከህዳር 8 ጀምሮ እንደሚከበር የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አሲያ ከማል ገለፁ።

ሰመራ ፣ ሕዳር 5 ፣ 2018 (አፋ.ብ.መ.ድ )

20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአፋር ክልል ከህዳር 8 ጀምሮ በተለያዩ ህዝባዊ ክንዋኔዎች እንደሚከበር የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አሲያ ከማል ገለፁ።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አሲያ ከማል በዓሉን አስመልክተው እንደተናገሩት፤ በወረዳእና በዞን ደረጃ ከሴቶች ፤ ከወጣቶችና ከማህበረሰብ ጋር የተለያዩ ውይይቶች እንደሚደረጉም ገልፀዋል።

በመቀጠልም በክልል ደረጃ በስፖርታዊ ውድድና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን ማጠቃለያውን በህዳር 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ተናግረዋል ።

አፈጉባኤዋ አክለውም የዘንድሮው የብሄር በሄረሰቦች ቀን በዓል ለየት የሚያደርገው የህዳሴ ግድባችን የተጠናቀቀበት ዓመት መሆኑ በክልላችን ደግሞ የከተሞ ፎረም በተጠናቀቀበት እና የምዕራፍ አንድ የኮሪደር ልማቶቻችንን ለህዝባችን ምቹ በሆነ መልኩ ባጠናቀቅንበት ወቅት መሆኑ ልዩና ደማቅ እንደሚያደርገው በመግለጫቸው ተናግረዋል።

"ዴሞክራሲያዊ መግባባት-ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይከበራል።

በተጨማሪም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሠረታዊ ዕውቀቶችን በሚያስጨብጡ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች እንደሚከበርም ነው አፈ ጉባኤዋ የተናገሩት።

በመጨረሻም ዴሞክራሲያዊ መግባባት-ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ 20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን እንደ ሀገር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሚከበረው የብሄሮች ብሄረሰቦች በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

አፋር ቲቪ

10/11/2025

Address

Awash

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Youth Sound Of Awash Fanti Qale posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share