Addis Ababa Trade Bureau

Addis Ababa Trade  Bureau Addis Ababa Trade Bureau
(1)

19/05/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ
12/9/ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡ እና በማደያዎቹ በመሰራጨት ላይ ያለው የተሽከርካሪዎች ናፍጣና ቤንዚን አቅርቦት መጠን መረጃ:-

19/05/2026
ባለፉት አምስት አመታት በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን ማሳደግና የንግድ ስርዓቱን ማዘመ በመቻሉ የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል፡፡ግንቦት11/2018 ዓ.ምየአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ...
19/05/2026

ባለፉት አምስት አመታት በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን ማሳደግና የንግድ ስርዓቱን ማዘመ በመቻሉ የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል፡፡

ግንቦት11/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ ከሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ ጋር በንግድ ዘርፍ ስራዎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እና የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመኑ በጋራ መርተውታል።

ከመድረክ ባለፉት አምስት አመታት በንግደ ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተገኙ ቱርፋቶችን በቢሮው የንግድ ጥናትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ባለፉት አምስት አመታት 16 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ኦንላይን እንዲሰጡ በማድረግ ከሙስና የፀዳ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።

እንደ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገለፃ በከተማችን አዲስ አበባ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ በከተማችን አዲስ አበባ ምርት አቅርቦት ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰራቱ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የቀጥታ ግብይት አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ሰው ሰራሽ በሆነ አሰራር የምርት እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የምርቶችን ዋጋ የሚጨምሩ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገያው በማስወጣት ምርቶች ከአምራቹ በቀጥታ ወደ ከተማው የሚገባበትን ሥርዓት ተዘርግቷል ብለዋል።

ባለፉት አመታት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት ከመፍጠር አንፃር መንግስት የአደባባይ ላይ ባዶ ቦታዎችን በመፍቀድ እና ከአርሶ አደሩ ጋር ቀጥታ ትስስር በማመቻቸት 259 የእሁድ ገበያዎች ተከፍተው ምርቶችን ከመደበኛው ገበያ 20 በመቶ ቅናሽ ለህብረተሰቡ በመቅረብ ላይ ይገኛሉም ብለዋል፡፡

የእሁድ ገበያዎችን ስራ ከማስጀመር ባሻገር በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት በኩል ዘይትና ስካርን በድጎማ በማቅረብ በከተማችን አዲስ አበባ የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አንፃር ትርጉም ያለው ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

ገበያውን ለማረጋጋት ከተሰሩ ስራዎች መካከል የአዲስ አበባ ንግድ ስራዎች ድርጅት እንዲቋቋም በማድረግ መሰረታዊ ፍጆታ ምርቶችን ከአምራቹ በቀጥታ በመግዛት በአዲስ አበባ ለሚገኙ መሰረታዊ የህረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች በማሰራጨት እንዲሁም ድርጅቱ ባሉት የመሸጫ ሱቆች አማካኝነት ምርቶችን ከነጻ ገበያው በቀነሰ ዋጋ ማሰራጨት ተችሏል፡፡

ሌላው አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ሊፈትን ይችላል ተብሎ የሚታሰበው የዳቦ ዋጋና አቅርቦት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ 29 የዳቦ ማምረቻ ቦታዎችን ለባለሀብቶች 10 ዓመት እንዲገለገሉበት በነፃ መስጠት በመቻሉ ዳቦን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሰባት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው የከተማችንን የግብይት ስርዓት ፍትሃዊና የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

አዲስ አበባን የአፍሪካ ፈር ቀዳጅ ያደረጋት የምገባ ፕሮግራም ስኬትበአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም በከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል። ...
19/05/2026

አዲስ አበባን የአፍሪካ ፈር ቀዳጅ ያደረጋት የምገባ ፕሮግራም ስኬት

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም በከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል።

ይህ ፕሮግራም በሀገር ውስጥ ካስመዘገበው ተጨባጭ ውጤት ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ በትላልቅ ተቋማትና ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና እውቅናን አግኝቷል፡፡

ስለፕሮግራሙ ስኬታማነት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምስክርነቶችና እውቅናዎች ተሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና የተለያዩ የጥናት ተቋማት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የምገባ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች ላይ ይስተዋል የነበረው የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

ሌላው በአሜሪካ ብሔራዊ የሕክምና ቤተ-መጻሕፍት (PMC) ላይ በወጣ ጥናት መሰረት፣ የምገባ ፕሮግራሙ ከተጀመረ በኋላ በተማሪዎች ላይ ይታይ የነበረው የመቀንጨር እና የክሳት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡

በተለይም ከ5 እስከ 9 ዓመት ባሉ ሴት ህጻናት ላይ የነበረው የመቀንጨር መጠን ከ12.2% ወደ 7.8% ዝቅ ማለቱን በጥናት መረጋገጡ በጥናቱ ተገልጿል፡፡

ይህ ፕሮግራም ምግብ ለሚያበስሉ፣ ለሚያቀርቡና ለሚያጸዱ በርካታ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶችና ሴቶች በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቋሚ የስራ ዕድል ፈጥሮላቸዋል፡፡

ፕሮግራሙ በትምህርት ቤቶች ከተጀመረው የተማሪዎች ምገባ በተጨማሪ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ያካተተ 29 የህዝብ ምገባ ማዕከላት የተገነቡ ሲሆን፣ ይህም በቀን ከአንድ ጊዜ በላይ መመገብ የማይችሉ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸዉ ዜጎችን ክብር ባለው መልኩ ለመደገፍ አስችሏል።

የአዲስ አበባ የምገባ ፕሮግራም ሰው ተኮር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ700 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተደራሽ ማድረግ የቻለ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረትን ስቧል።

አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራሟ አማካኝነት በ2022 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 133 ከተሞችን በመብለጥ በዘላቂ የአመጋገብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ የ8ኛው የሚላን ከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ወርቃማ ሽልማትን በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ ከተማ በተካሄደው መድረክ አሸንፋለች።

ይህን ሽልማት በማሸነፍም አዲስ አበባ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ ከተማ መሆን ችላለች።

በተመሳሳይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በጥቅምት ወር 2024 የሚላን ከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ሴክሬተሪያት ዋና ኃላፊ ፊሊፖ ጋቫዜኒ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን እና የህዝብ ምገባ ማዕከላትን በአካል ጎብኝተዋል፡፡

ሀላፊው ከጉብኝታቸው በኋላ የአዲስ አበባ የምገባ ፕሮግራም እጅግ የሚያስደንቅ እና ወደ ሌሎች የዓለም ከተሞችም በሞዴልነት ሊወሰድ የሚችል ተሞክሮ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የከንቲባ አዳነች አቤቤ ቁርጠኝነትንም ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ተሞክሮ መሆን አንደሚችል ሀላፊው አክለው አንስተዋል፡፡

በዓለም አቀፉ የኬኒያ የግሎባል አሊያንስ ፎር ኢምፕሩቭድ ኒውትሪሽን ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ማውሪን ሙኬታ በበኩላቸው ፕሮግራሙን ካዩ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ስራው በሀገሪቱ የወደፊት ትውልድ ላይ ትልቅ ኢንቨስትመንት እያደረገ ነው ብለዋል።

ማውሪን ሙኬታ ዛሬ የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኙት እነዚህ ህጻናት የነገዎቹ የሀገሪቱ ዶክተሮች፣ ጠበቃዎች እና መሪዎች ናቸው በማለትም የተሰማቸውን ስሜት ገልጸዋል፡፡
AMN

ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጐን ለጐን የአዘርባጃንን የአሳን ቀላል  የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን (ASAN-Azerbaijan Service and Assessment Network) ጉብ...
19/05/2026

ከዓለም የከተሞች ፎረም ተሳትፎ ጐን ለጐን የአዘርባጃንን የአሳን ቀላል የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን (ASAN-Azerbaijan Service and Assessment Network) ጉብኝተናል።

እኛም እስከአሁን በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያመጣነው ከፍተኛ ለውጥ ቢሆንም፣ አሁንም ልምድ ሊሆኑን በሚችሉ ጉዳዮችም ላይ ውይይት አድርገናል።
ከ14 ዓመታት በፊት የተጀመረው እና በቀን 40ሺህ አፕሊኬሽን ላይ አገልግሎት የሚያሳልጠው አሳን፣ በአውቶቡሶች የሚሰጥ የገጠር አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ የአገልግሎት ማዕከል በተደራጀ፣ ፈጣን ቀላል አገልግሎት ይሰጣሉ ።

በሀገራችን ኢትዮጵያም ከ41 በላይ ማዕከላት ገንብተን ስራ የጀመርን ሲሆን፣ ከዚሁ ውስጥ በአዲስ አበባ 6 ማዕከላት እና 1 ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት እንዳሉን ይታወቃል።

የአሳን ሰራተኞች አገልግሎት ሲሰጡ ፈገግታ እና ትህትና አንዱ የአገልግሎት መለኪያ እንደሆነ፣ የመከታተያ ካሜራዎች የተገጠሙ መሆኑን እና በጥሩ ሁኔታ የሚያገለግል ሰራተኛ ተመዝኖ እና የተገልጋዩ የዕርካታ መጠን ከፍተኛ ከሆነ ከደሞዝ በተጨማሪ ቦነስ እንደሚከፈለው ተመልክተናል። በዛው ልክ በመስፈርቱ መሰረት ያላገለገለ ወዲያው ይባረራል። ለነገ ተስፋ አድገው ህዝባቸውን በከፍተኛ ትጋትና አክብሮት የሚያገለግሉ በርካታ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችንም ተመልክተናል።
የእኛም ቢሮክራሲ በተጀመረው አግባብ ሙሉ በሙሉ እንደሚለወጥ እናምናለን።
እንዲሳካም ተግተን እንሰራለን!!

ፈጣሪ ኢትዮዽያና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

19/05/2026
19/05/2026
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረገው ጉብኝት ፣ ባኩ እጅግ ጽድት ያለችና ማራኪ ከተማ ናት። "ጥንታዊቷ ከተማ" (The Old City) በመባል የሚታወቀው የከተማዋ ክፍል...
19/05/2026

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአዘርባጃን ባኩ ከተማ ያደረገው ጉብኝት ፣

ባኩ እጅግ ጽድት ያለችና ማራኪ ከተማ ናት። "ጥንታዊቷ ከተማ" (The Old City) በመባል የሚታወቀው የከተማዋ ክፍል በጥንቃቄ ታድሶ ለጉብኝት ክፍት ሆኗል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከዚህ ቀደም "ጥቁሯ ከተማ" (The Black City) ይባል የነበረውን አሮጌና ጎስቋላ ስፍራ፣ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማፍረስና እንደ አዲስ በመገንባት፣ አዲሲቷንና ውቢቷን ከተማ "ነጭ ከተማ" (White City-Baku) በሚል ስያሜ እውን ማድረግ ችለዋል።

ይህ የከተማ እድሳት ሂደት የእኛንም ተሞክሮ የሚያንፀባርቅ ነው። እኛም ታሪክንና ቅርሶቻችንን ጠብቀን እያደስን፣ ጎስቋላ አካባቢዎችን ደግሞ አፍርሰን በአዲስ መልክ በመገንባት ላይ እንገኛለን። ለአብነት ያህል፣ ቅርሶችን በማደስና ለቀጣዩ ትውልድ በማሻገር ረገድ፤ በፒያሳ እና በአራት ኪሎ አካባቢ ያሉ ጥንታዊ ሕንፃዎችን፣ የመጀመሪያውን ሲኒማ ቤት፣ የመጀመሪያውን ማዘጋጃ ቤት፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን እንዲሁም የተለያዩ ሐውልቶችን አድሰናል። ከዚህም ባሻገር እንደ ሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና የጎንደር ፋሲል ቤተ መንግሥት የመሳሰሉትን ታላላቅ ቅርሶች በማደስ ላይ እንገኛለን ።

በተጓዳኝም፣ እጅግ ጎስቋላና ለመኖር ምቹ ያልነበሩ መንደሮችን በማፍረስ ዘመናዊና ምቹ በሆነ መልኩ በድጋሚ ገንብተናል። በተለይም በቅርቡ በመዲናችን አዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን ከተሞች በተሳካ ሁኔታ የተተገበረው ሰፊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የዚሁ የከተማ እድሳትና ማስዋብ ራዕያችን ዋነኛ ማሳያ ነው። በዚህም ስራ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ምቹ፣ ማራኪ፣ አረንጓዴ እና ዘመናዊ ለማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ከማስፋት፣ ለእግረኛና ለብስክሌት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን ከመፍጠር እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር አኳያ እጅግ አበረታችና ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቦበታል።

በአጠቃላይ ይህ የባኩ ጉብኝት፣ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የጀመርናቸውን የከተማ ልማት፣ እድሳትና የቅርስ ጥበቃ ስራዎች ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ትልቅ ልምድ የተቀሰመበት ጠቃሚ ጉብኝት ነበር።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Trade Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Trade Bureau:

Share