Voice Of Ethiopia

Voice Of Ethiopia 🌍🇪🇹 "Dive into Ethiopia's Tapestry: News, Culture, and Perspectives."

ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ሄርዞግ፡ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት “ሻባክ”በሃይማኖት ካሳው ፍለጋ ላይ እየተሳተፈ ነው አሉ! የእስራኤል ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ሄርዞግ ከሃይማኖት ካሳው ቤተሰብ ጋር...
25/08/2026

ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ሄርዞግ፡ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት “ሻባክ”በሃይማኖት ካሳው ፍለጋ ላይ እየተሳተፈ ነው አሉ!
የእስራኤል ፕሬዝዳንት ይስሃቅ ሄርዞግ ከሃይማኖት ካሳው ቤተሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ በቀጥታ መሳተፉን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሃይማኖት ፍለጋ እና መረጃዎችን በማጣራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል::

“ሻባክ” ከሀገሪቱ ዋና የደህንነት ተቋም “ሞሳድ” ያልተናነሰ ሀይል እንዳለዉ ይነገራል:: በሁለቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት ተቋማት ያለዉ ብቸኛ ልዮነት “ሻባክ” በሀገሪቱ ዉሰጥ የሚፈፀሙትን ከፍተኛ ወንጀሎች ሲቆጣጠር “ሞሳድ” ደንበር ተሻጋሪ የደህንነት ሰራዎችን ይሰራል! ተብሏል::

ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የ...
25/08/2026

ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን

ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል

ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስቸጋሪ ድርድር ወቅት የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በፅናት የተሞገቱትንና የዲፕሎማሲያዊ ግምባር መሪ የነበሩትን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዛሬ በስደት ሀገር በተራ የመኪና ማቆሚያ ስራ ላይ ተሰማርተው ማየት በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነው።

በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ የነበሩ ሰዎች የህዝብን ሀብት ዘርፈው በውጭ ሀገር ባንኮች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አካብተው በቅንጡ ህይወት ሲኖሩ ማየት በተለመደበት በዚህ ዘመን፣ አቶ ገዱ በስልጣን ዘመናቸው እጃቸውን ከሙስና እና ከሀገር ሀብት ምዝበራ ያቀቡ ታማኝ መሪ መሆናቸውን ዛሬ በራሳቸው ላብና ጥረት ለመኖር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህያው ምስክር ነው።

ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት እና ሀገር ወደድ ወገኖች፣ ይህንን የታማኝነት እና የህሊና ንጽህና አርአያ የሆነ ታላቅ ሰው በሰው ሀገር በጉልበት ስራ እንዲንገላታ መተው የለብንም።

ሀገራቸውን በቆራጥነት ያገለገሉ እና የህዝብን አደራ ያልበሉ ንጹሃን መሪዎችን ማከበርና መደገፍ የታማኝነትን ዋጋ የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለሌሎች ባለሥልጣናት ትልቅ አስተምህሮ የሚሰጥ ነው።

እኒህ ክቡር ሰው ያላቸውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና የአመራር ልምድ ተጠቅመው የሚገባቸውን የክብር ቦታ እንዲያገኙ፣ ባሉበት ሀገር የግል ቢዝነሳቸውን ማስጀመር የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ እና ተገቢውን የሞራልና ቁሳዊ ድጋፍ በመስጠት ከጎናቸው እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

10/05/2026
05/05/2026

"የልጄ የሄቨን ጉዳይ ነገ ረቡዕ ፍርድ ቤት ስለሚታይ፣ እንድትገኙልኝ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።" — ወይዘሮ አብቅየለሽ

ሰላም ቤተሰቦች፤ አብቅየለሽ ነኝ የህፃን ሄቨን እናት። ዛሬ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበረን፤ ለረቡዕ ተቀጥረናል።

አዲስ አበባ አካባቢ የምትኖሩ እህት ወንድሞቼ የሴቶች ሞት ጥቃት ይመለከተናል የምትሉ እንድትገኙልን በትህትና እጠይቃለሁ፤ አመሰግናለሁ።"

ነገ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በህፃን ሄቨን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ ተከትሎ የተመሰረተው ክስ በችሎት ይታያል።

በ6 ኪሎ የካቲት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ፍርድ ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የፍርድ ሂደቱ የሚከናወን ይሆናል።

በቪዲዮው ላይ የህፃን ሄቨን እናት አብቅየለሽ፣ የሴቶችና የህፃናት ጥቃት ጉዳይ የሚመለከተን ሁሉ በአካል በመገኘት ድጋፋችንን እንድናሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

22/04/2026

የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ቀኝ እጅ የሆኑት ቁልፍ ግለሰቦች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት እስካሁን አልተገለፀም:: የቴዲ አፍሮ ምክትል ማናጀር፣ ቃል አቀባይ እና የአዲሱ አልበሙ ስራዎች መሪ (ኦስትሪያዊት የዜግነት ያላት)። የረጅም ዘመን የልብ ወዳጁ እና በስቱዲዮ ስራዎቹ የማይለየው ባለሙያ።
እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉበት ይፋዊ ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን፣ ድንገተኛው እስር ከአርቲስቱ ጋር ካላቸው ጥብቅ የስራ እና የጓደኝነት ግንኙነት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል የሚሉ ስጋቶች እየተደመጡ ነው። ጉዳዩ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄንና ውግዘትን እየቀሰቀሰ ይገኛል።
አዳዲስ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናጋራችሁ ይሆናል፤ ገጻችንን ይከታተሉ።

ሲፒጄ ( ) ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገተው የ   ኤዲተር እንዲለቀቅ ጥሪ አቀረበ​አዲስ አበባ — የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋም (CPJ)፤ በዋና ከተማዋ ከአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል...
18/04/2026

ሲፒጄ ( ) ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገተው የ ኤዲተር እንዲለቀቅ ጥሪ አቀረበ

​አዲስ አበባ — የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋም (CPJ)፤ በዋና ከተማዋ ከአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተወስዶ የተሰወረው ሚሊዮን በየነ በአስቸኳይ ያለበት ተለይቶ እንዲለቀቅ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ጠየቀ።
​ሲፒጄ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ ሚሊዮን ረቡዕ ዕለት ረፋዱ ላይ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የመገናኛ ብዙኃኑ የዜና ክፍል በሲቪል ልብስ በለበሱ ሰዎች ተይዞ ወደማይታወቅ ቦታ መወሰዱን ገልጿል።

​የአዲስ ስታንዳርድ አሳታሚ የሆነው ጃኬን ፐብሊሺንግ (JAKENN Publishing PLC)፤ ማኔጂንግ ኤዲተሩ ሚሊዮን በየነ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ከተወሰደ 48 ሰዓታት ያለፉ ቢሆንም እስካሁን ያለበት ቦታ እንዳልታወቀ አስታውቋል። አሳታሚው ዛሬ ጠዋት ባወጣው መረጃ፤ በሚሊዮን ደኅንነት ላይ ያለው ስጋት እየጨመረ መሆኑንና ቤተሰቦቹም “በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ” እንደሚገኙ ገልጿል።

ጊዜ ቆጣቢው የመረጃ ምንጭ ይፋ ሆነ! www.tiktok.com/
14/04/2026

ጊዜ ቆጣቢው የመረጃ ምንጭ ይፋ ሆነ!
www.tiktok.com/

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ትገኛለች!ከሦስት ዓመታት በፊት፡ በሚያዝያ 9 ቀን፣ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በመዘገቧ ምክንያት በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ መስከረም አበራ...
10/04/2026

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ትገኛለች!
ከሦስት ዓመታት በፊት፡ በሚያዝያ 9 ቀን፣ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በመዘገቧ ምክንያት በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ዛሬም በአሳሳቢ ሁኔታ ትገኛለች።በሽብርተኝነት የተከሰሰችው መስከረም፣ የሞት ቅጣትን ሊያስከትል የሚችል የክስ ሂደት ይጠብቃታል ሲል CPJ ብልፅግናን አስጠንቅቋል::የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) መስከረም በአስቸኳይ እንድትፈታና መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገውን ማዋከብ እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል።
#ኢትዮጵያ

Address

Sheger
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Voice Of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share