Kidy Foundation

Kidy Foundation ‘Life has the right of way’ We are all created in the image and likeness of our creator. Life is the most precious thing in our world.

Kidy Foundation is dedicated to reducing vehicle accidents in Ethiopia through education and support. They provide immediate aid to accident victims and offer long-term recovery assistance. Their mission is to prevent accidents, respond promptly to collisions, and help victims reintegrate into society. Join them as a member, partner, or ambassador to make Ethiopia's roads safer. For more information, visit Kidy Foundation.

🌟 Get Dirty for a Cleaner Furi Primary School! 🌟Kidy Foundation invites students, parents, teachers, and community membe...
21/08/2025

🌟 Get Dirty for a Cleaner Furi Primary School! 🌟

Kidy Foundation invites students, parents, teachers, and community members to join our Hygiene & Sanitation Cleaning Campaign at Furi Primary School. 🧹🪣

We’ll be:
✅ Cleaning classrooms, playgrounds, and school compounds
✅ Collecting and properly disposing of waste
✅ Promoting a healthier and cleaner environment for our children

Everyone is welcome—let’s roll up our sleeves and make a difference!

ደህንነቱ የተጠበቀ ማሽከርከር፣ 🔹ሁለቱም ስፖክዮዎች ከኋላ የሚመጣውን ነገር በግልፅ ለማየትና የፍትለፊት መስታወት መጽዳት ደግሞ ፊትለፊት መንገዳችንን ለማየት ይጠቅማል፡፡🔹እርሶም ሆነ ውስጥ ...
20/08/2025

ደህንነቱ የተጠበቀ ማሽከርከር፣
🔹ሁለቱም ስፖክዮዎች ከኋላ የሚመጣውን ነገር በግልፅ ለማየትና የፍትለፊት መስታወት መጽዳት ደግሞ ፊትለፊት መንገዳችንን ለማየት ይጠቅማል፡፡
🔹እርሶም ሆነ ውስጥ ያለው ተሳፋሪ ቀበቶ ማሰሩን ያረጋግጡ፡፡
🔹እየነዱ በፍጹም ስልክ ለማናገርና የጽሑፍ መልእክት ለመለዋወጥ አይሞክሩ፡፡
🔹አዕምሮዎ እና ሰውነትዎ በቂ እረፍት ብያደርግ ይመከራል፡፡
🔹ምንም አይነት አደንዛዥ ነገር አይጠቀሙ፡፡
አንድ ሰከንድ ግድየለሽነት ሕይወትን ሊለውጥ ይችላል። እያንዳንዱ ጉዞ በደህንነት ይጀምር።

ኪዲፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የመንገድ ደህንነታቸው የተጠበቀ ልጆችን እናሳድግ! ድንገተኛ የመኪና አደጋ ገና ህይወትን በቅጡ ያላዩ፣ ሮጠው ያልጠገቡና ነገ ትውልድን ያስቀጥላሉ የተባሉ ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ህጻናት ላይም...
19/08/2025

የመንገድ ደህንነታቸው የተጠበቀ ልጆችን እናሳድግ!
ድንገተኛ የመኪና አደጋ ገና ህይወትን በቅጡ ያላዩ፣ ሮጠው ያልጠገቡና ነገ ትውልድን ያስቀጥላሉ የተባሉ ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ህጻናት ላይም አለንጋውን እያሳረፈ ይገኛል::
ህጻናት ከቤት ተልከው በሚወጡበት ሰዓት ትምህርት ቤት ሲሄዱና ሲመለሱ እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ መንገድ ላይ ሲጫወቱ ይህ አስከፊ አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል:: አደጋውን ለመከላከል የወላጆች ኃላፊነት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው መንገድ ዳር እንዳይጫወቱ፣ መንገድ ሲያቋርጡ ግራና ቀኝ እንዲመለከቱ፣ እንዲሁም የእግረኛ ማቋረጫ እንዲጠቀሙ ማስተማር ይገባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ደህንነታቸው የሚጀምረው በቤት ውስጥ በሚያገኙት ግንዛቤ ነው:: ጥቂት ደቂቃ ወስዶ ስለትራፊክ ደህንነት መማማር የህይወት ዘመን ጸጸትን ይከላከላል።

ኪዲፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የተጎጂዎች ድምፅ🔈ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኪዲ ፋውንዴሽን ተከታታዮች እንደምን ሰንብታችኋል፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያ...
12/08/2025

የተጎጂዎች ድምፅ🔈

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኪዲ ፋውንዴሽን ተከታታዮች እንደምን ሰንብታችኋል፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ፕሮግራሞችን ሲያደርግ ቆይቷል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቀን 26-11-2017 ዓ.ም በተደረገ ፕሮግራም የጉዳዩ አሳሳቢነትና ጉዳት በቅርበት ከሚመለከቱ ከአዲስ አበባ የትራፊክ ፖሊስ አባላት፣ ከኢንሹራንስ ተቋማት፣ ከሆስፒታሎች ከመጡ ዶክተሮችና ሐኪሞች እንዲሁም የመኪና አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ተጎጂዎች ጋር በመሆን ምክክርና ውይይት ተካሂዷል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ ተጎጂዎች የሕይወት ታርካቸውን አካፍለዋል፡፡ የተጎጂ ቤተሰቦች የጉዳቱ አስከፊነት ከራሱ ከተጎጂ አልፎ ቤተሰብ ላይም ጉዳት እንዳለው አስረድተዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላትም ተጎጂዎችን መንከባከብ፣ ማገዝና ድምፃቸውን መስማት አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁመዋል፡፡
ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን ይህን የሚመስሉ መድረኮችን በማዘጋጀት እጅግ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ቤተሰባዊ በሆነ መልኩ ተለዋውጠናል፡፡ እርስዎም ድርጅታችን በሚያደርገው ማንኛውም የትራፊክ አደጋ የመቀነስ እንቅስቃሴ አባል በመሆንና በመሳተፍ የተሻለ ነገን አብረን እንገንባ እያልን ጥሪ እናቀርባለን!

ኪዲ ፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የሰውን ልጅ ህይወት በሽርፍራፊ ሰከንድ ወደልተጠበቀ መንገድ ሊቀይር ከሚችል አደጋ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የመኪና አደጋ ነው፡፡ ለዚህ አስደንጋጭ አደጋ መድረስ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ አ...
21/07/2025

የሰውን ልጅ ህይወት በሽርፍራፊ ሰከንድ ወደልተጠበቀ መንገድ ሊቀይር ከሚችል አደጋ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የመኪና አደጋ ነው፡፡ ለዚህ አስደንጋጭ አደጋ መድረስ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ደግሞ ከተፈቀደው ፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ነው:: ፍጥነት ላይ ያለን መኪና በተፈለገው መልኩ መቆጣጠር እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ጥቂት ደቂቃዎችን ለማትረፍ ስንል የትራፊክ ደንብ ተላልፈን ከፍጥነት ወሰን በላይ እናሽከረክራለን፡፡ ጥቂት ሰከንዶችን እንደሄድን ደግሞ ያልጠበቅነው ነገር በመንገዳችን ላይ ያጋጥመናል፡፡ የመኪናችን ፍሬን አለመታዘዝ ወይም ሌላ ብልሽት፣ የመንገዱን ግራኛ ቀኝ ሳያይ እንደመጣ የሚያቋቋጥ እግረኛ፣ ከመንገድ ጠርዝ ተደናብሮ የሚገባ እንስሳት፣ አሊያም እንደ እኛ ሞገደኛ የሆነ አሽከርካሪ ከፊት ለፊታችን ያጋጥመናል፡፡ የተሸከርካሪያችን የፍጥነት ወሰን በልኩ የተገደበ ስላልነበር ለእነዚህ አደጋዎች ሁሉ ተጋላጭ እንሆናለን፡ የደረሰብን አደጋም የወገኞቻችን ወይም የእኛ ሕይወት መጥፋት አሊያም አካል ጉዳት ምክንያት ይሆናል፡፡
ከምናተርፈው ጥቂት ደቂቃ ይልቅ የምናተርፈው የሰው ልጅ ህይወት ዋጋው እጅግ የከበረ ነው!

ኪዲፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የተሸከርካሪ አደጋ የሚያስከትለው ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን እነዚህንም ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ከዚሁ ጋ...
18/07/2025

የተሸከርካሪ አደጋ የሚያስከትለው ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን እነዚህንም ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ትምህርቶች ለተለያዩ የህብረተሰብ አካላት በመስጠት፣ አብሮ መስራት የሚችሉ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማበረታት አደጋዎችን የመቀነስ ስትራቴጂን መሬት ላይ በማውረድና ተግባር ተኮር በማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረጋችን ለውጥ ማየት ጀምረናል፡፡
ይህም ለተማሪዎች እንዲሁም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት ብሎም ለተጎጂዎች የስራ እድል በመፍጠር እና የስነ ልቦና ድጋፍ በማድረግ አዕምሯቸው ብቁ ሆኖ ከሕብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ውጤታማና አምራች እንዲሆኑ የሚታይ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን!
ኑ! አብረን የወገኖቻችንን ሕይወት እንታደግ!!

ኪዲፋውንዴሽን

ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የተሸከርካሪ አደጋ ዘር፣ ቀለም፣ ጎሳ፣ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ  ሳይለይ በሰፊው ማበረሰብ ላይ ከባድ አደጋ እያስከተለ ይገኛል፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን ይህን በመረዳት  ለሁሉም የህብረ...
16/07/2025

የተሸከርካሪ አደጋ ዘር፣ ቀለም፣ ጎሳ፣ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ ሳይለይ በሰፊው ማበረሰብ ላይ ከባድ አደጋ እያስከተለ ይገኛል፡፡ ድርጅታችን ኪዲ ፋውንዴሽን ይህን በመረዳት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች አደጋው የሚመጣበትን መንስኤ፣ የሚያስከትለውን መዘዝና አደጋው ሲደርስ ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለብን ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችን ይሰራል:: ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ማለትም የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የሚዲያ አካላት እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች ጋር በትብብርና በጋራ መስራት አደጋውን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ድርጅታችን በፅኑ ያምናል:: በመሆኑም እርስዎም እየሰራን ያለውን ስራ ቢሮአችን መጥቶ እንዲያዩ፣ ዌብሳይታችንን እንዲመለከቱና የዚህ ስራ አካል በመሆን ህይወትን እንዲታደጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ኪዲፋውንዴሽን

ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የሰው ልጅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲሰራ ጤናማ መሆንና በቂ እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ የሚዳክሩ የሀገር አቋራጭ ሹፌሮች ሁሉም ባይሆኑም አንዳንዶች ቀንና ሌሊት ነቃ ብለው ረጅም ርቀ...
01/07/2025

የሰው ልጅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲሰራ ጤናማ መሆንና በቂ እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ የሚዳክሩ የሀገር አቋራጭ ሹፌሮች ሁሉም ባይሆኑም አንዳንዶች ቀንና ሌሊት ነቃ ብለው ረጅም ርቀት ለመጓዝ ሲሉ ጫትን ሲጠቀሙ እንመለከታለን፡፡: ነገር ግን በአግባቡ ያላረፈ አዕምሮ ለአደጋ የዳረጋቸውና ያሰቡበት ሳይደርሱ ከመንገድ የቀሩ ብዙዎች ናቸው:: ከተማ ውስጥም ቢሆን ከጠጡ አይንዱ የሚለውን የትራፊክ ህግን በመተላለፍ የሚመዘገቡ አደጋዎች ብዙ ናቸው:: መጠጥ ድፍረት ያለብሳቸው ሹፌሮች መሪ ሲጨብጡ አደጋዎች ተከስተው የብዙዎች ደስታ ወደ ሀዘን ተቀይሮ ተመልክተናል፡፡ መዝናናት ካሰቡ ቅድምያ ለደህንነትዎ በመስጠት በሹም ሹፌር ቢጠቀሙ ራስዎንም ህብረሰቡን ከአስከፊ አደጋ መከላከል ይችላሉ!
ደህንነትዎ ያሰስስበናል!

ኪዲፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ

ባለማስተዋል መኪናችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ነገሮች በህይወታችን ላይ እንዲሁም በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት እንደሚያስከትሉ ያውቃሉ? መኪናችን ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚገኙ የእሳት መከላከያ (ማጥፊያ...
30/06/2025

ባለማስተዋል መኪናችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ነገሮች በህይወታችን ላይ እንዲሁም በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት እንደሚያስከትሉ ያውቃሉ?
መኪናችን ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚገኙ የእሳት መከላከያ (ማጥፊያ)፣ እንደሽቶና ላይተር ነገሮችን ስናስቀምጥ በመኪናው መስታወት በኩል የፀሐይ ብርሃን በሚያገኝበት ወቅት ፍንዳታ ሊያጋጥም ይችላል።
ይህም በመኪናው ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እንደ ፍንዳታው መጠን ከቀላል እስከ ከባድ አደጋ ከማስከተል አንስቶ ንብረት ላይ ጉዳት ያደርሳል::
ስለዚህ ፀሐያማ በሆነ ወቅት ረጅም ኪሎሜትሮችን ስናቋርጥ እንዲሁም መኪናችንን በምናቆምበት ጊዜ የመስታወት መሸፈኛ መጓረጃዎችን በመጠቀም እንዲሁም ተቀጣጣይ ነገሮችን የፀሐይ ብርሃን ከሚያገኝበት ቦታ በማራቅ ራሳችንን ከአደጋ እንከላከል!!

ኪዲፋውንዴሽን
ደህንነትዎ ያሳስበናል!

"የእግረኞች መብትና ግዴታ" -    እግረኞች በዜብራ መንገድ መሻገርና በየትኛውም አካባቢ ሲጓዙ የእግርኛ መንገዶችን የመጠቀም መብት አላቸው፣ -   መንገዶችን በሚያቋርጡበት ጊዜ ለእግረኞች ...
26/06/2025

"የእግረኞች መብትና ግዴታ"
- እግረኞች በዜብራ መንገድ መሻገርና በየትኛውም አካባቢ ሲጓዙ የእግርኛ መንገዶችን የመጠቀም መብት አላቸው፣
- መንገዶችን በሚያቋርጡበት ጊዜ ለእግረኞች የተሰየሙ የእግረኛ ማቋረጫዎችን የመጠቀም መብት አላቸው::
- እግረኞች የትራፊክ መብራቶችን ፈቃድ ሲያገኙ እንደ መራመድ እና መንገድ የማቋረጥ መብት አላቸው።
- እግረኞቹ መንገድ በሚያቋርጡበት ጊዜ በተቻለ መጠን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሆን አለበት፣
ለማቋረጥ ካልሆነ በቀር መንገድ ላይ አለመቆየት እና ስራ ባለመስራት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፣
- የሰው ልጅ የመንገድ ደህንነት ደንብ አክብሮ ቢጓዝ እንኳን ምናልባት አሽከርካሪዎች ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አደጋ ሊገጥማቸው ስለሚችል እግረኞች ሁል ጊዜ በንቃት በመጓዝ ጥንቃቄ ማድረግ እና በመንገድ ላይ እያሉ ለደህንነታቸው የግል ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፣

ኪዲፋውንዴሽን
ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

የአሽከርካሪ መልካም ባህሪ ለህይወት ደህንነት!!!በሰው ልጅ ላይ የተሽከርካሪ አደጋ እንዳይከሰት በሰላም ወቶ በሰላም እንዲገባ የአሽከርካሪው እና የእግረኛው መልካም ባህሪ እንዲሁም ለህግ ተገ...
10/06/2025

የአሽከርካሪ መልካም ባህሪ ለህይወት ደህንነት!!!

በሰው ልጅ ላይ የተሽከርካሪ አደጋ እንዳይከሰት በሰላም ወቶ በሰላም እንዲገባ የአሽከርካሪው እና የእግረኛው መልካም ባህሪ እንዲሁም ለህግ ተገዢነት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ አለው:: ትክክለኛ ፐርሰንቱን ማስቀመጥ ባይቻልም ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ከሰማንያ ፐርሰንት በላይ አደጋን መከላከል የሚቻለው በአሽከርካሪ መልካም ባህሪና በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ነው:: ተሽከርካሪዎች በአሽከርካሪዎች አዕምሮና ጠባይ የሚዘወሩ ግዑዝ አካላት ናቸው፡፡ ስለሆነም የአሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲሁም የተሽከርካሪ የደህንነት ፍተሻ እና የአሽከርካሪው መልካም ባህሪ ተደማምሮ አደጋዎችን ለመከላከል ብሎም ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

መልካም ያልሆኑ ባህሪዎቻችንን በየቀኑ በማረም ለህይወታችን ደህንነት እንቁም!
ኪዲፋውንዴሽን

ለሕይወት ቅድምያ እንስጥ!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidy Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kidy Foundation:

Share