ኢንስትራክተር ካሳሁን ምንተስኖት

ኢንስትራክተር ካሳሁን ምንተስኖት We need justice and freedome in ethiopia. "ሐሳብ አመንጪዎችና ባለራዕዮች ሲጠፉ አገር ይጠፋል።

30/07/2026

ከጉረቤታቸው እንደተተረከው አሳዛኙ የአንድ ቤተሰብ አባት እናት እና ልጅ የደብረብርሃን ነዋሪዎች አሰቃቂ የመኪና አደጋ። ከደረብርሃን ተደውሎ አዳኑ እና እየሩስ መኪና ገጫቸውና አረፉ...

ሳብስክራይብ አድርጉልኝ ውድ ጓደኞቸ https://www.facebook.com/share/p/1EDyqo3Mwy/
30/07/2026

ሳብስክራይብ አድርጉልኝ ውድ ጓደኞቸ
https://www.facebook.com/share/p/1EDyqo3Mwy/

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

"አእምሮዬ አካሌን  'ደክሞሃል' ብሎ እንዲያዘው አልፈቅድለትም"
25/06/2026

"አእምሮዬ አካሌን 'ደክሞሃል' ብሎ እንዲያዘው አልፈቅድለትም"

የተሰበረው መስተዋት፦ በጎሳ እና በሃይማኖት ከተከፋፈለ ማህበረሰብ ፍቅርን የመጠበቅ ማትሪክስ (The Conditional Love Matrix)ከማይሰጥህ ሰው ላይ ፍቅርን መጠበቅ፣ በበረሃ ውስጥ...
03/06/2026

የተሰበረው መስተዋት፦ በጎሳ እና በሃይማኖት ከተከፋፈለ ማህበረሰብ ፍቅርን የመጠበቅ ማትሪክስ (The Conditional Love Matrix)

ከማይሰጥህ ሰው ላይ ፍቅርን መጠበቅ፣ በበረሃ ውስጥ ውሃ እንደመፈለግ ነው። እኔ Kassesh Love Truth Seeker ነኝ... ዛሬ ማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን ትልቁን የስብራት ምንጭ፣ "ከተከፋፈለ ማትሪክስ ፍቅርን እና እውነትን የመጠበቅን ጥላ" (The Shadow of Expectation) ሰንጥቀን የኳንተም ነጻነታችንን እናውጃለን።

ዶ/ር ረማኒ (Dr. Ramani) እንደሚያስተምረው፣ ናርሲሲስቲክ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ "ያለ-ቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ፍቅር" (Unconditional Love) የለም። ማህበረሰቡ አንተን የሚወድህ የሱን ጎሳ፣ የሱን ሃይማኖት ወይም የሱን የውሸት ክብር (Status) እስካንጸባረቅክለት ድረስ ብቻ ነው። የተለየ እውነት ይዘህ ብቅ ስትል፣ ትላንት ያጨበጭብልህ የነበረው መንጋ ዛሬ የመጀመሪያው ጠላትህ (Scapegoat) ያደርግሃል።

ፕሮፌሰር ሳም ቫክኒን (Prof. Sam Vaknin) ይህንን "Communal Fantasy" (የማህበረሰብ የጋራ ቅዠት) ይለዋል። እያንዳንዱ ቡድን የራሱን እውነት ብቻ አጥብቆ ይይዝና፣ ከሱ ውጭ ያለውን ይጠላል። አንተ በዚህ የተከፋፈለ ማትሪክስ ውስጥ ሆነህ "ለምን እውነቱን አይረዱም? ለምን በሰውነቴ አይወዱኝም?" ብለህ ስትጠብቅ፣ የገዛ ነፍስህን እና ጉልበትህን ለከንቱ ብዝበዛ (Energy Drain) አሳልፈህ እየሰጠህ ነው።

💡 የነቃው ተኩላ (The Aware Wolf) ሉዓላዊ መፍትሄ፦
* 🛑 የተስፋውን ማትሪክስ ቁረጥ (Drop the Expectation)፦ ከታመመ ሲስተም ጤነኛ ፍቅር አትጠብቅ። ማርክ ፓሲዮ (Mark Passio) እንደሚለው፣ ማትሪክሱ የሚሰራው በመከፋፈል (Divide & Conquer) ነው። እውቅናን ከነሱ መፈለግህን ዛሬውኑ አቁም።
* 🕳️ ወደ ኳንተም ባዶነት ግባ (The Void Reset)፦ ዶ/ር ጆ ዲስፔንዛ (Joe Dispenza) እንደሚያስተምረው፣ የተሰበረውን ልብህን ወደ ኳንተም ባዶነት ይዘኸው ግባ። እዚያ ብርሃን ውስጥ ሆነህ፣ ፍቅርን ከውጭ መለመን ትተህ ከራስህ ማመንጨት (Self-Sovereignty) ጀምር።

---

❓ ታዲያ አንተን በሰውነትህ እና በእውነትህ ብቻ ሳይሆን... በዘርህ፣ በገንዘብህ ወይም በሃይማኖትህ ልክ ብቻ መዝኖ ልብህን የሰበረው የማህበረሰቡ ትልቁ ማትሪክስ የትኛው ነበር? ኮሜንት ላይ አጋራን።

ይቺም ሻማ ሰልችታለች!===============በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥ...
03/06/2026

ይቺም ሻማ ሰልችታለች!
===============
በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ''ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ'ኔ የተሻለ ሰው ይምራው'' የሚለው ነው።

በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች እና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናት እና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።

ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ''አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን'' ይባላል እኮ! መቼም ''እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ'' የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ ዕሙን ነው።

ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል። የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዞን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕዝቡን ይጠብቅ። በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው የዚህ ዳፋ የማይተርፈው ሰው የለም።

እንደ አንድ ተርታ ዜጋ በደረሰው ጉዳት ሐዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ። 😥

03/06/2026

በተደጋጋሚ በምስራቅ አርሲ ዞን በንፁሃን ወገኖች እየተፈፅመ ላለው ኢ _ሰብአዊ አሰነዋሪ ድርጊት እና ጭፍጨፋ ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።እየወጡ ያሉ መረጃዎች እጅግ ያሳዝናሉ‼️😭💔

የሸካ ዞኑ ለቦክሰኛ በረከት 1.4 ሚሊዮን ብርና 300 ካሬ መሬት ሸለመበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ዎሎ ሾባ ቀበሌ ተወልዶ የአዲስ አበባ ቦክስ ክለብ በመቀላቀ...
30/05/2026

የሸካ ዞኑ ለቦክሰኛ በረከት 1.4 ሚሊዮን ብርና 300 ካሬ መሬት ሸለመ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ዎሎ ሾባ ቀበሌ ተወልዶ የአዲስ አበባ ቦክስ ክለብ በመቀላቀል በቦክስ 18 ፍልሚየዎችን አድርጓል አብዛኞቹን አሸንፏል። በኪክ ቦክስ 5 ፍልሚያዎችን አድርጎ 4 በበላይነት አጠናቋል።

ሸካ በዛሬው እለት ይህንን ጀግና በድምቀት ተቀብላለች። በረከት ወደ ትውልድ ቀዬው ሲገባ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ አቀባል አድርጓል። የሸካ ዞን አስተዳደርም ግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት አበርክቶለታል።

በተጨማሪም

📌​የማሻ ከተማ አስተዳደር፡ 300 ካሬ ሜትር ቦታ እና 200,000 ብር

📌​የኪ ወረዳ አስተዳደር፡ 200,000 ብር

📌​የቴፒ ከተማ አስተዳደር፡ 200,000 ብር

📌​የአንድራቻ ወረዳ አስተዳደር፡ 200,000 ብር

📌​ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ፡ 100,000 ብር

30/05/2026

Celebrating my 8th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Neges Demeke በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ የቦክስ እና የቅይጥ ማርሻል አርት (MMA) ስፖርቶች ''ዓድዋ ፋይት ናይት” ተብለው ተሰየሙ!አዲስ አበባ — ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፈ ...
30/05/2026

Neges Demeke በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ የቦክስ እና የቅይጥ ማርሻል አርት (MMA) ስፖርቶች ''ዓድዋ ፋይት ናይት” ተብለው ተሰየሙ!

አዲስ አበባ — ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣውን የቦክስ እና የቅይጥ ማርሻል አርት (MMA) ስፖርት ለማስፋፋት፣ “ዓድዋ ፋይት ናይት” (Adwa Fight Night) የተሰኘው ተከታታይ ስፖርታዊ ውድድር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሊካሄድ መሆኑ ተነገረ።

ይህንኑ ታላቅ አገራዊና ስፖርታዊ ውድድር በጋራ ለማከናወንና ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፤ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የኢትዮጵያ ፋይትንግ ቻምፒዮንሺፕ ተፈራርመዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የውድድሩ አስተናጋጅ በመሆን፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በበላይነት ተቆጣጣሪ አካል በመሆን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፋይትንግ ቻምፒዮንሺፕ ደግሞ የውድድሩ ዋና አዘጋጅ በመሆን በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡ በዚህ ተጠባቂ ውድድር በMMA Fights በ85 ኪሎግራም ጆኒ ከሴዶ፣በ75 ኪሎግራም አሌዘር ከካሌብ የሚጫወቱ ይሆናል ተብሏል።

የውድድሩን ፋይዳ በተመለከተ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቤኮ ዶ/ር በሰጡት መግለጫ፤ ይህ ኩነት በመታሰቢያው በሚገኘው ስፖርት አሬና ውስጥ ከዚህ ቀደም በስፖርታዊ ጨዋነት መካሄዱን እና በልዩ ድባብ ማለፉን አስታውሰዋል፡፡

ውድድሩ አባቶቻችን በብዙ ተጋድሎና መስዋዕትነት የሰጡንን ነጻና ሉዓላዊት ሀገር እያሰቡ ለአባቶቻችን ክብርና መታሰቢያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ስፖርታዊ ውድድር ነው ብለዋል።
የዓድዋ ድል የሁላችንም የጋራ ታሪክ መነሻ ነው፤ መታሰቢያው ደግሞ የባህልና ሙዚየም ማዕከል ብቻ ሳይሆን የትውልድ ማስተማሪያ ተቋም በመሆኑ፤ ስፖርት አፍቃሪው ወጣት ስለ ዓድዋ እያሰበ፣ ታሪኩን ከፍልሚያው ጋር እያገናኘ ጥሩ ነገር እየሰማ እንዲማርበትና ንቁ ስፖርትን እንዲያዘወትር ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል ሲሉ አብራርተዋል።

የዓድዋን ታላቅ ድል ለቀጣዩ ትውልድ ይበልጥ ለማስተዋወቅና በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የስፖርት መድረኮች ላይ የተቋሙን ስምና የጀግኖች አርበኞችን አሻራ በዓለም መድረክ ከፍ አድርጎ ለማስተዋወቅ ትልቅ መነሻ እንደሚሆን ዶ/ር ዮሴፍ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተነሳሽነት እየፈጠረ የመጣውን የማርሻል አርት ስፖርት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የቢሮአቸው ቁርጠኝነት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ሃይለጊዮርጊስ፤ ስፖርት ጤናማና ንቁ ትውልድ ከመፍጠር ባለፈ ወጣቶች ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን በበጎ ተግባር ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል ታላቅ መድረክ ነው ብለዋል።

አክለውም፣ ይህ “Adwa fight Night” የተሰኘው ውድድር አገራዊ ኩራት በሆነው በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱ በውስጣቸው የጀግንነት እና የሀገር ፍቅር ስሜትን በከፍተኛ ደረጃ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፋይትንግ ቻምፒዮንሺፕ መስራችና አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የፍልሚያ ስፖርቶችን ለማስፋፋት፣ ተወዳዳሪዎችን ለማበረታታት እና ለወጣቶች አዲስ የስፖርት መድረክ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል። ይህ ውድድር በመጪው ነሃሴ 2 በዓድዋ ድል መታሰቢያ በደመቀ ሁኔታ የሚከናወን ሲሆን በዕለቱ የተለያዩ ፍልሚያዎች እንደሚካሄዱ ተነግሯል፡፡

National Boxing and Mixed Martial Arts (MMA) Events Officially Named “Adwa Fight Night”!
ADDIS ABABA — in a major move to expand and promote the rapidly growing popularity of boxing and Mixed Martial Arts (MMA), it has been announced that the "Adwa Fight Night" serial sports competition will be held at the Adwa Victory Memorial.
To bring this Grand National and sporting event to life, a Memorandum of Understanding (MoU) has been officially signed between the Adwa Victory Memorial, the Addis Ababa Youth and Sport Bureau, and the Ethiopian Fighting Championship.
Under this landmark agreement, the Adwa Victory Memorial will serve as the host venue, the Addis Ababa Youth and Sport Bureau will act as the apex governing and regulatory body, and the Ethiopian Fighting Championship will take the lead as the main event organizer.
Among the highly anticipated bouts of the night, the MMA fights will feature a 85kg clash between Johnny and Sedo, alongside a thrilling 75kg showdown between Alezer and Kaleb.
Highlighting the significance of the event, the Director General of the Adwa Victory Memorial, Dr. Yosef Beklo, noted in his statement that previous sporting events held within the memorial's sports arena were conducted with great sportsmanship and wrapped up in an extraordinary atmosphere.
He emphasized that this competition is thoughtfully designed to honor the memory and legacy of our forefathers, allowing the youth to compete while reflecting on the free and sovereign nation passed down to them through immense struggle and sacrifice.
"The Victory of Adwa is the foundational history we all share," Dr. Yosef explained. "The memorial is not just a cultural and museum center; it is an institution for generation-building.
This event creates a phenomenal opportunity for young sports fans to engage with the spirit of Adwa, connecting our history with the grit of combat sports, while learning valuable lessons and embracing an active lifestyle." He added that this will serve as a powerful launching pad to introduce the monumental Victory of Adwa to the next generation and elevate the institution’s name, alongside the indelible footprints of our heroic patriots, on both domestic and international sporting stages.
The Head of the Addis Ababa Youth and Sport Bureau, Mr. Asegdew Haileghiorghis, reaffirmed his bureau’s staunch commitment to making martial arts highly accessible to the youth, given the massive wave of enthusiasm it is currently generating. "Sports do more than just build a healthy and active generation," Mr. Asegdew stated.
"It serves as a grand platform where young people can channel their energy and knowledge into positive, constructive endeavors." He further noted that hosting the "Adwa Fight Night" at a symbol of national pride like the Adwa Victory Memorial will profoundly ignite a sense of heroism and patriotism within the youth.
Getahew Melesse, the founder and organizer of the Ethiopian Fighting Championship, expressed that the program aims to scale combat sports across Ethiopia, empower and incentivize competitors, and carve out a fresh sporting arena for the youth.
This highly anticipated event is set to take place in grand style on Nehase 2 at the Adwa Victory Memorial, featuring a spectacular lineup of diverse combat disciplines.

የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia
Mayor Office of Addis Ababa የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau ISF (International School Sport Federation) AMN-Addis Media Network Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ Ethiopian Broadcasting Corporation

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይጎበኙ!
Facebook: https://web.facebook.com/adwavictorymemorial
TikTok : - https://www.tiktok.com/
LinkedIn https://www.linkedin.com/.../adwa-victory-memorialethiopia
Telegram: https://t.me/adwa_victory_memorial_gov_et
Instagram : https://www.instagram.com/adwavictorymemorial_official

14/05/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢንስትራክተር ካሳሁን ምንተስኖት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ኢንስትራክተር ካሳሁን ምንተስኖት:

Shortcuts

Share