Plant Protection Society of Ethiopia- PPSE

Plant Protection Society of Ethiopia- PPSE The Plant Protection Society of Ethiopia (PPSE) is a non profit professional association established in 1992.

23/12/2024

It is with great apologies that we announce postponement of the 28th Annual Conference of the Plant Protection Society of Ethiopia (PPSE). As we received comments from some PPSE members, the earlier schedule coincided with the EIAR research Review Program and other busy schedules. We will let you know the date and venue in our next communication. With the same message we encourage members to keep on submitting their abstracts.

Send a message to learn more

26/11/2024

Dear Colleagues,
We are delighted to announce that the 28th Annual Conference of the Plant Protection Society of Ethiopia (PPSE) will take place on December 26–27, 2024, at the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR), Hiruy Hall, Addis Ababa.

We look forward to your participation!

Sincerely,

Send a message to learn more

05/09/2024

የስንዴ በሽታ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መልዕክት!
****************
1. መግቢያ

ፉዛሪየም ሄድ ብላይት (Fusarium Head Blight Fusarium graminearum) በመባል የሚታወቀው በአለም ዙሪያ ያሉ የሳር ሰብሎችን በተለይም የስንዴውን ፍሬ የሚያጠቃ አደገኛ የፈንገስ በሽታ ነው። ፉዛሪየም ሄድ ብላይት ስንዴን ከሚያጠቁ በሽታዎች መካከል ውስብስብ ባህሪይ ያለው በጣም ክፍተኛ ብክነትና ብክለት የሚያስከትልና ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነ የስንዴ በሽታ ነው። ይህ በሽታ ከስንዴ በተጨማሪ ገብስንም የሚያጠቃ ሲሆን ከገብስም በበለጠ በስንዴ ላይ የምርት ቅነሳ እንዲሁም አፍላቶክሲን በመባል የሚታወቅ መርዛማ የሻጋታ ወይም ፈንገስ ዝሪያ በሰውና በእንስሳት ጤና ላይ ችግር የሚያስከትል ማይኮቶክስንን ያመነጫል፡፡

2. የፉዛሪየም ሄድ ብላይት በሽታ ምልክቶች

• የበሽታው ምልክት በተክሉ ጭንቅላት ላይ እና የስንዴ ፍሬውን በሚሸፍነው አንድ ወይም ከአንድ በላይ ክፍል ካለው (Spikelets) ላይ የመገርጣት ምልክት በአጭር ግዜ ውስጥ ያሳያል፣
• ይህም ምልክት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታየው የስንዴ ፍሬውን በሚሸፍነው ክፍል (Spikelets) መሀል ላይ ነው፣
• የዚህ በሽታ ምረዛውም መጀመሪያ ምልክቱ ከታየበት ወደ ጎኑ ካሉት የስንዴ ፍሬውን ወደ ሚሸፍነው ክፍል (Spikelets) ይዛመታል፣
• ቀስ በቀስም የስንዴ ፍሬውን በሚሸፍነው ክፍል (Spikelets) ላይ ደማቅ ሮዝ ቀለም ምልክት ይታያል፣
• የተመረዘው/የተጠቃው አበቢት (floret) ክፍል ቀስ በቀስ ጠቆር ያለ እና ዘይት መሰል ምልከት ያሳያል፣

3. ፉዛሪየም ሄድ ብላይት መከላከልን አስቸጋሪ የሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች

• በሽታውን ሙሉ በሙሉ ሊቋቋሙ የሚችሉ ዝርያዎች ሀገር ውስጥ አለመኖር፣
• የፀረ-ፈንገሱ ውጤታማነትም በርጭት ወቅት የተወሰነ መሆኑ፣
• የሰብሉ ዕድገት ደረጃ በአበባ ላይ ከሆነ እና የአየሩ ሁኔታ ርጥበት አዘል እና ሞቃት ከሆነ የበሽታው አደገኛነት እየጨመረ የሚመጣ መሆኑ፣
• ሰብሉን በፀረ-ፈንገስ ርጭት መቆጣጠር የሚቻለው በአበባ ወቅት በመሆኑ ውጤታማ ርጭት ለማካሄድ ከአምስት እስከ ስድስት ቀን ብቻ የሚፈልግ መሆኑ የበሽታውን ቁጥጥር ሥራ አስቸጋሪ ያደርገዋል፣

4. መከላከያና የመቆጣጠሪያ መንገዶች

4.1 የባህላዊ መከላከያ መንገዶች፡

• በእርሻ ቁሳቁሶችም ሆነ በመስክ ስራዎች ላይ ጥሩ የማሳ ንፅህና አጠባበቅ ዘዴዎችን መጠቀም የበሽታ አምጪ ፈንገስ መራቢያ አካል መጠን በመቀነስ የፉዛሪየም ሄድ ብላይት ስርጭትን ይከላከላል።
• ከማሳ ውስጥ ለበሸታ መራቢያነት የሚያገለግሉ የሳር ዘር የሆኑ አረሞችን ማስወገድ
• እንዲሁም በአበባው ወቅት የእርሻ ስራን ማቆም ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም የበሽታ አምጪ ተዋህሲያን ሊያሰራጭ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድርግ ይገባል፡፡ ነገር ግን መቆጣጠሩን ውጤታማ ለማድረግ ፀረ - ፈንገስ መጠቀም ያስፈልጋል።

4.2. አንፃራዊ የሆነ በሽታውን የመቋቋም ችሎታ ያላቸውን ዝሪያዎች መጠቀም
(Moderately resistant cultivars)

• በሀገራችን ምርምር ምክረ ሀሳብ መሠረት ሾርማና ኪንግ በርድ የሚባሉ የስንዴ ዝሪያዎች በመስኖ የሚለሙ ከሆነ ቱቦኮናዞልና ናቹራ የሚባሉ ፀረ-ፈንገሶችን ገና ቢጫ አበባ እንደታየ በመርጨት በሽታውን መቆጣጠር ይቻላል፡፡
• እንዲሁም ሻክ የሚባል የስንዴ ዝሪያ ፉዛሮ ፀረ-ፈንገስ ሁለት ጊዜ በወቅቱ በመርጨት መከላከል ይቻላል፡፡

4.3. ፀረ-ፈንገስ ኬሚካል መጠቀም

• ትክክለኛውን የተመዘገበ ፀረ-ፈንገስ ኬሚካል መጠቀም የበሽታውን ስርጭት እንዲሁም የጉዳት መጠን ለመቀነስ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡ ለዚህም የትራይዞል ፀረ-ፈንገስ (Triazoles Group) ምድብ የያዙ ፀረ-ፈንገሶችን መጠቀም፣
• የፀረ - ፈንገስ ርጭቱ ወቅት መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ወቅቱን በደንብ ለይቶ ማወቅ (አበባ ማበብ ሲጀምር የአበባው ቀለም ቢጫ በሚሆንበት ወቅት ርጭት ቢካሄድ በጣም ውጤታማ ወቅት መሆኑ፣ በተጨማሪም 50% አበባው ቢጫና 50% አበባው ነጭ ቀለም በሚሆንበት ወቅትም ርጭት ቢካሄድ መቆጣጠር እንደሚቻል ነገር ግን አበባው ሙሉ ለሙሉ ነጭ ቀለም ሲያወጣ እና የበሽታው ምልክት በተክሉ ላይ ከታየ ርጭት ቢካሄድ በጣም የዘገየ በመሆኑ ውጤታማ አይሆንም)
• የፀረ-ፈንገስ ርጭት የሚካሄደው በባለፈው ምርት ዘመን የበሽታው ክስተት ባለባቸው ማሳዎች አካባቢ ሲሆን ምክንያቱም የበሽታ አምጪ ተዋህሲያን በስንዴ ቃርሚያና በአፈር ውስጥ የህይወት ዑደቱን ስለሚያሳልፍ፣ ስንዴ ዓመቱን ሙሉ መመረቱና ምቹ የአየር ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
• በተጨማሪም በአጎራባች የስንዴ ማሳዎች ላይ የበሽታው ክስተት ካለ ርጭት ማካሄድ
• የስትሮብሊን (Striobin) ምርት የሆኑትን ፀረ - ፈንገሶች ለፉዛሪየም ሄድ ብላይት መቆጣጠር መጠቀም የለብንም ምክንያቱም ዶን (DON, Deoxynivalenol) Mycotoxins) የተባለውን ማይኮቶክሲን መጠን ስለሚጨምር፣
• ፀረ - ፈንገሱ መያዣ ላይ ያለውን የአሠራርና ጥንቃቄ መመሪያ በሚገባ መከተል የሚሉት በዋናነት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡

ግብርና ሚኒስቴር
ነሐሴ 2016 ዓ.ም

Address

EIAR
Addis Ababa
8441

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Plant Protection Society of Ethiopia- PPSE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Plant Protection Society of Ethiopia- PPSE:

Share

Why PPSE is established?

The Plant Protection Society of Ethiopia (PPSE) is a non profit professional association established in 1992 by the merger of two previously formed committees: the Ethiopian pathological Committee (EPC) Established in 1976, and the committee of Ethiopian Entomologists (CEE) established in 1981.

The objective of PPSE is to contribute towards the development of Ethiopian Agriculture by reducing crop losses caused by insect pests and diseases through promoting effective research, documenting and dissemination of scientific information, encouraging professional growth and fostering interdisciplinary interaction among plant protection scientists to solve problems related to plant protection.