Ethiopian Handball Federation

Ethiopian Handball Federation Ethiopia handball Federation is one of the sport federation in Ethiopia and founded on 1968 G.C

የ10ኛ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ።የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ሀዋሳ ተሞሽራለች ከፍተኛ ደስታ ልገልፅላቹ እወዳለው ለመላው ኢትዮ...
27/03/2026

የ10ኛ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
“ሀዋሳ ተሞሽራለች ከፍተኛ ደስታ ልገልፅላቹ እወዳለው ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ሀዋሳ ተሞሽራለች ቅዳሜና እሁድ ምን ታደርጋለች ኑ እያለች ስለሆነ በአዲስ አበባ በተለያዩ የሀገራችን ክፍላት ያላቹ ሰዎች የሀዋሳን ብርሀን የህዝቡን ፍቅር ታሪካዊ ማንነቱን ቅዳሜና እሁድ እየመጣቹ እንድትጋሩ ከሀዋሳ ግብዣ አቀርብላችሆለው "

ግብዣ ባስተላለፉ ማግስት በከተማዋ ክቡር ከንቲባ ጥራቱ በየነ እና ባልደረቦቻቸው ኑ ምቹ እናደርጋለን በማለት የረጅም አመት የእጅ ኳስ ቤተሰብ ጥያቄ የሆነው የውድድር ቦታ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰርተው ዝግጁ አድርገው የሀገሪቱ ከፍተኛ ውድድርን በማስተናገድ በድምቀት ተጀምሯል።

በሀዋሳ የተገኙት የ10 ክለባት ልዑካንም እውነትም ሀዋሳ ተሞሽራለች በማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቃል አረጋግጠዋል።

የስፖርት መሠረታዊ የእድገት ምንጭ የማዘውተሪያ ቦታ ዝግጅት ነውና ሀዋሳ የጥሩ ተሞክሮ መሪነቷን አሳይታለች።

ይህም ስኬት ጠንካራ የነበረውን የሀዋሳ ከተማ እጅ ኳስ ክለብ ወደ ውድድር በመመለስ ሙሉ ስኬት እንደሚያሳዩን አንጠራጠርም።

በሎጊታ እጅ ኳስ ሜዳ በመካሄድ ላይ ያለው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መጋቢት 18/2018 የተጀመረ ሲሆን ውድድር እስከ መጋቢት 26/2018 እንደሚቆይ እየገለፅን በዛሬው ዕለት በተካሄደ የመክፈቻ ውድድር በ12ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤት በሚከተለው መልኩ ተጠናቋል፡-

4:40 ሰዓት - መቻል 54 Vs 27 ከምባታ ዱራሜ
5:40 ሰዓት - ኦሜድላ 28 Vs 34 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ

ቀጣይ ፕሮግራም ቅዳሜ እረፍት በማድረግ እሁድ መጋቢት 20/2018 ሦስት ጨዋታዎች ሎጊታ ሜዳ ይካሄዳል።

እኛም እንደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዋሳዎች መጥተናል በሜዳ በመገኘት ስፖርቱን እንድትከታተሉ ጋብዘናል።

የኢትዮጵያ እጅ ኳስዐፌዴሬሽን

የሀዘን መግለጫየቀድሞ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ተስፋዬ በሻ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በእጅጉ ሀዘን እናስታውቃለን።ኮረኔል ተስፋዬ በሻ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ስፖር...
19/02/2026

የሀዘን መግለጫ

የቀድሞ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ተስፋዬ በሻ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በእጅጉ ሀዘን እናስታውቃለን።

ኮረኔል ተስፋዬ በሻ በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ስፖርት እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ታላቅ መሪ ነበሩ። በአመራራቸው ዘመን ለስፖርቱ እድገት እና ለወጣቶች እድል አግኝተዉ አለም አቀፍ ዉድድር እንዲሳተፉ ጥረት ያደረጉ አባት በመሆናቸዉ ሁሌም በክብር ይታወሳል። ታማኝነታቸው፣ ትጋታቸው እና ሀገር ፍቅራቸው ለብዙዎች አርአያ ነበር።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በለቡ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።

🗓 ቀን፡ ሐሙስ፣ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፡ 9፡00

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለስፖርቱ ማህበረሰብ በሙሉ እግዚአብሔር መጽናናት ይስጥልን።

ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ።

  News ,  ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ11 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ; ግብፅ; ሱዳ...
19/12/2025

News

,

ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ

11 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ; ግብፅ; ሱዳን; ደቡብ ሱዳን; ጅቡቲ; ሶማሊያ; ኬንያ; ሩዋንዳ; ኡጋንዳ; ታንዛንያ; ቡሩንዲ) የሚገኙበት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) እንድትመራ ኢትዮጵያ በድጋሚ በፕሬዝዳንትነት በ11ዱ አባል ሀገራት በሙሉ ድምፅ ተመረጠች።

ዛሬ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም. በካይሮ St. Rigis Hotel በተካሄደው የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዞን 5 (ምስራቅ አፍሪካ) የምርጫ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ከተያዘው 3 አጀንዳዎች አንዱ በሆነው የዞን 5 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ በሙሉ ድምፅ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጧል። ኮንግረሱ በዞኑ ስለተሰሩ እና በመሠራት ላይ ስላሉ ስራዎች የተወያየ እና ውሳኔም ማሳለፉ ታውቋል።

በኮንግረሱ የተገኙት የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝደንት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የአፍሪካን አንድነትና ጥቅም ማስከበር; በአንድነት ሁሉንም በስፖርታችን ማሳደግ እንዲሁም በአለምም መድረክ አንድ ሆነን መሠማት አለብን ብለዋል።

በማጠቃለያው የተናገሩት ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ አኛ እዚህ የወከልነውን ትልቁን የተከበረው ህዝቦቻችንን ካሰብን በአህጉራችን ጥቅም አንድ መሆናችን እና ለአለም አንድነታችንን ማሳየቻችን ትልቅ ክብር ነው ብለው የዞን 5ቱ ኮንግረስ ተጠናቋል።

በነገው እና እሁድ የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና የአለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽ የምርጫ ኮንግረሶች ይካሄዳሉ። ለአፍሪካው ፕሬዝደንትነት ዶ/ር አሬሙ መንሰሩ (ቤኒን) እንዲሁም ለአለም አቀፉ ዶ/ር ሀሰን ሙስጠፋ (ግብፅ) በእጩነት መቅረባቸው ታውቋል።

06/05/2025
06/05/2025
06/05/2025

Address

Addis Ababa
13689

Telephone

2515508983

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Handball Federation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Handball Federation:

Share