11/10/2026
በደሴ ከተማ በመስጅድ ኔት ፕሮግራም በተለያዩ የዲጂታል ዘርፎች የሰለጠኑ 40 ተማሪዎች ተመረቁ!
EMYC | ጥቅምት 1፣ 2019 ዓ.ል | ረቢዑስ ሳኒ 30፣ 1448 ዓ.ሂ
በአማራ ክልል የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል፣ በታላቁ አረብ ገንዳ መስጂድ በሚገኘው የመስጅድ ኔት ማዕከል በተለያዩ የዲጂታል ዘርፎች የሰለጠኑ 40 ተማሪዎችን ዛሬ በድምቀት አስመርቋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ፣ የደቡብ ወሎ ዞን፣ የከሚሴ ማዕከልና የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አመራሮች፣ የመጅሊስ አመራሮች፣ ወጣቶችና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሰልጣኞቹ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በዲጂታል ማርኬቲንግና በሌሎች ዘመኑን የዋጁ የዲጂታል ዘርፎች ተግባራዊ ሥልጠና ያገኙ ሲሆን፣ ይህም ወጣቶች የዲጂታል ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና የሥራ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ ያግዛል።
የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ወጣቶችን በቴክኖሎጂና በዲጂታል ክህሎት በማብቃት፣ የፈጠራ አቅማቸውን በማጎልበትና ከዘመኑ የሥራ ዓለም ጋር እንዲላመዱ በማድረግ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር በተለያዩ አካባቢዎች እየሠራ ይገኛል። የመስጅድ ኔት ፕሮግራምም የዚሁ ጥረት አካል ሲሆን፣ ወጣቶች የዲጂታል እውቀታቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል።