16/10/2025
👉በጋሞ ልማት ማህበር ገረሴ ቅርንጫፍ የ2018 ዓ.ም የአርሶ አደር አባላት መዋጮ ለመሰብሰብ የንቅናቄ መድረክ ከገረሴ ከገረሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ተካሄደ (ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ገረሴ)
👉በዛሬው ዕለት ማለት በቀን 5/2/2018 ዓ.ም የጋሞ ልማት ማህበር ገረሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የአርሶ አደር አባላት መዋጮ ለመሰብሰብ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። መድረኩ የተካሄደው ከገረሴ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን የገቢዎች ጽ/ቤትም የ2018 የመሬት ግብር በሚሰበስብበት እግረ መንገድ የልማት ማህበሩ መዋጮ እንዲሰበሰብ ለማድረግ ነው።
👉 የጋሞ ልማት ማህበር የገረሴ ቅርጫፍ ሥራ አስኪያጁ አቶ ሳሲዮስ ሻርቶ በመድረኩ እንዳስታወቁት ከ2 ሽህ 95 አባል አርሶ አደሮች የ2018 ዓ.ም መዋጮ 104,750 ብር (አንድ መቶ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ) ብር ለማሰባሰብ ማቀዱን አስታውቋል። በእግረ መንገዱም ለተጀመረው ለገረሴ መካከለኛ ደረጃ ግንባታ 2ዙር ድጋፍ ከአንድ ግብር ከፋይ 100 ብር ከጠቅላላው ከ2,095 አርሶ አደር 209,500 (ሁለት መቶ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ) ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም ገልፀዋል።
👉መድረኩን የመሩት የገረሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኤርሚያስ ጋሞ ልማት ማህበር ጉዳይ ማለት የማንነታችን ጉዳይ በመሆኑና እኛ ለእኛው የሚንሰራ የእኛው ማህበር በመሆኑ ሁሉም አርሶ አደር ጊዜ ሳይሰጥ የአባልነቱን መዋጮ መክፈል፣ የሞዴል ት/ቤት ግንባታ ድጋፉንም ሳያንጠባጥብ መክፈል እንዳለበትና ይህም እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ መጠናቀቅ እንዳለበት አበክረው ገልፀዋል።
👉የጋሞ ልማት ማህበር ገረሴ ቅርንጫፍ ስለ ትብብሩ የገረሴ ከተማ አስተዳደርን እያመሰገነ አርሶ አደር አባላቱ በተባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ መዋጮውን በማጠናቀቅ የልማት አጋርነታቸውን እንዲገልፁ ጥሪ ያስተላልፋል።
ቅድሚያ ለጋራ ልማት!