ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association

ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር በሚቶ ወረዳ ከሚገኙ ማህበረሰብና ከሌሎች አጋር አካላት በሚያገኘው ድጋፍ አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው !!

ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር  ከ30 በላይ ለሚሆኑ ለአቅመ ደካሞች የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የማድ ማጋራት መርሐግብር አካሄደ፡፡የካቲት 13/2018ዓ.ም  ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህ...
20/02/2026

ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ30 በላይ ለሚሆኑ ለአቅመ ደካሞች የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የማድ ማጋራት መርሐግብር አካሄደ፡፡

የካቲት 13/2018ዓ.ም
ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ30 በላይ ለአቅመ ደካሞች የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የቦቆላ፣ክክ እና ዘይት ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፉ ወቅት የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር መሀመድ ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዲ ዋበላ፣ምክትል አስተዳደር እና የፋይናንስ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጃ ቆርቻ ፣ የወረዳዉ አመራሮች እና የሰዉኛ በጎ አድራጎት ማህበር
አስተባባሪዎች ተገኝተዋል ።
የረመዳን ወር የመተዛዘን፣ የመረዳዳት እና የደስታ ወር ነው። ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር ይህንን ታላቅ ወር ምክንያት በማድረግ፣ አቅመ ደካሞች በሰላም እና በደስታ እንዲጾሙ ለማስቻል ሲያከናውን የቆየውን የአስቤዛ ማሰባሰብ እና ማሰራጨት መርሃ-ግብር በስኬት አጠናቋል።
ባለፉት ቀናት ባደረግነው ከፍተኛ ጥረት፦ እጅግ ችግረኛ ለሆኑ ምስኪን ወገኖቻችን መድረስ ተችሏል። የተከፋፈለው አስቤዛ፦ በቆሎ፣ ዘይት እና የሾርባ ክክ መሰረታዊ የምግብ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።ዛሬ እነዚህ ወገኖቻችን የረመዳን ወር ሲገባ "ምን አፍጥሬ አነጋለሁ?" የሚለው ጭንቀታቸው ተወግዶ በፊታቸው ላይ የታየው ፈገግታ የሁላችንም ኩራት ነው። ይህ ትልቅ ስኬት ያለ እናንተ የልግስና እጅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነበር።
ምስጋና ለእናንተ!
በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጪ ሆናቹ በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ፣ በሃሳባችሁ እንዲሁም ይህ ጥሪ ለብዙዎች እንዲደርስ በማድረግ አብራችሁን ለቆማችሁ ውድ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ፈጣሪ በረከቱን በቤታችሁ ያፍስሰው!
የሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር ጉዞ ይቀጥላል። ወደፊትም ከጎናችን በመሆን የበጎነት አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በጋራ በመሆን የሰዎችን ህይወት መለወጥ እንችላለን!
ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር
ሰዉኛ በጎ:- 1000406998529
ስልክ:- +251928714254
+251939841090
+251919572573

20/02/2026
  በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጪ ያላቹ የሚቶ ወረዳ ተወላጆች በሙሉ  እንደሚታወቀዉ  #ረመዳን ሊገባ  በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተዉታል ሆኖም ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር  በረመዳን ወር...
12/02/2026

በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጪ ያላቹ የሚቶ ወረዳ ተወላጆች በሙሉ እንደሚታወቀዉ #ረመዳን ሊገባ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተዉታል ሆኖም ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር በረመዳን ወር ለሚቸገሩ ጧሪ ለሌላቸዉ ለየቲሞች እና ለሚስኪኖች የሚዉል የረመዳን ፓኬጅ በሚል መሪ ቃል የሞባይል ቻሌንጅ መጀመሩ ይታወቃል ስለዚህ እናንተም ቻሌንጁን እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እነጠይቃለን🙏🙏🙏

ድጋፍ ለማድረግ 👉1000406998529
ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር

የረመዳን የምስኪኖች ሰደቃ የሰውኛ አስተባባሪ  የሆነው ወንድማችን የሱፍ አህመድ በይፋ ጀምሮታል
08/02/2026

የረመዳን የምስኪኖች ሰደቃ የሰውኛ አስተባባሪ የሆነው ወንድማችን የሱፍ አህመድ በይፋ ጀምሮታል

 #የተከበረዉ የረመዳን ወር   ....                                 የተከበረዉን  የረመዳንን ወር ልንቀበለው ከ10 ቀናቶች  ያነሱ  ቀርተዉታል  ይሄንን የተባረከ  ወር...
08/02/2026

#የተከበረዉ የረመዳን ወር ....
የተከበረዉን የረመዳንን ወር ልንቀበለው ከ10 ቀናቶች ያነሱ ቀርተዉታል ይሄንን የተባረከ ወር ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅት ያስፍልጋል ይህ የተባረከ የረመዳን ወር ከሌሎች ወራቶች ለየት የሚያደርገዉ ኸይር ስራዎች በብዙ እጥፍ መባዛታቸዉ ነዉ ብዙ ኸይሮችን ይዞልን እየመጣ ነው እኛስ ለረመዳን ለአቅመ ደካማ ምስኪኖች ምን አሰብን በዚህ በተባረከ ወር ምንዳ ለመሰብሰብ ምን ያህል ዝግጁ ነን

የረመዳን ወር ሲመጣ ብዙ ሚስኪኖች፣ የቲሞች እና አቅመ ደካሞች ለአፍጥር ይቸጋረሉ ፣በዓመት ዓመት ከእናንተ የለመዱትን ይጠብቃሉ በተለይ የኑሮ ውድነት እየተባበሰ ባለበት ወቅት ያለንን በመካፈል መረዳዳት አለብን ይሄው የእዝነት፣ የበረካ፣ የራህመት ወር ምስኪን፣ አቅመደካሞችን እና የቲሞችን በማስፈጠር የተለያዩ ኸይር ስራዎችን የምናበዛበት ሀጅር የምናገኝበት የተባረከው እንግዳው ወር እየመጣ ነውና ከወዲሁ በኸይር በመሳተፍ እንጠቀምበት

ሰዉኛ የበጎ አድራጎት ማህበር ለሚመጣው ታላቁ የረመዳን ወር ይቸገራሉ ፣ የሚያፈጥሩበትን ያጣሉ ፣ ላላቸው ብዙ የቲሞች እና ምስኪኖች የወር አስቤዛዎች ለመስጠት ለማስፈጠር የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም እርሶም እንደ አቅሞት እንዲሳተፋ ተጋብዛዋል ።

በሰዉኛ አድራጎት ማህበር አካውንት ገንዘብ ገቢ ማድረግ ለምትፈልጉ👇
ኢ.ን.ባ.ጣ.አ.ቁ፦1000406998529

#መልካም ስራችሁን አላህ ይቀበላችሁ

 -ትባላለች  በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ነዋሪ ስትሆን    በሽተኛ ናት የቀኝ ጡቷን ታማ ለረጅም ጊዜ ስትሰቃይ ኖራ በመጨረሻም አስቆርጣለች አሁላ ደሞ ወደ ግራው እየተዛመተባት እንደሆነና እተ...
08/12/2025

-ትባላለች በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ነዋሪ ስትሆን በሽተኛ ናት የቀኝ ጡቷን ታማ ለረጅም ጊዜ ስትሰቃይ ኖራ በመጨረሻም አስቆርጣለች አሁላ ደሞ ወደ ግራው እየተዛመተባት እንደሆነና እተሰቃየች መሆኑን በዘየርናት ጊዜ ተረድተናል።

በመሆኑም አሁን ላይ ወደ ግራ እተዛመተ ስለሆነም በጨረር መመታት ስላበት ለህክምናው የተጠየቀችው እስከ 200,000 ሺ ብር በመሆኑ ከአቅሟዋ በላይ በመሆኑ መታከም አለመቻሉዋን አሳውቃናለች እናም የ1ወር ህፃን ልጅ ደሞ ይዛ ነው የምትታገለው በተጨማሪም ለልጁ ወተት እንጂ የተቀረውን ጡት እንዳታጠበው በህክምናው ወክት ተከልክላላች።

ራዲያ ሁልሼ ከመታመሟ በፊት ጀግናና ጠንካራ እናት ነበረች አሁን ላይ ግን በበሽታ ተይዛ ቤቷ ላይ የሚላስ የሚቀመስ ነገር ባለመኖሩ የናተን እጅ ትጠባበቃለች.....🙏🙏🙏🙏 ሁለት ሂወትን እንታደግ አንድ ጡት እንዳይጠባ ተብሎ የተከለከለ #ህፃን ሌላኛዋ ደሞ ለህፃኑ የምታስፈልገው እናቱን እናድንለት ።

ያው በተቻላቹ አቅም ከ100 ብር ጀምራቹ አቅማቹ የፈቀደውን በራዲያ በሯሷ ስም የተከፈተ አካውንት አላት እንርዳት ነገ እኔስ እኛስ እናንተስ ምን እንደሚገጥመን በምን እናውቃለን ፈጣሪ አይፈትነን....🤲🤲

የኢትዮጲያ የንግድ ባንክ አካውንት
1000468830292
RADIYA HULSHA GUTAGO

ኢንሻላህ ነገ የሚቶ ወረዳ ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር 10,000 ሺህ ብር ለመስጠት ቃል ገብቶዋል አላህ ከይር ጀዛቹን ይክፈላቹ 🙏🙏

 !! በዛሬው ቀን እለት እሁድ 14/03/2018 ለረጅም ጊዜ ታማ የቆየችን እናታችን  #ወ/ሮ ዙልፋ ሀ/ሙዴን ለመዘየር ችለናል።እናት ዙልፋ ሀ/ሙዴ  ለረጅም ጊዜ በካንሰር በሽታ ታማ እግሩዋ...
23/11/2025

!!

በዛሬው ቀን እለት እሁድ 14/03/2018 ለረጅም ጊዜ ታማ የቆየችን እናታችን #ወ/ሮ ዙልፋ ሀ/ሙዴን ለመዘየር ችለናል።

እናት ዙልፋ ሀ/ሙዴ ለረጅም ጊዜ በካንሰር በሽታ ታማ እግሩዋ ተቆርጦ አልጋ ለይ መቆየቱዋን ቢታወቅም አሁንም ቢሆን ወደ ሌላ ሰውነቱዋ እተንሰራፋ ለከፍተኛ ህመም ስትዳረግ በየቀኑ ለመስተገሻ ተብሎ የሚወጣው ወጪ ከባድ በመሆኑ አሁን ላይ ከአቅም በላይ ሆኖባት ተስፋ መቁረጥ ለይ እንደደረሰች መሆኑን በዘየርናት ወቅት ለመረዳት ችለናል።

በመሆኑም ዛሬ እኛም ባካል በመገኘት በምንችለው ልክ ለህክምና የሚያግዛትን #10,000 ብር አስተውፅኦ አድርገንለታል።

ኑ! ወደ ሰውነት ከፍታ አብረን በጋራ እንውጣ🙏🙏🙏........................................................
👉ኢ.ን.ባ.ጣ.አ.ቁ፦1000406998529
👉ስ.ቁጥር፦ 0923894193
👉email ፦ [email protected]
👉Faceboሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association0367/?app=fbl
👉Telegram group link፦https://t.me/c/1570099187/354
👉WhatsApp group link፦https://chat.whatsapp.com/IdZwFUNbRL82IbWPBhgxL4

@ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር

 !!ዛሬ ማለትም 20/01/18 በየት/ቤቶች የኢኮኖሚ አቅም ችግር ኖሮባቸው ት/ቤት መምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች ደፍተር የማድረስ ስራ ሰርተናል።በዚህ ተግባርም ከጎናችን ሆናቹ በጎነታቹን ለምታሳ...
29/09/2025

!!

ዛሬ ማለትም 20/01/18 በየት/ቤቶች የኢኮኖሚ አቅም ችግር ኖሮባቸው ት/ቤት መምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች ደፍተር የማድረስ ስራ ሰርተናል።

በዚህ ተግባርም ከጎናችን ሆናቹ በጎነታቹን ለምታሳዩን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳሊ🙏🙏

ኑ! ወደ ሰውነት ከፍታ አብረን በጋራ እንውጣ🙏🙏🙏........................................................
👉ኢ.ን.ባ.ጣ.አ.ቁ፦1000406998529
👉ስ.ቁጥር፦ 0923894193
👉email ፦ [email protected]
👉Faceboሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association0367/?app=fbl
👉Telegram group link፦https://t.me/c/1570099187/354
👉WhatsApp group link፦https://chat.whatsapp.com/IdZwFUNbRL82IbWPBhgxL4

@ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር

  እናመሰግናለን 🙏🙏መስከረም 20/2018ዓ.ም የሚቶ ወረዳ የንግዱ ማህበረሰብ 1ደርዘን ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ቃል ሲያሰባስቡ የነበረው  የክረምት በጎ ተግባር 24 ደርዘን ደብተር ለሚቶ ...
29/09/2025

እናመሰግናለን 🙏🙏

መስከረም 20/2018ዓ.ም

የሚቶ ወረዳ የንግዱ ማህበረሰብ 1ደርዘን ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ቃል ሲያሰባስቡ የነበረው የክረምት በጎ ተግባር 24 ደርዘን ደብተር ለሚቶ ወረዳ ሰዉኛ በጎ አድራጎት ማህበር አስረክበዋል።

 !! ! በሚል መሪ ቃል ስናሰባስብ የነበረው ደፍተርና እስኪሪቢቶ በዛሬው እለት ማለት 09/01/2018 ለአቅመ ደካማና የቲም ልጆች አድርሰናል። ይህንን ተግባር እንዲሳካ ከልብ በመነጨ በጎነ...
19/09/2025

!!

! በሚል መሪ ቃል ስናሰባስብ የነበረው ደፍተርና እስኪሪቢቶ በዛሬው እለት ማለት 09/01/2018 ለአቅመ ደካማና የቲም ልጆች አድርሰናል። ይህንን ተግባር እንዲሳካ ከልብ በመነጨ በጎነት ስታስተባብሩ የነበራቹ የማህበሩ ግንበር ቀደም የሆናቹ :-



#አ/ቁዱስ_ደልባር
/ኑሪ
#አ/ረህማን_ራመቶ እነዲሁ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት በዋናነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በእግራቹ እየዞራቹ ያሰባሰበቹ ስለሆነ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!!🙏🙏

እንዲሁም ከራሳቸው በመጀመር ሲያስተባብሩ ለነበራቹ የወረዳ አስተባባሪዎች እና አመራሮች እንዲሁም የከተማችን ማህበረሰብ እና ነጋዴዎች እጅግ አድርገን እናመሰግናለን🙏🙏!!

በመቀጠል በዚህ መልካም ተግባር የተሰተፋቹሁ ሁሉ በማህበራችን ስም እጅግ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን 🙏🙏🙏!!

ኑ! ወደ ሰውነት ከፍታ አብረን በጋራ እንውጣ🙏🙏🙏........................................................
👉ኢ.ን.ባ.ጣ.አ.ቁ፦1000406998529
👉ስ.ቁጥር፦ 0923894193
👉email ፦ [email protected]
👉Faceboሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association0367/?app=fbl
👉Telegram group link፦https://t.me/c/1570099187/354
👉WhatsApp group link፦https://chat.whatsapp.com/IdZwFUNbRL82IbWPBhgxL4

@ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር

Address

Mitto
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ሰውኛ የበጎ አድራጎት ማህበር/Sewugna Charity Association:

Share