EvaSUE

EvaSUE EvaSUE is a fellowship of Students and Graduates who are dedicated to follow and witness Jesus Christ as Lord and Savior.

Evangelical Students' and Graduates' Union of Ethiopia is a ministry that serves University and College Evangelical Christian Student Fellowships.

ተስፋ | ክፍል 4ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ።  ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩ...
03/10/2026

ተስፋ | ክፍል 4

ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ። ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩም እግዚአብሔር ነው ። ወንዝ የተጓዘበት መንገድ ሁሉ ልምላሜን ይቸራል ። ከወንዝ አጠገብ ያለ ተክል ፍሬያማ ፣ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ሁሉ በተስፋ የሚደረግ ጉዞ ሕይወት እና ስኬታማነትን ይጎናጸፋል ። መሠረቱ ምንጭ የሆነ ወንዝ የማይቆም ወንዝ ነው ። የማይቆም ወንዝ ደግሞ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል ። ድንጋዩን ሰንጥቆ የሚያልፈው ግን በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ ነው ። ለዚህም ጽናትን ወልደ ተስፋ ልንለው እንችላለን ። ያለተስፋ ጽናት እንዲሁ የሚመጣ ነገር አይደለም ። የምንጸናው በተስፋ ነውና ። ተስፋ ከእግዚአብሔር ስለሚመነጭ ተስፋ ቢስ ሆኖ ለደከመው የሰው ልጅ ልምላሜ እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ የማይጠፋ ተስፋን ሰጠው ።

ባለመታዘዝ ጠንቅ በሠራው ኃጢአት ምክንያት ለወደቀው የሰው ልጅ እግዚአብሔር የሰጠው ሀብት ተስፋን ነበር ። ርሱም ተስፋ በክርስቶስ በኩል ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የመምጣት ተስፋ ነበር ። ተስፋን የሰጠ የታመነ አምላክ ነውና እንደተናገረው ተስፋውን ፈጸመው ። በርግጥም ቀቢጸ ተስፋነት ባየለበት ዓለም ፤ በኃጢአታችን ከዛልንበት ድካም ብርቱ ሆነን ምንቆመው ፥ ሞታችን ተሽሮ ሕያውነትን ምንጐናጸፈው እግዚአብሔር በላከው አንዲያ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ስናመን ነው ። አምነን የዳንበት ወንጌል ቀድሞ የተሰጠ ተስፋም ነው ።

ይህ ተስፋ ዛሬም በክርስቶስ ኢየሱስ ባለማመን በብዙ ተስፋ መቁረጥ ላሉት ሕይወትን የሚሰጥ ወንጌል ነው ። የምንሰብከው ፥ ያመነው ፣ የምንኖርበት ወንጌል እግዚአብሔር የሰጠው የዘላለም ተስፋ ነው ። ለምውቱ ሰው ሕያውነትን የሚዘራ ተስፋ በክርስቶስ መሆን ነው ። ዘለዓለማዊው ዕረፍት በዘለዓለሙ ተስፋ በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ነው ። ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ካላመነ በቀር ከተስፋ መቁረጥ ስሜት ነጻ ሊሆን አይችልም ።

ተስፋችን ፍጹም የሚሆነውም የምንጠበቀው ተስፋችን ኢየሱስ በክብር በመላእከት ታጅቦ ሲመጣ ነው ። ዳሩ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነንም መከራ በበዛበት ዓለም ስላለን ፤ አንዳንዴ ቀድሞ በዓለም እንዳለው ያይደለ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ልናስተናግድ እንችል ይሆናል ። እንዲህ ባለ ሁናቴ ብዙዎቹ ቅዱሳን እንዳሳለፉ በቅዱሱ መጽሐፍ ተጽፏል ። አብርሃም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ነገሩን ለእግዚአብሔር ያዋየዋል ። መበርቻ የሚሆንም ቃል ከእግዚአብሔር ሰምቶ ይጸና ፥ ይጽናና ነበር ። ኤልያስንስ ብናነሣው ከኤልዛቤል በደረሰበት ዛቻ በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ እና ሀዘን ሆኖ ፥ ፍረኃቱን በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ ሞቱን እስኪመኝ በደረሰ ጊዜ ዳግመኛ ታድሶ እና በርትቶ ለብዙዎች የመነሣት ምክንያት ሲሆን እንመለከታለን ። ደካማውን እና ተስፋ በመቁረጥ የዛለውን ልብ እግዚአብሔር በተስፋ ሞልቶ ማስነሣቱ ድንቅ ነው ።

ይቀጥላል ...
ተጻፈ በጌታሁን አያኖ

የመንግሥቱ ተስፋ ለማን ነው የተሰጠው?የማናውቀውን ነገር አንናፍቅም።የማንወደውንም አንገዛለትም።የማንፈልገውን አንጠብቅም።ታዲያ የመንግሥቱን ተስፋ እየጠበቅን ከሆነ፣ የምንጠብቀውን መንግሥት በ...
26/09/2026

የመንግሥቱ ተስፋ ለማን ነው የተሰጠው?

የማናውቀውን ነገር አንናፍቅም።
የማንወደውንም አንገዛለትም።
የማንፈልገውን አንጠብቅም።

ታዲያ የመንግሥቱን ተስፋ እየጠበቅን ከሆነ፣ የምንጠብቀውን መንግሥት በእውነት እናውቀዋለን?

የመንግሥቱ ተስፋ አውቀን፣ ወደን፣ በክርስቶስ አምነን ለዳንን የተሰጠ ተስፋ ነው። ድነን ብቻ ግን የቆምን አይደለንም፤ እንደ ፈቃዱ ለመኖር የወሰንንም ነን።

እዚህ ላይ ልንረሳው የማይገባን አንድ ነገር አለ፦ ኢየሱስ አዳኛችን ብቻ ሳይሆን ንጉሣችንም ነው።

ንጉሥ ከሆነ ደግሞ፣ የእርሱ ሕዝብ የሆኑት ሁሉ እንደ ፈቃዱ መኖር አለባቸው። ልንገዛለት፣ ልንቀደስ እና ሕይወታችንን ለእርሱ ፈቃድ ልንሰጥ የሚገባንም ለዚህ ነው። ተስፋ የምናደርገው መንግሥቱን ነውና።

እስቲ ቆም ብለን እናስብ፦ ኑሮአችን ለክርስቶስ የተገዛ ነው? ካልሆነስ፣ የመንግሥቱን ተስፋ መጠበቅ ምን ያህል ትርጉም ይኖረዋል?

በእርግጥም፣ በዚህ ተስፋ ስንኖር፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያደረግን፣ በቃሉ ራሳችንን እየመገብን፣ ራሳችንን እየቀደስን፣ በማንኛውም ሁኔታ ከፊታችን ያለውን ተስፋ በደስታ መጠበቅ ይኖርብናል።

1 ጴጥሮስ 1:13, 15 — NASV

[13] ስለዚህ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ራሳችሁንም ግዙ፤ ተስፋችሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለእናንተ በሚሰጠው ጸጋ ላይ ሙሉ በሙሉ አድርጉ።

[15] ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።

እንደዚህ መኖር ይሁንልን!
አሜን።

—ምህረት

አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን።...
19/09/2026

አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣
ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣
ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣
እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን።
አምላካችን ማን እንደሆነ እንረሳለን።

ይህ በእኛ አልተጀመረም። በኢሳይያስ ምዕራፍ 40:27ን
ብናይ፣ እስራኤላውያን መብታቸው በእግዚአብሔር እንደተዘነጋ፣
እንደተተዉ እና እንደተረሱ ስለተሰማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ
ተስፋ መቁረጣቸውን እናያለን።

እኔም ብዙ ጊዜ ይህን አድርጌያለሁ። ዓለም በዙሪያዬ እየፈራረሰ እንደሆነ
፣ እግዚአብሔር ግን የትም እንደሌለ የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ።
እግዚአብሔር ግን ለእስራኤላውያን የሰጠውን መልስ ቁጥር 28 ላይ እዩ።

የእስራኤላውያን ትኩረት ሁኔታቸው ላይ ስለነበር፣ እግዚአብሔር
ትኩረታቸውን ወደ እርሱ ማንነት መለሰ። ስለ ታላቅነቱ በማስታወስ፣
እርሱ የምድር ፈጣሪ መሆኑን፣ የማይደክም፣ የማይታክት፣ ብርታት ሰጪ
አምላክ እንደሆነ ዘርዝሮ፣ ተስፋ የሚጣልበት አምላክ መሆኑን አሳያቸው።

ቁጥር 31 ላይም፦

“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥
እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”

በማለት መልእክቱን ደመደመው።

እስራኤል በወቅቱ የእግዚአብሔርን ማንነት ማስታወስ እንደነበረባት ሁሉ፣ እኛም እንዲሁ ማድረግ አለብን ብዬ አስባለሁ።
አዎ፣ ሁኔታዎቻችን እግዚአብሔር እንደረሳን ሊነግሩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ባሕርዩ የሚነግረን ከዚህ በተቃራኒ ነው።
ለዛም ነው እርሱ ማን እንደሆነ ራሳችንን ማስታወስና ተስፋችንን በእርሱ ላይ ማድረግ የሚገባን።

ምክንያቱም እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ኃይላቸውን ያድሳሉና።
እግዚአብሔር ይህን ዓመት ዕለት ተዕለት ማንነቱን እንድናስታውስ ይርዳን!
አሜን።

—ምሕረት

አደይ አበባ ሳይ መጀመሪያ ትዝ የሚለኝ እንቁጣጣሽ ነው። ቀኑ ሲደርስ እንኳን አደረሰህ! እንኳን አደረሰሽ! እየተባባልን በማዕድ ዙሪያ አንድ ላይ እንቀርባለን። በጨዋታውም መሃል ስለሚመጣው ዓ...
11/09/2026

አደይ አበባ ሳይ መጀመሪያ ትዝ የሚለኝ እንቁጣጣሽ ነው።
ቀኑ ሲደርስ እንኳን አደረሰህ! እንኳን አደረሰሽ! እየተባባልን በማዕድ ዙሪያ አንድ ላይ እንቀርባለን። በጨዋታውም መሃል ስለሚመጣው ዓመት ብዙ ተስፋ እንሰንቃለን፤ ከፊት ያለውንም እያሰብን እራሳችንን እናበረታለን።

ታዲያ ስለ ተስፋ ሲነሳ፣ በሐዋርያት ሥራ ላይ ውብ በተባለው ደጅ ጴጥሮስ ለሽባው ለማኝ ያደረገው ትዝ አለኝ። ተስፋው መንምኖ ጴጥሮስን ለአንዳች ነገር እየጠበቀ ነበር፤ እርሱም ገንዘብ! አልፈርድበትም! ጴጥሮስ ግን ከገንዘብ ይልቅ የተሻለ ነገርን ለማካፈል ወደደ።
በደንብ ስናጠና ጴጥሮስ ገንዘብ ቸግሮት እንዳልነበር እንረዳለን።
ለለማኙ ገንዘብ ከመስጠት ይልቅ ግን ፣ በጌታው የተስፋ ቃል ታምኖ፣ “ተነስ እና ተመላለስ” ማለትን መረጠ። ቁርጭምጭሚቶቹም ፀንተው ቀሩ!

ከጠበቀው እና ካሰበው፣ ተስፋም ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ሆነለት።
ከዚያም ሕይወቱን ሙሉ እያየው ያላገኘው፣ እየተመኘው ተስፋ የቆረጠበት፣
ቤተ መቅደስ መግባት ቻለ! እግዚአብሔርንም አመሰገነ!
ሕይወቱን ሙሉ ከተቀበለው ገንዘብም በላይ ሆነለት።

ዛሬስ እኛ ለዚህ ተስፋ ለቆረጠ ትውልድ ምንድነው የምንሰጠው?
ብር? ወርቅ? ልብስ? ቤት? ጌጥ?

ከእነዚህ ጊዜያዊ ነገሮች በላይ፣ ነፍስን የሚያድስ፣
ከጨለማ የሚያወጣ ሕያው የሆነ ተስፋ ተቀብለናል።
ስለዚህ፣ አዲሱን ዓመት ይህን ተስፋ በጨለማ ላሉት ሁሉ የምናጋራበት፣
ስለማይጠፋው እና ስለማይበላሸው በሰማይ ላለው ርስት የምናወራበት፣
እንዲሁም የትውልዱን ትኩረት እንደገና ወደ የኢየሱስ መምጣት የምናዞርበት ዓመት ይሁንልን።

✨መልካም አዲስ ዓመት✨

—ምሕረት

ተስፋ ክፍል 4ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ።  ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩም ...
29/08/2026

ተስፋ
ክፍል 4

ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ። ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩም እግዚአብሔር ነው ። ወንዝ የተጓዘበት መንገድ ሁሉ ልምላሜን ይቸራል ። ከወንዝ አጠገብ ያለ ተክል ፍሬያማ ፣ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ሁሉ በተስፋ የሚደረግ ጉዞ ሕይወት እና ስኬታማነትን ይጎናጸፋል ። መሠረቱ ምንጭ የሆነ ወንዝ የማይቆም ወንዝ ነው ። የማይቆም ወንዝ ደግሞ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል ። ድንጋዩን ሰንጥቆ የሚያልፈው ግን በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ ነው ። ለዚህም ጽናትን ወልደ ተስፋ ልንለው እንችላለን ። ያለተስፋ ጽናት እንዲሁ የሚመጣ ነገር አይደለም ። የምንጸናው በተስፋ ነውና ። ተስፋ ከእግዚአብሔር ስለሚመነጭ ተስፋ ቢስ ሆኖ ለደከመው የሰው ልጅ ልምላሜ እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ የማይጠፋ ተስፋን ሰጠው ።

ባለመታዘዝ ጠንቅ በሠራው ኃጢአት ምክንያት ለወደቀው የሰው ልጅ እግዚአብሔር የሰጠው ሀብት ተስፋን ነበር ። ርሱም ተስፋ በክርስቶስ በኩል ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የመምጣት ተስፋ ነበር ። ተስፋን የሰጠ የታመነ አምላክ ነውና እንደተናገረው ተስፋውን ፈጸመው ። በርግጥም ቀቢጸ ተስፋነት ባየለበት ዓለም ፤ በኃጢአታችን ከዛልንበት ድካም ብርቱ ሆነን ምንቆመው ፥ ሞታችን ተሽሮ ሕያውነትን ምንጐናጸፈው እግዚአብሔር በላከው አንዲያ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ስናመን ነው ። አምነን የዳንበት ወንጌል ቀድሞ የተሰጠ ተስፋም ነው ።

ይህ ተስፋ ዛሬም በክርስቶስ ኢየሱስ ባለማመን በብዙ ተስፋ መቁረጥ ላሉት ሕይወትን የሚሰጥ ወንጌል ነው ። የምንሰብከው ፥ ያመነው ፣ የምንኖርበት ወንጌል እግዚአብሔር የሰጠው የዘላለም ተስፋ ነው ። ለምውቱ ሰው ሕያውነትን የሚዘራ ተስፋ በክርስቶስ መሆን ነው ። ዘለዓለማዊው ዕረፍት በዘለዓለሙ ተስፋ በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ነው ። ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ካላመነ በቀር ከተስፋ መቁረጥ ስሜት ነጻ ሊሆን አይችልም ።

ተስፋችን ፍጹም የሚሆነውም የምንጠበቀው ተስፋችን ኢየሱስ በክብር በመላእከት ታጅቦ ሲመጣ ነው ። ዳሩ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነንም መከራ በበዛበት ዓለም ስላለን ፤ አንዳንዴ ቀድሞ በዓለም እንዳለው ያይደለ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ልናስተናግድ እንችል ይሆናል ። እንዲህ ባለ ሁናቴ ብዙዎቹ ቅዱሳን እንዳሳለፉ በቅዱሱ መጽሐፍ ተጽፏል ። አብርሃም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ነገሩን ለእግዚአብሔር ያዋየዋል ። መበርቻ የሚሆንም ቃል ከእግዚአብሔር ሰምቶ ይጸና ፥ ይጽናና ነበር ። ኤልያስንስ ብናነሣው ከኤልዛቤል በደረሰበት ዛቻ በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ እና ሀዘን ሆኖ ፥ ፍረኃቱን በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ ሞቱን እስኪመኝ በደረሰ ጊዜ ዳግመኛ ታድሶ እና በርትቶ ለብዙዎች የመነሣት ምክንያት ሲሆን እንመለከታለን ። ደካማውን እና ተስፋ በመቁረጥ የዛለውን ልብ እግዚአብሔር በተስፋ ሞልቶ ማስነሣቱ ድንቅ ነው ።

ይቀጥላል ...
ተጻፈ በጌታሁን አያኖ

22/08/2026

Thank you to our amazing volunteers
18/08/2026

Thank you to our amazing volunteers

17/08/2026

Address

Queen Elizabeth II
Addis Ababa
34354

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EvaSUE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share