መንግሥተ ሰማያት-Kingdom of heaven

መንግሥተ ሰማያት-Kingdom of heaven #ክርስትና በኢየሱስ ከኢየሱስ ስለኢየሱስ ነው !!! #

  ይጨነቃልና ለነገ  #አትጨነቁ፤  #ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”    (ማቴ 6:34)
08/06/2026

ይጨነቃልና ለነገ #አትጨነቁ፤
#ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”
(ማቴ 6:34)

የዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) እናት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ  | በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በበጀትና ሂሳብ ባለሙያነት ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘ...
25/05/2026

የዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) እናት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

| በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በበጀትና ሂሳብ ባለሙያነት ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ተድላ በ74 ዓመታቸው አርፈዋል።

የሽኝት እና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ እንደሚፈጸም ታውቋል።

ባለፈው ወር በዩናይትድ ስቴትስ 74ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት ወይዘሮ ቅድስት አምስት ልጆቻቸውን በጥሩ ሥነ ምግባርና በትጋት ያሳደጉ ጠንካራ እናት ነበሩ።

የታዋቂዋ ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) እንዲሁም የዶክተር ለዓለም ጥላሁን፣ የጂጂ ጥላሁን፣ የኪኪ ጥላሁን እና የዳግማዊ ጥላሁን እናት የሆኑት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ላለፉት 13 ዓመታት መኖሪያቸውን በአሜሪካ አድርገው ቆይተዋል።

ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሙሉ በውጭ ሀገር የሚኖሩ በመሆኑ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እሮብ ዕለት በሜሪላንድ እንደሚፈጸም ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሟች ሙሉ የሕይወት ታሪክ በቅርቡ በተወዳጅ ሚዲያ ዲጂታል አማራጮች የሚቀርብ ሲሆን ለተባረከው ቤተሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

#ሀዘን #ጌጡ #ጌጡተመስገን

22/05/2026
21/05/2026

#በልጁ በኩል የእግዚአብሔር ልጅነትን ያግኙ ..

09/05/2026

በኢትዮጵያ በግንቦት ወር የሚሰራ ኪዳኑን የሚያድስ የትኛውም የአጋንንት ፣ የጥንቆላ ፣ የሟርተኛ ፣ የደጋሚ አሰራር በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የፈረሰ ይሁን !

ቅዳሜ ግንቦት 1 ከጠዋቱ 12 ሰአት በአዲስ አበባ ስታዲየም አብራችሁን እንድታሳልፉ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።
08/05/2026

ቅዳሜ ግንቦት 1 ከጠዋቱ 12 ሰአት በአዲስ አበባ ስታዲየም አብራችሁን እንድታሳልፉ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

ፖስተር ደረጄ "የቴዲ ዘፈን ወንጌል ነው" ማለቱን ተከትሎ አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል ....."ለፓስተር ደረጄ ከበደ በቅርቡ በዚህ መሰል ማህበራዊ አውታር ላይ የሰነዘ...
01/05/2026

ፖስተር ደረጄ "የቴዲ ዘፈን ወንጌል ነው" ማለቱን ተከትሎ አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል .....

"ለፓስተር ደረጄ ከበደ

በቅርቡ በዚህ መሰል ማህበራዊ አውታር ላይ የሰነዘሩትን ሀሳብ ተመልክቼ ነበር። ከዚህ በመነሳት ቀጥሎ ያለውን ለማለት ወደድኩ።

ሲጀመር እርሾው ዘፈን ከሆነ እግሌ ዘፈነው እግሌ…..
ግጥሙ ምንም ይሁን ምን ጥጉ ዘፈን ዘፈን ነው ወደሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሰናል፡፡
እኔ እንደ ወንጌል አማኝ እገሌ የዘፈነው ዘፈን ሀ-ጢአት እገሌ ደግሞ የዘፈነው ዘፈን ጽድቅ ነው፣ ወንጌል ነው የሚል አቋም የለኝም።

ስለ ፍቅር ተዘፈነ፤ስለ በጎነት ተዘፈነ፤ስለ ችሮታ ተዘፈነ፤ስለ በጎ አድራጎት ተዘፈነ ዘፈን ያው ዘፈን ነው፡፡ፓስተር ደረጄ የዘፈን ግጥም አጥንተው አድምጠው ለመተንተን በምን መንፈሳዊ አቋም የትኛውም የወንጌል ክፍል እንደፈቀደሎት አላውቅም፡፡ የቀደሙ አባቶች፣ አሁን ያሉ ትውልዶች፣ በጌታ ቤት ፀንተው ያሉ፣ ቤቱን ጥለው የሄዱ ወይም ስተዋል የሚባሉት እንኳን ሳይቀር የትኛውም ዘፈን ወንጌል ነው ብለው አያምኑም።

መጽሃፍ ቅዱስም እንዲህ ዓይነት ወንጌል የሆነ ምርጥ ዘፈን አለ ብሎ አላስተማረኝም፣ ደግሞም አልነገረኝም፡፡ ታድያ በእግዚአብሔር ቤት በርካታ አስርት ዓመታትን በአገልግሎት ያሳለፉ፣ በዝማሬዎ ለብዙዎች ወደ ጌታ መንግስት መምጣት ምክንያት የሆኑ፣ ለወንጌል ብዙ ዋጋ የከፈሉ እርስዎ ዛሬ ምን ነካዎትና ነው ይሄ ዘፈን ሳይሆን ወንጌል ነው ለማለት የተነሱት?

መንግስትን መደገፍም ይሁን መቃወም መብቶ ነው ። ፖለቲካውን መውደድም መጥላትም የግል ፍላጎትዎ ነው፡፡ ይሁንና መንግስትን ወይም ፖለቲካውን ለመቃወም ዘፈንን ከወንጌል ጋር ማገናኘት ግን የዘመሩለት ጌታ ኢየሱስ፤ እጅግ ዋጋ የከፈሉ አባቶች፤ በጌታ ቤት ያሉ ቅዱሳን ሁሉ የሚወዱሎት ይመስሎታል? እኔ ይህንን ሀሳብ አብዝቼ እጠ-የፋለሁ፡፡ ዘፈን መቼም ወንጌል ሆኖ አያውቅምና።
ብንኖረውም ባንኖረውም ወንጌል የማይለዋወጥ የዘለዓለም እውነት የማይሻር ህያው ቃል ነው። "

- ጥላሁን ጉግሳ

27/04/2026

ስለ ኢየሱስ አዳኝነት ማውራት ሱስ ይሁንብን !

26/04/2026

በዝህ የመጨረሻ ዘመን የነፍሳችሁ ቤዛ ለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ራሳችሁን አሳልፋችሁ ስጡ !

26/04/2026

ኢየሱስ ጌታ ነው !

Address

Bole
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንግሥተ ሰማያት-Kingdom of heaven posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share