መቄዶንያ

መቄዶንያ መቄዶንያ ከ4,000 በላይ ወገኖችን ከጎዳና የያነሳ ነው! አያት ፀበል መድሀኒዓለም ፊትለፊት ይምጡና ይጎብኙን!

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ምንም ሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መፀዳዳት፣ መመገብ እና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ከወደቁበት ጎዳና ላይ በማንሳት ኮተቤ ብረታ ብረት አጠገብ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ 40 የሚሆኑ አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት ጎዳና ላይ በማንሳት ስራውን የጀመረ ሲሆን ማዕከሉ ድጋፍ የሚያደርግላቸውን አረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ የዘር፣ የሐይማኖት እና የፆታ ልዩነት ሳይደረግ ደጋፊ ያጡ በመሆናቸው ብቻ ከአካባቢው ነዋሪዎች በሚሰበሰብ መረጃ ከወደቁበ

ት ተነስተው ማዕከሉን ተቀላቅለው የምግብ፣ የአልባሳት፣ የመጠለያና የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ በ2004 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡ ማዕከሉ ስራውን የጀመረበት መኖሪያ ግቢ እየተረዱ የነበሩትን ተገልጋዮች ለማኖር በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ 3 የመኖሪያ ግቢዎችን በአቅራቢያው በመከራየት በወር 50 ሺህ ብር ለቤት ኪራይ ብቻ በማውጣት አገልግሎቱን የቀጠለ ሲሆን በ2007 ዓ.ም በወቅቱ የተረጂዎቹ ቁጥር 700 በነበረበት ወቅት አያት ኮንዶሚንየም አጠገብ 30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ በቦታውም ላይ መኖሪያዎች ተገንብተው በአሁኑ ሰዓት 4,000 በላይ የሚሆኑ ተረጂዎችን እየረዳ ይገኛል፡፡

ማዕከላችንን ልዩ የሚያደርገው ምንም አይነት የውጪ ሀገር እርዳታ ሳይጠቀም ወገኖቻችን ከሆኑ ኢትዮጵያውያን በሚያገኘው እርዳታ ብቻ እየታገዘ በርካታ የተቸገሩ ሰዎችን በተለይም የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ሰዎችን መርዳቱ ሲሆን፤ ይህም በሀገር ውስጥ እርዳታ ብቻ በመታገዝ ብዙ ሰዎችን እየረዳ የሚገኝ ድርጅት ያደርገዋል፡፡

ማዕከሉ ከጎዳና የሚያነሳቸው ወገኖች በቀደምት ህይወታቸው ለሀገሪቷ በተለያዩ የስራ መስኮች ያገለገሉና የሀገር ባለውለታ የሆኑ አባቶችና እናቶች ሲሆኑ በሚደረግላቸው ልዩ እንክብካቤ እና ድጋፍ እንዲሁም የጤና ክትትል በመልካም ሁኔታ ላይ ሲገኙ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማዕከሉን እንዲያገለግሉ ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሙያ ስልጠና አግኝተው አምራች እንዲሆኑ የሚደረግ ሲሆን ቤተሰብ ያላቸውንም ተረጂዎች ቤተሰባቸውን በማፈላለግ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ይደረጋል፡፡ ከተረጂዎቹም መካከል ትላንት የአልጋ ቁራኛ የነበሩ ሰዎች ከጎዳና ተነስተው ዛሬ የማዕከሉ ላብራቶሪ ቴክኒሽያን፣ ሹፌር፣ ልብስ ሰፊ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ገንዘብ ተቀባይ፣ አስጎብኚ፣ ጥበቃ፣ ተንከባካቢ፣ ፅዳት፣ ምግብ አብሳይ፣ ሠዓት ተቆጣጣሪ፣ የኮንስትራክሽን ባለሙያ (አናፂ፣ ግንበኛ…)፣ ጉዳይ አስፈፃሚ፣ የእንጨት ሠራተኛ፣ የብረት ባለሙያ፣ ወዘተ… መሆን የቻሉ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡

call 0979797979

Address

Addis Ababa
CALL8131

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መቄዶንያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to መቄዶንያ:

Share

mekedonia

mekedonia