Talita - Rise Up

Talita - Rise Up Talita (Rise Up) is a non- governmental non-profit organization that strives to provide support for the poorest in society especially women and children.
(1)

Celebrating with Our Partners – Ordinary HeroThe second day of our Gena celebration was shared with our valued partners,...
08/01/2026

Celebrating with Our Partners – Ordinary Hero

The second day of our Gena celebration was shared with our valued partners, Ordinary Hero, who brought a team of about 30 people to celebrate with us. The day focused especially on the abandoned babies under our care, as the team spent time with them and generously provided essential items such as clothes, towels, shoes, formula milk, diapers, and more.

In addition, gifts were distributed to families: 20 adults, 20 teenagers, 35 young girls, and 20 children aged 3–6 received clothes, shoes, bags, and other necessities. One of our girls’ group programs also prepared a special presentation for the visiting team, featuring choreography and worship. The Ordinary Hero team then shared three songs with us, creating a beautiful moment of unity and joy.

Together, we also visited families in desperate need and made commitments to sponsor them, ensuring access to food, medical care, and education. It was a powerful and humbling day—full of love, generosity, and hope—and a true blessing for everyone involved, including our own team.

✨ We are thankful for all who celebrated with us and made this Gena a time of joy, compassion, and shared purpose.

ጣሊታ ራይዝ አፕ በጎ አድራጎት ድርጅት የገና በአልን አስመልክቶ የፍቅር ስጦታ አበረከተ።♦️ስጦታውን ያበረከተላቸው ወገኖች በይርጋ አለም ከተማ  ለሚገኙ ረዳት የለሽ አረጋውያን ፣ ወላጅ አጥ...
07/01/2026

ጣሊታ ራይዝ አፕ በጎ አድራጎት ድርጅት የገና በአልን አስመልክቶ የፍቅር ስጦታ አበረከተ።

♦️ስጦታውን ያበረከተላቸው ወገኖች በይርጋ አለም ከተማ ለሚገኙ ረዳት የለሽ አረጋውያን ፣ ወላጅ አጥና ለችግር ተጋላጭ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኛ ወገኖች እና በችግር ውስጥ ላሉ ተማሪ ሴቶች ሲሆን በጠቅላላው 160 ያህል ቤተሰብን መድረስ ችሏል።
👉የድርጅቱ ባለራዕይና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አትክልት እንደገለፁት ይህ ከድጋፍ አድራጊዎቻችን ጋር በመተባበር በየበአሉ ከምናደርገው ልገሳ አንዱ ነው ብለዋል።
♦️በፕሮግራሙ ላይ የይርጋለም ከተማ ከንቲባ ኢ/ር እምባቆም ጴጥሮስ፣ የከተማው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በየነች ቦጋለ፣ የከተማው የሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላም ደንጉራ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በክብር እንግድነት በመገኘት በአሉን በጋራ አክብረዋል።
👉 ለበአሉ አስፈላጊ የሆኑ የዶሮ ፣ እንቁላል ሽንኩርት እና ዘይት የተበረከተላቸው ሲሆን፥
♦️ ተጠቃሚዎችም አቅመ ደካማ መሆናቸውን ተመልክቶ በየጊዜው ስለሚያደርግላቸው ድጋፍ ድርጅቱን አመስግነዋል።

Merry Christmas!🎄We love you!❤️
24/12/2025

Merry Christmas!🎄
We love you!❤️


 #ጣሊታ ራይዝ አፕ  ተጎበኘ!በቀደሙት ጊዜያት በደቡብ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ቢሮ፣ ሴቶች  እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፣ በጤና ቢሮ በኃላፊነትና በብቃት የመሩ...
21/10/2025

#ጣሊታ ራይዝ አፕ ተጎበኘ!
በቀደሙት ጊዜያት በደቡብ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ቢሮ፣ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፣ በጤና ቢሮ በኃላፊነትና በብቃት የመሩ ፤በኃላም በአለም የምግብ ድርጅት ውስጥ የሥርዓተ ጾታ ባለሞያ ሆነው እያገለገሉ የቆዩ ልምድ ጠገቧ እና የስራ ሰው ወይዘሮ አማረች አግደው ፦
ዛሬ ድርጅታችንን በመጎብኘት ስላበረታቱንና በቀጣይም ያላቸውን ልምድና ዕውቀት በማካፈል የጣሊታን ስራዎች ለማገዝ ቃል ስለገቡልን ከልብ እናመሰግናለን🙏
👉በቀጣይም በጋራ ለተሻለ አገልግሎት እንደምንሰራ ዕምነታችን ነው።
Atikelt Janka, Amarech Agidew

የይርጋዓለም ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት  የ12 ዓመቷን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረውን  የ65 አመት አዛውንት በ23 ዓመት ከ6ወር ፅኑ እስራት ቀጣ።    👉 የይርጋዓለም ከተማ የመጀ...
14/10/2025

የይርጋዓለም ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ12 ዓመቷን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረውን የ65 አመት አዛውንት በ23 ዓመት ከ6ወር ፅኑ እስራት ቀጣ።

👉 የይርጋዓለም ከተማ የመጀመርያ ደረጀ ፍርድ ቤት
ነሃሴ 6/2017 ዓ/ም የ12 ዓመት ህፃን ልጅን ተልካ በሄደችበት ከመንገድ ለይ በመጎተት አስገድዶ ከደፈረ በዋላ ለማምለጥ ሲሞክር በፓሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር ሳያመልጥ ተይዞ ቆይቷል።
የይርጋ ዓለም ከተማ ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ከፍል በሰው ማስረጃና በሰነድ መረጃ ሲያጣራ ቆይቶ መዝገቡን ለ አቃቤ ህግ በማስተላለፍ የይርጋዓለም ከተማ አቃቤ ህግ ቢሮ መዝገቡን አጣርቶ በመመርምር ለችሎት ካቀረበ በዋላ ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።
👉 ተከሳሹ የተከሰሰው በሁለት ክስ ሲሆን አስገደዶ በመድፈር በ 15 ዓመት እና ኤች አይቪ እንዳለበትና ላለፉት 14 አመት መድሃኒት እየተጠቀመ መቆየቱን በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ ተላላፊ በሽታ እንዳለበት እያወቀ ለፈጸመው ወንጀል ደግሞ 8 ዓመት ከ 6 ወር በድምሩ በ23 ዓመት ከ6 ወር በኢትዮጽያ ወንጀል መቅጫ ህግ መሰረት በአንቀፅ 627/1/እና 628/1 መሰረት ውሳኔ ተሰጥቷል።
👉 ህፃኗ ከደረሰባት ጥቃት በኃላ የነበረባትን አካላዊና ስነ ልቦቦናዊ ጉዳት ለማገገም ከቆየችበት ጣሊታ ራይዝ አፕ በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በመቆየት የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል ።
👉 ስለጤናዋ ሁኔታም በመጀመሪያ ምርመራ ከኤች አይቪ ነጻ መባሏንም ጠቅሰው እርግጠኛ ለመሆን ከ3ወር በኃላ በድጋሚ የሚደረገውን የምርመራ ውጤት እየጠበቁ መሆኑን በተጨማሪ ለማወቅ ተችሏል።
🙏 ምንም እንኳን ከህፃኗ ዕድሜ፣ እና ከደረሰባት አካላዊ ፣ ስነልቦናዊና የጤና ጉዳት አንፃር የተሰጠው ፍርድ የሚነፃፀር ባይሆንም፤ የጥቃት አድራሹን ዕድሜ ከግምት በማስገባት እንዲሁም ወንጀለኛውን ይዞ በአጭር ጊዜ ፍትህ መሰጠቱ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ልብ ይሏል።

እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ። ጣሊታ ራይዝ አፕ እንደ ሁልጉዜው መልካም በአል ይመኝላችኋል!!🎉🌼🌼✝️✝️
27/09/2025

እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ። ጣሊታ ራይዝ አፕ እንደ ሁልጉዜው መልካም በአል ይመኝላችኋል!!🎉🌼🌼✝️✝️

የአዲስ አመት🌻 አዲስና ውድ ስጦታ🌞ለልባሞቹ ከጣሊታ🌹♦️ ልጅ አንድም ከአብራክ አንድም ከልብ በፍቅር ይወለዳል።♦️ ልጅ ባለመውለድ ምክንያት ወላጅ አለመሆን አይቻልም♦️ ምክንያቱም ልጅን ከል...
24/09/2025

የአዲስ አመት🌻
አዲስና ውድ ስጦታ🌞
ለልባሞቹ ከጣሊታ🌹
♦️ ልጅ አንድም ከአብራክ አንድም ከልብ በፍቅር ይወለዳል።
♦️ ልጅ ባለመውለድ ምክንያት ወላጅ አለመሆን አይቻልም
♦️ ምክንያቱም ልጅን ከልብ መውለድ ይቻላልና
🙏 ጣሊታ ራይዝ አፕ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ይርጋለም ከቀናት ዕድሜ ጀምሮ በወራትና እስከ 2 አመት ያሉ ህፃናትን በህጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ተቀብላችሁ የልጅ ፍቅርንና ወላጅነትን እንድታጣጥሙ በፍቅር ይጋብዛል።
ለተጨማሪ መረጃ፦
0922 17 48 46/0926998384 ይደውሉ
ልጅን ከልብዎ ይውለዱ❤🌻🌞🌹

Panelists Taking Questions and Responding for Way Forward. Director Atikilt Janka was the Lead Panelist and Moderator in...
21/09/2025

Panelists Taking Questions and Responding for Way Forward.
Director Atikilt Janka was the Lead Panelist and Moderator in the Event
and Responding for Questions & Encouraging and Enhancing the Action Group for Gender-Based Violence to Do What is Expected of Each Institution and Key Figures.

Talita Rise Up proudly took part in the closing ceremony of our partner’s 7-month Safe House Legal Aid Project on Enhanc...
21/09/2025

Talita Rise Up proudly took part in the closing ceremony of our partner’s 7-month Safe House Legal Aid Project on Enhancing Access to Justice for Gender-Based Violence Survivors through multi-sectoral discussions and platforms.

From the very beginning, Talita Rise Up has been actively involved — monitoring and supervising the project, taking part in Safe House trainings, and raising critical gaps we have witnessed in services in collaboration with police, prosecutors, judges, and the One-Stop Center.

The closing event was deeply engaging, truth-seeking, and survivor-centered. It also strengthened the Action Group that Talita Rise Up initiated through advocacy and promotion — a network of committed government and non-government stakeholders working together for change.

Through our Director and visionary founder, we shared our work, challenges, and opportunities, emphasizing the importance of a strong Action Group as a real pathway to address the barriers survivors face and bring lasting change to our communities.

ጣሊታ ራይዝ አፕ (Talita Rise Up) ከአጋራችን ድርጅት ጋር በመተባበር ለአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሴቶች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል ሲሰራ የቆየው የ7 ወር የህግ ድጋፍ ፕሮጀክት የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በደስታ ተሳትፏል። በዚህ ፕሮጀክት ላይ ከተለያዩ ሴክተሮች የተውጣጡ ባለሙያዎች በመወያየትና ልምድ በመለዋወጥ ጠቃሚ ግብአት ሰጥተዋል።

ጣሊታ ራይዝ አፕ ፕሮጀክቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቅርብ በመከታተልና በመቆጣጠር፣ በአጋር ቤቶች በተሰጡ ስልጠናዎች በመሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ማዕከል፣ ከፖሊስ፣ ከዐቃቤ ህግና ከዳኞች ጋር በመሆን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያየናቸውን ክፍተቶች በጋራ በመለየት በንቃት ተሳትፏል።

የምረቃ ስነ-ስርዓቱ እጅግ ጠቃሚ፣ እውነታን የፈለገ እንዲሁም በወንጀሉ ሰለባ በሆኑ ሴቶች ላይ ያተኮረ ነበር። በተጨማሪም ጣሊታ ራይዝ አፕ ጥብቅና በመቆም ያቋቋመውን የአስፈፃሚዎች ቡድን ያጠናከረ ሲሆን ቡድኑ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኛ የሆኑ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት መረብ ነው።

በዳይሬክተራችንና በባለራዕያችን እንዲሁም በመስራቻችን በወ/ሮ አትክልት ጃንካ አማካኝነት ያከናወናቸውን ስራዎች፣ ያጋጠሙንን ተግዳሮቶችና ያሉንን እድሎች ለተሰብሳቢው ያጋራን ሲሆን የአስፈፃሚዎች ቡድን ጠንካራ መሆን በአስገድዶ መድፈር ሰለባ የሆኑ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቅረፍና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት እውነተኛ መንገድ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተን ለተሰብሳቢው አስረድተናል።

እንኳን ለአዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!ጣሊታ ራይዝ አፕ መልካም አዲስ አመት ይመኝላችኋል!🌼🌼🌼🎉Happy Ethiopian New Year.Talita Rise Up wishes you a Happy...
11/09/2025

እንኳን ለአዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
ጣሊታ ራይዝ አፕ መልካም አዲስ አመት ይመኝላችኋል!🌼🌼🌼🎉

Happy Ethiopian New Year.
Talita Rise Up wishes you a Happy New Year.🌼🌼🌼🎉

✨ Strengthening Justice & Hope for GBV Survivors in Sidama ✨Talita Rise Up is honored to announce the signing of a Memor...
12/08/2025

✨ Strengthening Justice & Hope for GBV Survivors in Sidama ✨

Talita Rise Up is honored to announce the signing of a Memorandum of Understanding (MoU) with Mizan Lawyers Center.

🤝 This partnership is a great stride and a key endeavor in the fight against Gender-Based Violence (GBV) injustice in the Sidama Region.

Together, we are committed to:
✅ Providing comprehensive legal aid alongside medical, financial, food, shelter, and psychosocial support
✅ Delivering integrated services that address the holistic needs of GBV survivors
✅ Empowering women through training, advocacy, and capacity building
✅ Working hand-in-hand with stakeholders to ensure justice and dignity for every survivor

This collaboration is not just about services—it’s about restoring confidence, rebuilding lives, and breaking the cycle of violence.

💛 At Talita Rise Up, we believe that justice is most powerful when it walks alongside compassion. With Mizan Lawyers Center, we take one more step towards a future where every woman and girl in Sidama can rise up in safety and strength.

✨ በሲዳማ ክልል ጾታዊ ተዕኮር ጥቃትን (GBV) ለመቋቋም ፍትህ ለማስፈን እና በጋራ ለመከላከል የተገባ ዉል✨

ጣሊታ ራይዝ አፕ (Talita Rise Up) ከ ሚዛን ጠበቃዎች ማዕከል (Mizan Lawyers Center) ጋር የመግቢያ ሰነድ ስምምነት (MoU) የፈረመ መሆኑን በታላቅ ደስታ እናሳውቃለን።

🤝 ይህ የጋራ ስራ በሲዳማ ክልል ውስጥ ጾታን መሠረት ባደረገ ጥቃት ግፍን ለመቋቋም ጉልህ ሚና አለዉ ።

በአንድነት ለመስራት የተገባዉ ዉል፦
✅ ከህጋዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘ ሕክምና፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ ምግብ፣ መኖሪያ እና ማህበራዊ-ስነ-ልቦና ድጋፍ መስጠት
✅ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ተጎጂዎች የሚያስፈልጋቸውን ሙሉ አገልግሎት በተዋሃደ መንገድ ማቅረብ
✅ ሴቶችን በስልጠና፣ በንቅናቄ እና በአቅም ግንባታ ማደራጀት
✅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የፍትህን እና የሰብአዊ መብትን ለሁሉም ተጠቂዎች ማረጋገጥ

ይህ የህዝብ አገልግሎት ህይወትን ይገነባል፣የቀድሞ ማንነትን ያድሳል፣ ማኅበረሰብን ይገነባል ከዳግም ጥቃት ደግሞ ይከላከላል።

💛 በጣሊታ ራይዝ አፕ ፍትህ ከርኅራኄ ጋር ሲራመድ የሚኖረው ኃይል እጅጉን አመርቂ ነው። ከሚዛን ጠበቃዎች ማዕከል ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል ውስጥ እያንዳንዲቱ ሴትና ልጃገረድ በሰላምና በሙሉ ራስ መተማመን እንድትነሳ: ሰብአዊ መብቷ ተጠብቆ በነፃነት እንድትንቀሳቀስ በአንድነት ይሰራል።

Address

Yirgalem
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Talita - Rise Up posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Talita - Rise Up:

Share