Lawyers for Human Rights - የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች

Lawyers for Human Rights - የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች LHR is a Local Organization which has been re-registered and accorded legal personality with registry number 4113 on September 18, 2019 G.C

ለተከበራችሁ የድርጅታችን ሠራተኞች፣ አባላት፣ የቦርድ አመራሮች ፣ አጋሮች እና ለመላው የሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ በዓል...
11/04/2026

ለተከበራችሁ የድርጅታችን ሠራተኞች፣ አባላት፣ የቦርድ አመራሮች ፣ አጋሮች እና ለመላው የሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም የትንሳኤ በዓል
---------------------------------
To our organizational staff, individual members, board management and leaders, partners and to the entire followers of the Christian faith, Lawyers for Human Rights extends its best wishes for a holiday filled with peace, love, unity, and compassion.

Happy Ethiopian Easter

02/04/2026

የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የነፃ የሕግ ድጋፍ መስጫ እና ማስተባበሪያ ማዕከል

የቅድመ ክስ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን በተመለከተ የባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የምክክር መድረክ
25/03/2026

የቅድመ ክስ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን በተመለከተ የባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የምክክር መድረክ

የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት መስጫ እና ማስተባበሪያ ቢሮ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሔደ“የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች” በቅድመ ክስ ሂደት...
25/03/2026

የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት መስጫ እና ማስተባበሪያ ቢሮ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሔደ

“የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች” በቅድመ ክስ ሂደት እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች ታስረው ለሚገኙና ጠበቃ ለመቅጠር አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፤ በሲዳማ፤ እና በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ነፃ የሕግ ድጋፍ መስጫ ማዕከላትን በማቋቋም እና በተንቀሳቃሽ አገግሎት መስጫ አማካኝነት አገለግሎቱን እየሰጠ ይገኛል። ድርጅታችን ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የፍትህ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የዜጎችን መብቶች እና ነጻነቶች ለማስከበር ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ጥራቱ የተጥበቀ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ለማስፋፋት፣ እንዲሁም የተቀናጀ የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል ራሱን የቻለ የነፃ የሕግ ድጋፍ መስጫ እና ማስተባበሪያ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍቶ ስራ በማስጀመር አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአራት ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት ወይም የመንገድ እና ትራንፖርት የሚገኝበት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የማስተባበሪያ ቢሮው ዋና አላማ በድርጅታችን የሚሰጡ የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቶች (በቅድመ -ክስ እና በማረሚያ ቤቶች የሚሰጡ ነፃ የህግ አገልግሎቶችን ጨምሮ) በተቀናጀ መልኩ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማስቻል እና በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች እና የሕግ ጉዳዮች እንዲሁም በነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎቱ ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመፍጠር ተደራሽነት ያለው እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲኖር ማስቻል ነው። ከዚህም በተጨማሪ የነፃ የሕግ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮው ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን በተለይም የቅብብሎሽ ስረዓትን በመጠቀም ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።
የማስተባበሪያ ቢሮው የማስጀመሪያ ፕሮግራም መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ ሲካሄድ የድርጅታችን ዋና ዳይሬክተር አቶ አመሃ መኮንን ባደረጉት ገለጻ የማስተባበሪያ ቢሮው በተለያዩ ቦታዎች የሚሰጡ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቶች በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ እንዲሰጡ ከማድረግ በተጨማሪ በፍትህ አስተዳደር ሂደት ውስጥ የአገልግሎቱን አስተዋፅዎ ለመገምገም እና የባለ ድርሻ አካላት ትብብርን ለማጠናገር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው አመላክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የነፃ ሕግ ድጋፍ አገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን እና ውጤታማ የሆነ የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ጠቁመዋል።
ከማስተባበሪያ ቢሮው የማስጀመሪያ ፕሮግራም ቀደም ብሎም ከ.ኢ.ፌ.ደ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ሊኖር በሚገባው ትብብር ዙሪያ ከሚመለከታቸው ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ጥልቅ ምክክር የተደረገበትን መድረክ ለማዘጋጀት የተቻለ ሲሆን በምክክር መድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፍትህ ቢሮ፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፍትህ ቢሮ፤ የኢትዮጲያ ፌደራል ፖሊስ፤ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የፌደራል ጠበቆች ማህበር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በምክክር መድረኩ የእለቱን ቁልፍ ንግግር ያደረጉት አቶ አወል ሱልጣን (በኢፌደሪ ፍትህ ሚኒስቴር የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር) ሲሆኑ በንግግራቸውም ፍትህ የማግኘት መብት ለሁሉም የሰው ልጆች የተሰጠ ሰብአዊ መብት መሆኑን አስታውሰው ይህም መብት ከሚከበርባቸው መንገዶች መካከል ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዋነኛው እና መሰረታዊ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይም የወንጀል ፍትህ አስተዳደር በሚጀምርበት በፖሊስ ጣቢያዎች የሚሰጡ የቅድመ-ክስ ነፃ የሕግ ድጋፎች ከምርመራ እስከ ማረም እና ማነፅ ድረስ ያሉትን ሂደቶች ውጤታማነት የሚወስኑ በመሆኑ ከተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች እና ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፍትህ ተቋማት አላማቸውን ከማሳካት አንፃርም ሊቃኝ እና ሊደገፍ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የቅድመ-ክስ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቱን በማስመልከት የቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሚና እና የትብብር ማዕቀፍ አስፈላጊነት ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ እና ጥልቅ ውይይት የተደረገ ከመሆኑም በላይ በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የገጠሙ ተግዳሮቶች በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብበር እና ቀጣይነት ባለው የመረጃ ልውውጥ በሚፈቱበትን አቅጣጫዎች ላይ በመግባባት የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።

19/03/2026

ዒድ ሙባረክ !
Eid Mubarak !
🕌🌙✨

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳች ሁ !

We at Lawyers for Human Rights extend our warm wishes to all Ethiopian Muslims and Muslims around the world celebrating Eid al-Fitr. May this special occasion bring you peace, happiness, and abundant blessings. Wishing you a joyful celebration with your loved ones.

🏛 Strengthening the Path to Justice: LHR Hosts Strategic Litigation Roundtable Discussion.February 28 - March 1, 2026
11/03/2026

🏛 Strengthening the Path to Justice: LHR Hosts Strategic Litigation Roundtable Discussion.

February 28 - March 1, 2026

🏛 Strengthening the Path to Justice: LHR Hosts Strategic Litigation Roundtable Discussion On February 28 - March 1, 2026 Lawyers for Human Rights (LHR) conv...

10/03/2026

On International Women’s Day, we celebrate the strength, resilience, and leadership of women and girls everywhere.

At Lawyers for Human Rights (LHR), we recognize that sustainable peace, justice, and democratic governance cannot be achieved without the meaningful participation, protection, and empowerment of women. Across Ethiopia, women continue to play a vital role in promoting human rights and contributing to community development and justice.

Yet many women and girls still face discrimination, violence, and barriers to accessing justice. On this day, we reaffirm our commitment to advancing gender equality and amplifying women’s voices in all spaces where decisions about justice and rights are made.

We stand with women human rights defenders, survivors, and community leaders who continue to advocate for dignity, equality, and justice. Their courage inspires and strengthens the work we do every day.

Let us continue working together to build a society where the rights, safety, and leadership of women and girls are fully respected and protected.

08/03/2026

🏛 Strengthening the Path to Justice: LHR Hosts Strategic Litigation Roundtable Discussion On February 28 - March 1, 2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lawyers for Human Rights - የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Lawyers for Human Rights - የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች:

Share