Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት, Community Organization, Arbaminch, Arba Minch'.
(1)

Gamo Development Association is legally registered indigenous Charity Association
striving to change the lives of its people through holistic and integrated development interventions

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ  ቅዳሜ  እና ዕሁድ (ሚያዚያ 17 እና 18/2018 የስጋ ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑን በታላቅ ትህትና ይገልጻል።1 ኪሎ ስጋ ዋጋ 1,500 ብር መ...
24/04/2026

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ቅዳሜ እና ዕሁድ (ሚያዚያ 17 እና 18/2018 የስጋ ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑን በታላቅ ትህትና ይገልጻል።
1 ኪሎ ስጋ ዋጋ 1,500 ብር መሆኑን እናሳውቃለን።

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ እንኳን ለ2018 ዓ/ም የፋሲካ በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓሉ የስጋ ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑን በታላቅ ትህትና ይገልጻል።1 ኪሎ ስጋ ዋ...
11/04/2026

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ እንኳን ለ2018 ዓ/ም የፋሲካ በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓሉ የስጋ ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑን በታላቅ ትህትና ይገልጻል።
1 ኪሎ ስጋ ዋጋ 1,500 ብር መሆኑን እናሳውቃለን።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ የ2018 ዓ/ም የ8 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ አርባምንጭ፣መጋቢት 20/2018 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን) ጋሞ ልማት...
29/03/2026

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ የ2018 ዓ/ም የ8 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

አርባምንጭ፣መጋቢት 20/2018 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ የ2018 ዓ/ም የ8 ወራት የስራ አፈጻጸም ለቅርንጫፉ ስራ አስፈፃሚዎች ቀርቦ ግምገማ ተካሂዷል።

በመድረኩ ለቅርንጫፉ ሥራ አስፈጻሚዎች የ8 ወር ሪፖርት ያቀረቡት የጋሞ ልማት ማህበር የአርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘርይሁን ዘንባ ሲሆን አባላትን የማፍራት ስራ፣ ገቢ አሰባሰብ፣ የፕሮግራም ስራዎች ሪፖርት፣ ገቢና ወጪ የሚያሳይ ሪፖርት፣ የገቢ ማመንጫ ስራዎችን የያዜ ሪፖርት አቅርቧል።

በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሥራዎች ክፍተት እንዳይታይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።

እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን ቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ስራዎች በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የቅርንጫፉ የበላይ ጠባቂና የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ የቀረበውን ሪፖርት በጥልቀት ገምግመው ቀጣይ ትኩረት መሠጠት ባለባቸው ቁልፍ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ በማስቀመጥ ቅርንጫፉን በማገዝ በከተማው በርካታ ልማቶች መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።

በመጨረሻም ተጠሪነቱ ለከንቲባው የሆነ 12 አባላት ያሉት የጋልማ አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ስራ አስፈጻሚዎች ተቋማዊ አስተዋጽኦቸውን ከግንዛቤ በማስገባት የተመረጡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አቶ ገዳሙ ሻንበል ሰብሳቢ፣አቶ ትግሉ ሀይሌ ም/ሰብሳቢ፣አቶ ማዶ መንገሻ ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።

በመድረኩ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባና የቅርንጫፉ የበላይ ጠባቂ መስፍን መንዛ( ዶ/ር ) ፣የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘርይሁን ዛንባ እና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል፡፡

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ ከ18 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በከተማው ያስገነባቸውን 3(ሶስት)  የማህበረሰብ ፋርማሲ እና ቢሮ ግ...
26/03/2026

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ ከ18 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በከተማው ያስገነባቸውን 3(ሶስት) የማህበረሰብ ፋርማሲ እና ቢሮ ግንባታ ከፍተኛ የክልል፣ የከተማ አመራሮች በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል

‎አርባምንጭ፡ መጋቢት 17/2018 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)

‎በዛሬው እለት እየተመረቀ የሚገኘው የማህበረሰብ ፋርማሲ የህብረተሰቡን ፍትሃዊ የአገልግሎት ተደራሽነት ባስጠበቀ መልኩ የተገነባ ሲሆን በዶ/ር አመኑ መታሰቢያ ሆስፒታል በር ፣ ድል ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና በኦሞ አዳራሽ በር ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

‎የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል እየተደረገ ባለው ጥረትና ርብርብ ልማት ማህበር እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።

‎በመርሃግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛን ጨምሮ የዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አድማሱ፣ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ፣ የከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አቶ ሽመልስ ታደሰ፣የከተማው ከፈተኛ ፍ/ቤት አቶ ኡፋይሳ ኡርዳ፣የከተማው ም/ከንቲባ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ፣ የከተማው ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ዛምባ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥትና የፓርቲ ኃላፊዎች ታድመዋል።

‎በሠላማዊት ደረሰ

የጋሞ ልማት ማህበር በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን በማበረታት የልማት አጋርንቱን ገለፀ***********አርባ ምንጭ፣ መጋቢት 14/2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒ...
24/03/2026

የጋሞ ልማት ማህበር በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን በማበረታት የልማት አጋርንቱን ገለፀ
***********
አርባ ምንጭ፣ መጋቢት 14/2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በኖክ ሳይት በአዲስ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እያቀላጠፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ምሽቱን የፍቅር ማዕድ አጋርቷል።

በምሽቱ የእራት ፕሮግራምና የአብሮነት ቆይታ ላይ የታደሙት የከተማው ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛና ሌሎች የከተማው ስራ አስፈፃሚዎች ሠራተኛው አበረታተዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ዛንባ በበኩላቸው የእራት ግብዣ መርሃግብሩ የጋራ ልማታችንን በሕብረት ሆነን በመተጋገዝ እንደምንጨርስ ያለንን አቋም ለመግለፅና ለሰራተኛው የሞራል አቅም እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

የሕዝቡ ድጋፍ ለሰራተኛው የሞራል ብርታት በመሆኑ ልማት ማህበሩ ለፕሮጀክቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት እገዛውን ይቀጥላልም ብለዋል።

የአባያ ክ/ከተማ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው ካሳሁን በበኩላቸው የአንድነትና የመተባባር መገለጫ የሆነው አዳሱ የኮሪደር ልማት ሥራ ከሕዝቡና ከተለያዩ ተቋማት የሚሰጠው ጠንካራ ድጋፍ ፕሮጀክቱን እያቀላጠፈ ይገኛል ብለዋል።

የጋሞ ልማት ማህበርም የፕሮጀክቱ ሥራ እንዲቀላጠፍ ታላቅ የሞራል ድጋፍ በተደጋጋሚ እየሰጠ እንደሚገኝ አውስተው ማህበሩ ለሰራተኛው ያዘጋጀው የእራት ግብዣም የሞራል አቅም እንደሚሆነው ገልፀው የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በአዲስ ምዕራፍ የተጀመረው የከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራ በ12 ሎቶች የተከፈለ ሲሆን በኖክ ፕሮጀክት ሳይት ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ ዳር ልማት ሥራ ጨምሮ የተለያዩ የስፖርት ሜዳዎች፣ ግዙፍ የገበያ ማዕከልና የሕፃናት መጫዎቻ ማዕከል ግንባታ ተካተውበታል።

በጌታ ፈቀደ

ጋሞ ልማት ማህበር በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ~~~በዞናችን በተከሰተው ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖ...
15/03/2026

ጋሞ ልማት ማህበር በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ
~~~
በዞናችን በተከሰተው ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን የጋሞ ልማት ማህበር ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚጠጋ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንድፍሮት ዱባለ እና የማህበሩ ምክትል ሥራ አስፈፃሚዎች በአካል ተገኝተው ለተጎጂዎች በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ አስረክበዋል። ከድጋፉ ባሻገር የማህበሩ አመራሮች ተጎጂዎችን በመጎብኘት አጽናንተው ከደረሰባቸው አደጋ በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንድፍሮት ዱባለ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ የማህበሩ ዋና ዓላማ የጋሞ ህዝብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማጠናከር፣ በአደጋ ጊዜ ለተጎዱ ወገኖች ፈጣን የሰብአዊ ድጋፍ መስጠት፣ እና በህዝቡ መካከል አንድነትና መተባበርን ማጎልበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ይህ የተሰጠው ድጋፍ ማህበሩ በአስቸጋሪ ጊዜ ከህዝቡ ጎን መቆም እንደሚገባ የሚያሳይ ተግባራዊ ምሳሌ መሆኑን ገልፀው፤ ማህበራችን ወገኖቻችን በችግር ጊዜ ብቻቸውን እንዳይሆኑ ሁልጊዜ ከጎናቸው ይቆማል ብለዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ የበጎ አድራጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሳጳ ዋና ቢሮ ከቅርጫፎች ጋር በመተባበር የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ያስረዱት የመሬት መንሸራተትና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቀነስ የአካባቢ ጥበቃ፣ የደን ልማት እና የመሬት አጠቃቀም ግንዛቤን ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም፣ ማህበሩ በዚህ ዘርፍ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር የተለያዩ የግንዛቤና የልማት ስራዎችን ለማከናወን እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በመጨረሻም ማህበሩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለድጋፍ በተከፈተው የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት የኢትዮጵያ ብቻ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር CBE፦ 1000321312865 ግቢ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል::

አካባቢው ነዋሪዎችም ማህበሩ በአስቸጋሪ ወቅት ከጎናቸው በመቆሙ ከፍተኛ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

መጋቢት 6/2018 ዓ/ም

ጋሞ ልማት ማህበር በአርባምንጭ ከተማ ሲቀላ ክ/ከተማ በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የእራት አቅርቦት መርሃግብር አካሄደየተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም በመሠረታዊነት መንግስት ...
11/03/2026

ጋሞ ልማት ማህበር በአርባምንጭ ከተማ ሲቀላ ክ/ከተማ በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የእራት አቅርቦት መርሃግብር አካሄደ

የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም በመሠረታዊነት መንግስት እያደረገ የሚገኘውን ጥረት በይበልጥ ለመደገፍ ማህበሩ በተለያዩ ዘርፎች አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጀቱን የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስ/አስፈጻሚ ተወካይ እና የፕሮግራም እና ፕላን ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አለምሰገድ ሉቃስ ገልጸዋል።

ከጋሞ ልማት ማህበር የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ በተፈጥሮ አደጋ ተጎጂዎችን ድጋፍ ማድረግ መሆኑን የገለጹት አቶ አለምሰገድ ከዚህ ቀደም በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች፤ በጎፋ ዞን፣ በኮንሶ፣ በወላይታ ዞን እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች በደረሱ ተፈጥሮዊ አደጋዎች ማህበሩ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል::

አቶ አለምሰገድ መንግስት ለተፈናቃዮች እያደረገ ላለው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: ይህንንም ለመደገፍ በዛሬው ዕለት የእራት አቅርቦት መርሃግብር መካሄዱን ገልጸዋል::

የጋልማ ዋናዉ መ/ቤት ም/ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ማኔጅመንቱ፣ የሲቀላ ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የአርባምንጭ ከተማ ጋልማ ስራ አስኪያጅ በርሃግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
2/6/2018

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በከተማው የኮሪደር ልማት ግንባታ ላይ ላሉ ሰራተኞች የእራት ግብዣ አደረገ። የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በከተማው የኮሪደር ልማት ግንባታ...
06/03/2026

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በከተማው የኮሪደር ልማት ግንባታ ላይ ላሉ ሰራተኞች የእራት ግብዣ አደረገ።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በከተማው የኮሪደር ልማት ግንባታ ላይ ላሉ ሰራተኞች የእራት ግብዣ አድርጓል።

የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ከተማዋን ከአፍሪካ ካሉ10 የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች መካከል በቀዳሚነት የምትጠራና ተመራጭ የቱሪስት ማዕከል እንዲሁም ስሉጥ ከተማ እንድትሆን የተያዘን ራዕይ እውን የሚያደርግ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ሥራአስኪያጅ አቶ ዘርይሁን ዘንባ ኮሪደር ልማት በከተማ ቀንና ማታ ሳይቋረጥ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረው ልማት ማህበሩ በከተማው የሚሰራውን ማንኛውም ልማት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

እራት ግብዣው ኮሪደር ልማት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ለማበረታታትና ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድጠናቀቅ ለማድረግ የታሰበ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከተማዋ ማራኪ፣ፅዱና ምቹ እንድትሆን አዲስ የሥራ ባህልን የቀየረው የአርባምንጭ ከተማ ኮሪደር ሥራ የጋራችን ነውና ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ በቦታው ተገኝተው ሰራተኞቹን አበረታተው የከተማው ሕብረተሰብ፤የንግዱ ማህበረሰብ፣አልሚ ባለሀብቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች በየአደረጃጀቱ እጅ ለእጅ በመያያዝ በግዙፉ የፕሮጀክት ሥራ ላይ ከራስ ትብብር ጀምሮ የጋራ አሻቸራውን ማኖር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአርባምንጭ ከነማ ታዳጊ ቡድን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለ...
28/02/2026

ጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአርባምንጭ ከነማ ታዳጊ ቡድን የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ ለታዳጊ ቡድናችን ለቡድኑ አባለት በሙሉ ማሊያ ፣ለአሰልጣኝ ቡድን አባላት ሙሉ ቱታ ትጥቅ እና የኳስ ድጋፍ አደረገ ።

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የክለባችን የደጋፊ ማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ዘንባ ጋሞ ልማት ማህበር በተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች ድጋፎችን እያደረገ ያለ አንጋፋ ማህበር መሆኑን አንስተው ታዳጊዎች የነገ ተስፋዎች በመሆናቸው ድጋፉ ትልቅ ደረጃ እንድደረሱ የሚያግዛቸው መሆኑን ተናግረዋል ።

አርባምንጭ ከተማ የበርካታ እግርኳስ ጥበበኞች የሚፈልቁባት ከተማ በመሆኗ የታዳጊ ቡድን አባላትም ትልቅ ቦታ ለመድረስ ጠንክረው መሰራት እንዳለባቸው አቶ ዘሪሁን ዘንባ አሳስበዋል ።

በድጋፍ በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ትግሉ ኃይሌ እና የደጋፊ ማህበሩ የበላይ ጠባቂ የሆኑት አቶ አየነው ውበቴ ትልቅ ደረጃ ለመድረሰ ትልቅ ራዕይ ልኖራቸው እንደሚገባ ተናግረው የቡድኑ አሰልጣኞች ከሚሰጠው ልምምድ በተጨማሪ እራሳቸውን በግልም እየሰሩ ጠንካራ መሆን እንድሚገባቸው አሳስበዋል ።

አክለውም አቶ ትግሉ ኃይሌ እና አቶ አየነው ውበቴ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም መብቃት የሚችሉ የኳስ ጥበበኞችን የምትፈራ በመሆኑ የዋናውን ቡድን ለመወከል ብቻ ሳይሆን ከዛም አልፎ ለመሄድ ዛሬ ላይ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል ።

በመጨረሻም የአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ ከ20 በታች ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጌትነት ቡታቆ ለተደረገላቸው የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አመስግነው የቡድኑ አባላት በውጤት ለመካስ ያላቸውን ሁሉ መሰጠት ይገባቸዋል ብለዋል።

የካቲት 21/2018ዓ/ም
ቅድሚያ ለጋራ ልማት!

26/02/2026
‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጪ ዘመናዊ የፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ250 ...
25/02/2026

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጪ ዘመናዊ የፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጪ ለአርባምንጭ ከተማ ኩልፎ አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤት ዘመናዊ የፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮምፒውተር ድጋፍ አድርጓል።

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ዛንባ ተቋሙ በትምህርት፣ በጤና፣ በመሰረተ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ በርካታ ተግባራት እየተሰሩ መሆኑን አንስተው ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተቋማት በመገንባት፣ የጎደሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላትና የኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ተማሪዎችን የማስተማርና የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የማድረግ ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ አስረድተዋል።

በየአመቱ በጳጉሜ ለትውልድ ዘመቻ በሚያደርጉት የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለ6500 ተማሪዎች ደጋፍ ማድረጋቸውንም አብራርተዋል።

‎በዛሬው እለትም የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ጋር ባደረጉት የመስክ ምልከታና አቅጣጫ መሰረት ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ፕሪንተር ስካነ የሚያደርግ ዘመናዊ የኮፒ ማሽን፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተርና የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው በሁሉም ዘርፍ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዶ መንገሻ ከለውጡ ወዲህ በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ ስራዎች የከተማው እድገት እንዳሳለጡ ተናግረው ተደራሽነቱን ለማስፋት ባለሙ አካባቢዎች ትኩረት በመስጠት በርካታ የልማት ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

መንግስት በማህበራዊ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ ትምህርት መሆኑን ጠቁመው እንደሀገር የገጠመንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል።

ልማት ማህበሩ በተለያዩ ዘርፎች ከመንግስት ጎን በመሆን በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑ የሚደቅ ያሉት ኃላፊው ለትምህርት ዘርፉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ የሚበረታታ ነውም ብለዋል።

‎የከተማው ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አቶ አብርሃም አምሳሉ ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትምህርት በመስጠት በከተማው ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ የሚመራው ልዑክ ትምህርት ቤቶች ያሉበት ደረጃ ወርዶ የመስክ ምልከታ በማድረግ ችግሮችን ለይቶ ግብዓት ከማሟላት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ልማት ማህበሩ የህብረተሰቡ የልማት አይን በመሆን የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ በቅንጅት በመከታተል እያደረገ ላለው ድጋፍና አጋርነት አመስግነዋል።

ትምህርት ቤቱ ያለበትን ችግር ወርዶ መደገፍ፣ መከታተልና መፍትሔ መስጠት ለዜጎች ማሰብ ነው ያሉት የኩልፎ አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ኡሸቾ ኡዳ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ አምራችና ውጤታማ ትውልድ ለመፍጠር በቅንጅት አፋጣኝ ምላሽ ለሰጡ ክቡር ከንቲባው እና ለከተማው ልማት ማህበሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በሠላማዊት ደረሰ

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በ524 ሺህ ብር ወጪ ለ400 ቤተሰቦች የጤና መድህን(ማጤመዐ) ድጋፍ አደረገ‎‎አርባ ምንጭ፣ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒ...
16/02/2026

የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በ524 ሺህ ብር ወጪ ለ400 ቤተሰቦች የጤና መድህን(ማጤመዐ) ድጋፍ አደረገ

‎አርባ ምንጭ፣ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦

‎የጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ቅርንጫፍ በ524 ሺህ ብር ወጪ ለ400 ቤተሰቦች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን(ማጤመዐ) ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ መንግሥት አጠቃላይ ዜጋው ወደ ተቀራራቢ የኑሮ ደረጃ እንዲመጣ ህዝብን ያሳተፈና ያስተባበረ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራ ያለ ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑን ተናግረው በአንድ ጀምበርና በመደበኛ የተሰሩ በርካታ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ፣ የማዕድ ማጋራትና ድንበር ተሻጋሪ ድጋፍ ስራዎች ለአብነት ማሳያ መሆናቸውን አስረድተዋል።

‎መንግስት እንደሀገር አካታችና አቀመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍልን ታሳቢ ያደረገ የጤና ፖሊሲ ቀርፆ ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

‎ልማት ማህበሩ በከተማው በተለያዩ ዘርፎች እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ከሚሰራቸው በርካታ ተግባራት አንዱ የጤና ዘርፍ እንደመሆኑ በጤና ተቋም ግንባታ፣ የቁሳቁስ ድጋፍ፣ በዝቅተኛ ዋጋ መድሃኒት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ከመድሃኒት ቤቶች ግንባታ በተጨማሪ ገንዘብ ከፍለው መታከም ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረገው የጤና መድህን ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በጋሞ ልማት ማህበር አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ዛምባ እንዳሉት ልማት ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ የራሱን አቅም በማደራጀት በትምህርት፣ በጤና፣ በንጹህ ውሃ መጠጥና በሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንዳለ አውስተው ተቋማትን በመገንባት፣ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ በማድረግ በቅናሽ ዋጋ መድሃኒት ለማቅረብ በጤና ዘርፍ ህብረተሰቡን ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

‎ከዚህ ቀደም ለህክምና አገልግሎት መክፈል ስለማይችሉ ለተለያዩ ለ200 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ወጪ በመሸፈን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጋቸውን ተናግረው ዛሬ ለነባሮች እድሳትና ተጨማሪ አዲስ ለ200 ቤተሰቦች የጤና መድህን ሽፋን በመስጠት በ2018 ዓ፣ም በ524 ሺህ ብር ወጪ ለ400 ቤተሰቦች የጤና መድህን(ማጠመዐ) ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል፡፡

‎የከተማው ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አንተነህ ካሳዬ መንግስት በሁሉም ዘርፍ የህብረተሰቡን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራው በመደገፍ ልማት ማህበሩ በሁሉም ዘርፍ ቅድሚያ ለጋራ ልማት ብሎ እየሰራ ያለው ሰው ተኮር ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው

‎መንግሥት እንደ ሀገር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍ ተግባራዊ ባደረገው የጤና መድህን(ማጠመዐ) አገልግሎት ዜጎች ቀድመው በሚከፍሉት መዋጮ አመቱን ሙሉ የሚታከሙበት ስርዓት እንደሆነ ተናግረው በገንዘብ እጥረት ጤናቸውን መጠበቅ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቀድመው በሚከፍሉት መዋጮ አመቱን ሙሉ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የጤና መድህን ሽፋን ድጋፍ ያደረጉ አካላት አመስግነዋል።

የጤና መድህን አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ የተናገሩት ኃላፊው አዲስ አባል ምዝገባና እድሳት የሚያደርጉ አካላት በ3(በሶስት) ተከታታይ ሳምንት ውስጥ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ‎ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የበጎ አድራጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ሳጳ ‎ልማት ማህበሩ ህብረተሰቡን በማስተባበር አባል ያልሆኑትን አባል እያደረገና የገቢ ምንጮችን ለይተው በመሥራት የተሻለ አቅም እየፈጠረ እንዳለ ገልጸው ቀጣይ ላይ የተሻለ አቅም ፈጥሮ በርካታ ድጋፎችን እንዲያደርግ አባል ያልሆኑ ሰዎች አባል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በመርሃግብሩ የአርባምንጭ ከተማ ም/ከንቲባና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያን ጨምሮ፣ የጤና መምሪያ ኃላፊ፣ የጋሞ ልማት አርባምንጭ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ፣ የጋሞ ልማትማህበር ስራ አስፈፃሚዎችና የጤና መምሪያ ማኔጅመንት አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

‎በሠላማዊት ደረሰ

Address

Arbaminch
Arba Minch'
20

Telephone

+251926446250

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Development Association Arbaminch Branch/ጋልማ አርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት:

Share