Ethiopian Wildlife Conservation Authority

Ethiopian Wildlife Conservation Authority Guardians of the Wild and Native!

The Ethiopian Wildlife Conservation Authority is established under proclamation number 575/2008 having the responsibility to undertake appropriate conservation and development of wildlife for its sustainable use, under the mission “To develop and conserve scientifically Ethiopia’s Wildlife resources and protected areas through active participation of community and other stakeholders, to bring ecological, economic and social benefits for Ethiopians as well as the global community and pass them to the next generation as a heritage.”

መልካም ዕድል ለሬንጀሮቻችን።ዛሬ wildlife Ranger challenge የመጨረሻው የውድድር ቀን ነው። ለ Game Rangers Association of Africa ውድድር በአቢጃታ ሻላ Ab...
19/09/2026

መልካም ዕድል ለሬንጀሮቻችን።
ዛሬ wildlife Ranger challenge የመጨረሻው የውድድር ቀን ነው። ለ Game Rangers Association of Africa ውድድር
በአቢጃታ ሻላ Abijatta-Shalla National Park
ሬንጀሮቻችን 22 ኪሎ ግራም ተሸክመው 21 ኪሎ ሜትር ርቀት ፈታኝ ጉዞ ያደርጋሉ።
በአፍሪካ የተለያዩ ብሔራዊ ፓርኮች ውድድሩ ይካሄዳል። መልካም ዕድል!

19/09/2026
18/09/2026

መልካም ዕድል ለሬንጀሮቻችን!

New Egg-Eating Snake Species Discovered in Ethiopia’s Harenna ForestA new species of harmless egg-eating snake, Dasypelt...
18/09/2026

New Egg-Eating Snake Species Discovered in Ethiopia’s Harenna Forest

A new species of harmless egg-eating snake, Dasypeltis albigularis, has been discovered in the Harenna Forest of Bale Mountains National Park, Ethiopia.

Known as the white-throated egg-eater, the species belongs to the African genus Dasypeltis, which feeds exclusively on birds’ eggs. It has distinctive white throat and belly markings and has been recorded in dense forest at elevations of 1,500–1,700 metres above sea level.

The discovery further highlights the exceptional biodiversity and scientific importance of Bale Mountains National Park and the Harenna Forest, one of the remaining large natural forests in the Horn of Africa.
For detail, see www.Phys.org

ለልጆች የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ የህፃናት ማቆያ ማዕከልመስከረም 07/2019 ዓ.ምኢ.ዱ.ጥ.ባየኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለሴት ሠራተኞቹ የሥራ ሁኔታን  ለማጣጣም ያስችል...
18/09/2026

ለልጆች የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ የህፃናት ማቆያ ማዕከል

መስከረም 07/2019 ዓ.ም
ኢ.ዱ.ጥ.ባ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለሴት ሠራተኞቹ የሥራ ሁኔታን ለማጣጣም ያስችል ዘንድ ከአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያቋቋመው የህፃናት ማቆያ ማዕከል በዛሬው ዕለት አምስት ህፃናትን በምርቃት ሸኝቷል።

በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 መሠረት በባለስልጣኑ ተቀጥረው ለሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ከአራት ወር እስከ አራት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናት ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያስችለው የህፃናት ማቆያ ማዕከል በሥራና ላይ ለሚከሰቱ ተግዳሮቶች መፍትሔ ከማበጀት ባለፈ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያግዝ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የማቆያ ማዕከሉ የአራት ዓመት ዕድሜ የሞላቸውን አምስት ህፃናት በመንከባከብ የቆይታቸውን ጊዜ በማጠናቀቅ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን መኮንን እና በአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዳኛው ገብሩ በተገኙበት የምርቃትና የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ በተለይም ሴት ሠራተኞች የሥራ ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ወቅት ልጆቻቸው በተገቢው እንክብካቤ ስር እንዲሆኑ በማድረግ የሥራ ቦታ ላይ የሚያጋጥሙ መቅረት፣ የትኩረት መቀነስና የሥራ ቅልጥፍና መዳከም የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

የዛሬ ህፃናት የነገ ትውልድ መሪዎችና ባለሙያዎች በመሆናቸው፣ ለደህንነታቸው፣ ለእድገታቸውና ለትምህርታቸው የሚደረግ ድጋፍ የነገን ብሩህ ተስፋ የመገንባት አካል ነው። የህፃናት ማቆያ ማዕከሉም የሠራተኞችን የሥራ አቅም ከማጠናከር ባለፈ ለህፃናት የተሻለ እድገትና የወደፊት ተስፋ ለመፍጠር የሚያበረክት ተግባራዊ እርምጃ ነው።

18/09/2026
𝐒𝐢𝐦𝐢𝐞𝐧 𝐌𝐨𝐮𝐧𝐭𝐚𝐢𝐧𝐬 𝐍𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐏𝐚𝐫𝐤Dramatic landscapes meet extraordinary wildlife resources, a breathtaking view of Ethiopia...
16/09/2026

𝐒𝐢𝐦𝐢𝐞𝐧 𝐌𝐨𝐮𝐧𝐭𝐚𝐢𝐧𝐬 𝐍𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐏𝐚𝐫𝐤

Dramatic landscapes meet extraordinary wildlife resources, a breathtaking view of Ethiopia’s highlands, showcasing the park’s rugged mountains, lush vegetation, and iconic high-altitude flora.

የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ውይይት ተካሄደ።መስከረም 4/2019 ዓ.ም አዳማየኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከባለድርሻ እና አጋር አካላ...
14/09/2026

የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ውይይት ተካሄደ።

መስከረም 4/2019 ዓ.ም
አዳማ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ያዘጋጀው የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ የውይይት መድረክ አጋር አካላትን ጨምሮ የፓርክ ሀላፊዎችና ተወካይ እንዲሁም ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ተካሄዷል።

መድረኩን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በመልዕክት የከፈቱ ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም የጋራ ዕዳችንን ለማሳካት በተደረገው ርብርብ መልካም ውጤቶች እንደተገኙና ተግዳሮቶችም እንደነበሩ በመግለፅ በቀጣይም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በማቀድና በመስራት የጥበቃ ሥራውን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩም የተቋሙ እና የአጋር አካላት የዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በውይይቱም የተቋሙን የጥበቃ ሥራ ማዘመንና ዲጂታላይዜሽን፣ የጥናትና ምርምር፣ የአቅም ማጎልበቻና የግንባታ ሥራዎችን ማጠናከር፣ ከክልል ፓርኮችና አጋር አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንዲሁም የማህበረሰብ ግንዛቤና የሕግ ማስከበር ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ሀሳቦች ቀርበዋል።

ውይይቱን የመሩት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን መኮነን ሲሆኑ፣ የተነሱ ሀሳቦችን በመቀበል እንደ ተቋም የተሻለ ስራ እንደሚሰራ በመግለፅ በተቋም ደረጃ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በዕቅድ፣ በሪፖርትና በትብብር ከሁሉም አካላት ጋር በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን።

በተለይም የጥበቃ ሥራውን ለማጠናከር ማህበረሰቡን ከፊት በማስቀደም ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከርና የአጋር አካላትን ድጋፍ ማስፋት አስፈላጊነቱ በሰፊው የተጠቀሰ ሲሆን መድረኩም በ2019 ዓ.ም የተሻለ የጋራ ዕቅድና አፈጻጸም ለማስመዝገብ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ በመልካም የሥራ ዘመን ምኞት ተጠናቋል።

Ethiopian Wildlife Conservation Authority
60 Years for Ethiopian wildlife

የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ውይይት ተጀመረ።መስከረም 4/2019 ዓ.ምአዳማ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከባለድርሻ እና አጋር አካላ...
14/09/2026

የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ውይይት ተጀመረ።

መስከረም 4/2019 ዓ.ም
አዳማ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ያዘጋጀው የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ የውይይት መድረክ የተለያዩ አጋር አካላት በተሳተፉበት በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

መድረኩን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በመልዕክት የከፈቱት ሲሆን፣
በመድረኩም ላይ አጋር አካላትን ጨምሮ የብሔራዊ ፓርኮች ሀላፊዎች እና ተወካዩች እንዱሁም ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በሚኖረው ቆይታም የተፈጥሮ ሀብቱ ሊጠበቅ በሚችሉባቸው አሰራሮች ዙሪያ የጋራ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ ይጠበቃል።

Ethiopian Wildlife Conservation Authority
60 Years for Ethiopian wildlife

የኢትየጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ ፣ ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ እያለ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና  የእድገት ይሆንላችሁ ዘንድ...
10/09/2026

የኢትየጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ ፣ ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ እያለ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የእድገት ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
መልካም አዲስ ዓመት!
የኢትየጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን!

Address

Head Office, Mexico Square
Addis Ababa
386

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115504838

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Wildlife Conservation Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share