Women in MICE Ethiopia

Women in MICE Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Women in MICE Ethiopia, Non-Governmental Organization (NGO), Africa Avenue Mega buildingBole road, Addis Ababa.

Women in MICE Ethiopia is a board-led, non–profit–making, non–religious, non-political, and non – governmental women’s organization with a special interest in empowering women and girls to contribute to transforming society and impacting positive change.

29/05/2026

ውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ/Women in MICE Ethiopia
በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ አስተዳደር በአረካ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በማክሰኞ ገበያ ላይ ዜጎች በነቂስ ወተው ይበጀኛል ብለው ላመኑበት ድምፃቸውን እንዲሰጡ በራሪ ወረቀት በመስጠትና በሴቶች እና አካል ጉዳተኞች በምርጫ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ክርክር እና ውይይት እንዲሁም ቲያትር በማሳየት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቷል።

29/05/2026
28/05/2026

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሠረት:-
- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

Taste of Nardi
28/05/2026

Taste of Nardi

ውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ/Women in MICE Ethiopiaበወላይታ ዞን በአረካ ከተማ አስተዳደር በማክሰኞ ገበያ ላይ ዜጎች በነቂስ ወተው ይበጀኛል ብለው ላመኑበት ድምፃቸውን እንዲሰጡ በ...
28/05/2026

ውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ/Women in MICE Ethiopia
በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ አስተዳደር በማክሰኞ ገበያ ላይ ዜጎች በነቂስ ወተው ይበጀኛል ብለው ላመኑበት ድምፃቸውን እንዲሰጡ በራሪ ወረቀት በመስጠትና በሴቶች እና አካል ጉዳተኞች በምርጫ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ቲያትር በማሳየት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቷል

28/05/2026

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
• ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
• የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
• የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
• የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ

2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
• የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
• የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
• ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

Website: https://l1nq.com/n5amd66

X (Twitter): https://t.ly/o2nM9

Telegram: https://t.ly/BmT_4

YouTube: https://t.ly/N80Eo

LinkedIn: https://t.ly/zntYV

WhatsApp: https://t.ly/3Gfih

TikTok: https://surl.li/rrtdog

ከልብ እናመሰግናለን
27/05/2026

ከልብ እናመሰግናለን

26/05/2026

ግንቦት 15/2018 በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከነበረን የተማሪዎች ክርክር እና ውይይት በወላይታ Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት

Address

Africa Avenue Mega BuildingBole Road
Addis Ababa
4462

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Women in MICE Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Women in MICE Ethiopia:

Share