Scripture Union Ethiopia

Scripture Union Ethiopia የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)

Serving God's Vision for Middle and High School Students
"ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት"

ዓመታዊ ብሔራዊ የስታፍ ስብሰባ እና የእቅድ ጊዜ!​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) ዓመታዊ የስታፍ ስብሰባ እና የቀጣይ ዓመት የእቅድ ጊዜ እጅግ በተባረከ ሁኔታ ተካሂ...
22/09/2026

ዓመታዊ ብሔራዊ የስታፍ ስብሰባ እና የእቅድ ጊዜ!

​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) ዓመታዊ የስታፍ ስብሰባ እና የቀጣይ ዓመት የእቅድ ጊዜ እጅግ በተባረከ ሁኔታ ተካሂዷል። በነበረን ቆይታ ያለፈውን ዓመት አገልግሎት ስንገመግም፣ ለቀጣይም ስንጸልይ እና ስልታዊ እቅዶችን ስናዘጋጅ ቆይተናል።
​
በዚሁ መድረክ ራዕያችንን ተካፍለው የተቀላቀሉ አዳዲስ የስታፍ አባላትን በታላቅ ደስታ ተቀብለናል!

​በወጣው እቅድ መሠረት ራዕያችንን ከዳር እንድናደርስ፣ እንዲሁም ለአዳዲስ አገልጋዮቻችን ጌታ ጸጋውን እንዲያበዛላቸው በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!

​የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
​🌐

11/09/2026

የየዕለቱ ብርሃን

The Scripture Union Ethiopia team has safely returned from the SU Africa Bible Engagement Consultation, bringing home ri...
17/08/2026

The Scripture Union Ethiopia team has safely returned from the SU Africa Bible Engagement Consultation, bringing home rich insights, practical strategies, and shared experiences from across the continent.
We praise God for the inspiring commitment witnessed among SU movements to deepen God's Word in the lives of children, youth, and adults. Equipped with fresh vision and renewed passion, the team is eager to implement these lessons to strengthen Bible engagement and ministry impact across Ethiopia. 🙏

የደቡብ ምስራቅ (ሀዋሳ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በደቡብ ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በሀዋሳ ከተ...
17/08/2026

የደቡብ ምስራቅ (ሀዋሳ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በደቡብ ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በሀዋሳ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።
በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የደቡብ ምስራቅ እና አጎራባች አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች በንቃት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቻችንም ከሚከተሉት ከተሞች እና ስፍራዎች የመጡ ነበሩ፦
▪️ ከሲዳማ እና አካባቢው፦ ሀዋሳ፣ ይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ አለታ ጩኮ፣ ቦሩ፣ ዶሬ እና አርቤጎና
▪️ ከጌዴኦ እና አካባቢው፦ ዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ጓንጓ፣ ቺቹ እና ወንዶ ወሻ
▪️ ከምዕራብ አርሲ እና ባሌ፦ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ ኩየራ፣ ዶዶላ፣ አሳሳ፣ አዳባ እና ባሌ ጎባ
▪️ ከቦረና፣ ጉጂ እና ሌሎችም፦ ቡሌ ሆራ፣ ያቤሎ፣ ፊንጨዋ፣ ኤልወዬ፣ ለኩ፣ ዳራካባሎ፣ ተፈሪኬላ፣ ወርቃ እና ሱርጷ
📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦
በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦
🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method)
🔹 አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)
🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ራዕይ (Highschool Vision)
🔹 ሚዛን የጠበቀ ህይወትና አገልግሎት (Balanced Life and Ministry)
🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦
እነዚህ የተማሪ መሪዎች በቃሉ ታንጸው ወደየ ትምህርት ቤቶቻቸው ሲመለሱ በትምህርት ቤቶቻቸው ብርሃን ሆነው እንዲያበሩ፣ በጓደኞቻቸውም ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በቀጣይ አገልግሎታቸው ሁሉ ጌታ አብሮአቸው እንዲሆን በጸሎት እንድታስቧቸው አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
🌐
#ሀዋሳ

የምስራቅ (ድሬዳዋ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል! የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በድሬዳዋ ከተማ ያስተ...
16/08/2026

የምስራቅ (ድሬዳዋ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በድሬዳዋ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች በንቃት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቻችንም ከሚከተሉት ከተሞች እና ስፍራዎች የመጡ ነበሩ፦

▪️ ከድሬዳዋ እና ሁርሶ
▪️ ከሐረር፣ ባቴ፣ ሀሮማያ እና አደሌ
▪️ ከጅግጅጋ እና ባቢሌ
▪️ ከጭሮ፣ በዴሳ፣ ካራሚሌ እና ጨለንቆ

📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦
በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦
🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method - BSM)
🔹 የሃይስኩል ራዕይ ማብራሪያ (Highschool Vision Illustration)
🔹 የእግዚአብሔር ልብ ለሃይስኩል (God's Vision for Highschool)
🔹 የቤተሰብ ቡድን (Family Group)
🔹 ራስን ማሳደግ (Self Development)

🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦
እነዚህ የተማሪ መሪዎች ወደየ ትምህርት ቤቶቻቸው ተመልሰው በትምህርት ቤቶቻቸው ብርሃን ሆነው እንዲያበሩ፣ በጓደኞቻቸውም ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ፣ በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)

🌐
#ድሬዳዋ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ሆሳዕና) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል! የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው...
10/08/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ሆሳዕና) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በሆሳዕና ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዞኖች እና አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች በንቃት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቻችንም ከሚከተሉት ዋና ዋና ከተሞች እና ዙሪያ የመጡ ነበሩ፦
▪️ ከሆሳዕና እና አካባቢዋ (ከሀዲያ ዞን)
▪️ ከዱራሜ (ከከምባታ ጠምባሮ ዞን)
▪️ ከሀላባ ቁሊቶ (ከሀላባ ዞን)
▪️ ከወራቤ (ከስልጤ ዞን)
▪️ ከወልቂጤ (ከጉራጌ ዞን)
▪️ ከቡታጅራ (ከምስራቅ ጉራጌ ዞን)
📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦
በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦
🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method)
🔹 አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)
🔹 የቤተሰብ ቡድን (Family Group)
🔹ወዳጃዊ ወንጌል የመጋራት ስልት (PCS)
🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦
እነዚህ የተማሪ መሪዎች ወደየ ትምህርት ቤቶቻቸው ተመልሰው በትምህርት ቤቶቻቸው ብርሃን ሆነው እንዲያበሩ፣ በጓደኞቻቸውም ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ (ሀዋሳ) እና በምስራቅ (ድሬዳዋ) ለሚኖረን ቀጣይ ጉባኤ በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
🌐
#ሆሳዕና

የደቡብ ኢትዮጵያ (ወላይታ ሶዶ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በወላይታ ሶዶ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም...
10/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ (ወላይታ ሶዶ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!
​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በወላይታ ሶዶ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።
​በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች በንቃት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቻችንም ከሚከተሉት ስፍራዎች የመጡ ነበሩ፦
​▪️ ከጂንካ
▪️ ከአርባምንጭ እና አካባቢዋ (ጨንቻ)
▪️ ከጎፋ ሳውላ
▪️ ከኮንሶ
▪️ ከታርጫ
▪️ እንዲሁም ከሶዶ እና አካባቢዋ
​📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦
በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦
🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method)
🔹 አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)
🔹 ሚዛን የጠበቀ ህይወትና አገልግሎት (Balanced Life and Ministry )

​🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦
እነዚህ የተማሪ መሪዎች ወደየ ትምህርት ቤቶቻቸው ተመልሰው በትምህርት ቤቶቻቸው ብርሃን ሆነው እንዲያበሩ፣ በጓደኞቻቸውም ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ፣ እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ (ሀዋሳ) እና በምስራቅ (ድሬዳዋ)ለሚኖረን ቀጣይ ጉባኤ በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
​የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
​🌐
#ወላይታሶዶ

የምዕራብ (ነቀምቴ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል! የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በምዕራብ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በነቀምቴ ከተማ ያስተ...
02/08/2026

የምዕራብ (ነቀምቴ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) በምዕራብ ክልላዊ ቢሮ ማዕከል በሆነችው በነቀምቴ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የምዕራብ አካባቢዎች የተውጣጡ የተማሪ መሪዎችና አገልጋዮች (Associates) በንቃት ተሳትፈዋል።

📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦ በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) ከነበረን ጥናት በተጨማሪ፣ የተማሪዎችን እና የአገልጋዮችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ የሚከተሉት ስልጠናዎች (Seminars) ተሰጥተዋል፦ 🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህብረት መሪነት (Highschool Fellowship Leadership) 🔹 ተልዕኳዊ ህብረት (Missional Fellowship) 🔹 የአገልጋዮች አገልግሎት (Associate Ministry) 🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method)

🚀 ቀጣይ ርምጃችን፦ ይህንኑ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ ይዘን ወደ ቀጣይ የጉባኤያችን መዳረሻዎች፦
📍 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፡ ሆሳዕና
📍 በደቡብ ኢትዮጵያ፡ ወላይታ ሶዶ
በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
🌐
#ነቀምቴ

Yaa'iin Hooggantoota Barattootaa Naannoo Lixaa (Neqemtee) ayyaana Gooftaatiin xumurameera!

Tokkummaa Dubistoottaa Sagalee Waaqayyoo Itoophiyaa (SUE) wiirtuu waajjira naannoo Lixaa kan taate magaalaa Neqemteetti Yaa'ii Hooggantoota Barattoota Sadarkaa Lammaffaa Naannoo (SUE-RHLS) bara 2018 kan qopheesse haala eebbifamaa fi milkaa'aa ta'een xumurameera.

Yaa'ii guddaa kana irratti hooggantoonni barattootaa fi tajaajiltoonni (Associates) naannawa Lixaa garaa garaa irraa dhufan dammaqinaan hirmaataniiru.

📖 Qorannaa Sagalee fi Seminaarota: Turtii keenyatti mata duree "Jireenya Ergamummaa : Tokkummaa Ergamummaa" jedhuun (Macaafa Qorontos 1ffaa irratti) qorannaa taasisneen dabalata, mata dureewwan dandeettii barattootaa fi tajaajiltootaa ijaaran irratti leenjiiwwan (Seminars) armaan gadii kennamaniiru፦ 🔹 Hooggansa Tokkummaa Mana Barumsaa Sadarkaa 2ffaa (Highschool Fellowship Leadership) 🔹 Tokkummaa Ergamummaa (Missional Fellowship) 🔹 Tajaajila Tajaajiltootaa (Associate Ministry) 🔹 Mala Qorannaa Macaafa Qulqulluu (Bible Study Method)

🚀 Tarkaanfii keenya itti aanu: Yaa'ii hooggantoota barattootaa kana qabachuun gara iddoowwan yaa'ii keenya itti aanutti imalla፦ 📍 Itoophiyaa Giddugaleessaatti: Hosaa'inaa
📍 Itoophiyaa Kibbaatti: Walaayittaa Sooddoo
Kadhannaan akka nu yaadattan isin gaafanna!

Tokkummaa Dubistoottaa Sagalee Waaqayyoo (SUE)

🌐

የሰሜን ምዕራብ (ባህርዳር) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) የሰሜን ምዕራብ ክልላዊ ቢሮ ማእከል በሆነችው በባህር...
31/07/2026

የሰሜን ምዕራብ (ባህርዳር) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!

​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) የሰሜን ምዕራብ ክልላዊ ቢሮ ማእከል በሆነችው በባህርዳር ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።

​ይህ ታላቅ ጉባኤ በአጠቃላይ ከ14 ከተሞች እና ከ36 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ወጣቶችን፣ መሪዎችንና አገልጋዮችን (Associates) ያገናኘ ስትራቴጂካዊ መድረክ ነበር።

የተሳታፊዎቹ ስብጥርም የሚከተለውን ይመስላል፦

ከደቡብ ጎንደር፦ አዲስ ዘመንና ወረታ፤

ከምስራቅ ጎጃም፦ ደብረ ማርቆስና ቢቸና፤

ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፦ አዲስ ቅዳምና ዳንግላ፤

ከምዕራብ ጎጃም ዞን፦ ከፍኖተ ሰላም፣ ቡሬና ጣቦ፤

ከሰሜን ጎጃም፦ አዴት፣ ዱር ቤቴና መራዊ እና
ከባህርዳር

ተልዕኳዊ ህይወትና ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) የቃል ጥናት አድርገናል።

በተጨማሪም የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናዎች እና አገልግሎት ተኮር ውይይቶች ተካሂደዋል።

ሴሚናሮች፦
ኦርቶዶክስን መረዳት (Understanding EOTC)
የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ (BSM)
የትምህርት ቤት ህብረት አመራር (Fellowship leadership)
የእግዚአብሔር ልብ ለኃይስኩል (God's Vision for Highschool)
ወዳጃዊ የወንጌል ምስክርነት (PCS)

​የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
​
#ባህርዳር

Address

Https://maps. App. Goo. Gl/n5r8toGSyMExEnU 37
Addis Ababa
30723

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Scripture Union Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share