Ethiopian Human Rights Commission

Ethiopian Human Rights Commission EHRC is an independent NHRI tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ አፈጻጸሙ የተቀዛቀዘው የሽግግር ፍትህ ሂደት ትግበራ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ።ጄኔቫ፣ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች...
16/09/2026

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ አፈጻጸሙ የተቀዛቀዘው የሽግግር ፍትህ ሂደት ትግበራ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ።

ጄኔቫ፣ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በ63ኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ትግበራውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በእውነት፣ ፍትህ፣ ካሳ እና ድጋሚ አለመፈጸምን ማረጋገጫ ጉዳዮች ልዩ ራፖርተር ጋር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ፣ መንግሥት የብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን በሚያዝያ 2016 ዓ.ም. እንዲሁም የትግበራ ፍኖተ ካርታውን በሰኔ 2016 ዓ.ም. ማጽደቁን አስታውሰዋል።

ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የብሔራዊ ምክክር መድረኩ ዋና ጉባኤ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ከተጠናቀቀ በኋላ መንግሥት ሂደቱን ለማስፈጸም የገባውን ቁርጠኝነት አድንቋል።

በተጨማሪም ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ መንግሥት በህገ መንግሥታዊ ስርዓት መናድ ሙከራ እና በሽብርተኝነት ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸውን ወይም በክስ ሂደት ላይ የነበሩ ከ600 በላይ ግለሰቦችን መፍታቱን በአደናቆት ገልጸዋል።

ኮሚሽነር ብርሃኑ መንግሥት ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር፣ ዲሞክራሲያዊ ምህዳርን ለማስፋት እና የሰላም ግንባታ ጥረቶችን ለማስቀጠል የሚያግዙ ተመሳሳይ እርምጃዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

የብሔራዊ ምክክሩ መጠናቀቅን ተከትሎ፣ ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ህጋዊ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አጠቃላይ፣ ሰለባ-ተኮር እና ታማኝነት ያለው የሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲኖር ያለውን ፍላጎት በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ በዚሁ ውይይት ላይ አረጋግጠዋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
📌 ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
****
📌 ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770

📌 ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231

📌 ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

📌 በነጻ የስልክ መስመራችን 👉 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ልዑክ በኒው ደልሂ ለብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት በተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ላይ እየተሳተፈ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 ዓ....
15/09/2026

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ልዑክ በኒው ደልሂ ለብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት በተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 ዓ.ም (ኢሰመኮ)

በምክትል ዋና ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ልዑክ፣ ብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት (NHRIs) ላይ ያተኮረ የህንድ ቴክኒካልና ኢኮኖሚያዊ ትብብር (ITEC) አስፈጻሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም ላይ በኒው ደልሂ፣ ህንድ እየተሳተፈ ይገኛል።

የኢሰመኮ ልዑኩ የአካል ጉዳተኞችና የአረጋውያን መብት ኮሚሽነር አቶ መሐመድ አህመድ እንዲሁም የሴቶችና ህፃናት መብት ኮሚሽነር ወ/ሮ አሸነፈች አበበን ያካተተ ነው።

ፕሮግራሙ ከመስከረም 4 እስከ 9 ቀን 2019 ዓ.ም በህንድ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

ለስድስት ቀናት የሚቆየው ይህ ፕሮግራም ከደቡባዊው ዓለም (Global South) የተውጣጡ ብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎችን በማሰባሰብ፣ ሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋትና ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ተቋማዊ አቅሞችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ፕሮግራሙ በዕውቀትና ተሞክሮ ልውውጥ እንዲሁም በአዳዲስ የሰብአዊ መብት ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ በተሳታፊ ተቋማት መካከል ትብብርንና ትስስርን ለማጎልበትም ያግዛል።

የኢሰመኮ በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ፣ ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን ለማጠናከር፣ ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ለመማር እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋትና ለመጠበቅ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ይበልጥ ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

The Government must continue Strengthening Lawful Measures that Promote National Consensus, Expand Democratic Space, and...
11/09/2026

The Government must continue Strengthening Lawful Measures that Promote National Consensus, Expand Democratic Space, and Consolidate Peace-building ..
Press Release - September 10, 2026

Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established as per the Federal Constitution and reporting to the House of People’s Representatives as a national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.

EHRC has consistently issued timely reports and recommendations advocating for sustainable peace in Ethiopia, while persistently urging and actively working to ensure that disputes and differences are resolved through legal, peaceful, and negotiated means. Guided by the conviction that promoting and protecting human rights requires constructive engagement with the government and key stakeholders—while firmly maintaining the Commission’s independence—EHRC continues to execute various initiatives that have delivered tangible outcomes.

Accordingly, acting upon requests submitted to the Commission by citizens convicted of attempts to forcefully subvert the constitutional order, terrorism, and other serious crimes, as well as those currently under prosecution, EHRC submitted the matter to the government, requesting special review of their cases.

Taking these voluntary requests from the prosecuted parties as a starting point, H.E. Prime Minister Dr. Abiy Ahmed favorably received the Commission's submission. The Prime Minister reiterated his administration's steadfast commitment to taking steps that foster peace, national reconciliation, and democratic governance while respecting the rule of law. Expressing full support for EHRC to continue its joint efforts with relevant stakeholders, the Prime Minister issued decisive directives to government structures to execute this national peacebuilding initiative through established legal frameworks. Regional Chief Executives took corresponding decisions and demonstrated equal commitment for regional-level cases.

In accordance with these legal and pardon procedures, individuals convicted of various crimes were granted clemency, while prosecutions against defendants were conditionally terminated, enabling their release. Decisive steps were also taken to restore their legally restricted rights and support their reintegration into society. EHRC commends and believes these outcomes should be sustained.

EHRC looks favorably upon the government's broad initiatives to strengthen peace-building, national consensus, and democracy, including the National Dialogue, Disarmament, Demobilization, and Reintegration (DDR) programs, regional peace calls, and public consultations. While acknowledging all entities that contributed positively to the Commission's last five-month effort, EHRC reaffirms its belief that these legal and pardon-based actions serve as a major catalyst for lasting peace, national consensus, and democracy.

The Commission will closely track these positive government measures and peace-oriented solutions. EHRC will produce monitoring reports to ensure these processes remain inclusive, respect human rights, and establish a firm foundation for enduring peace, justice, and accountability. Reaffirming that lasting peace is fundamental to the universal enjoyment of human rights, the Commission urges the continuation of these endeavors while recognizing all achievements made thus far.

EHRC reaffirms that the government’s decision to accept this request through joint coordination, which resulted in the release of these citizens, holds immense national value and serves as an exemplary model internationally.

Pursuant to this decision, over 600 individuals were released today. The Commission intends to maintain its high level of engagement in similar initiatives as we advance. EHRC extends its gratitude to the government for its firm stance, to the released individuals for their constructive engagement, and to all partners who contributed to this successful outcome.

The Commission urges the released citizens to return home, participate lawfully and peacefully in national peacebuilding and development, and steer clear of destabilizing activities. EHRC also calls on regional administrative bodies, civil society organizations, and non-governmental organizations to assist in rehabilitating these citizens as they reintegrate into daily life.

Additionally, EHRC renews its call for groups seeking to address Ethiopia's challenges through force and armed conflict to choose peace and negotiation instead.
Finally, the Commission cautions all actors against exploiting the outcomes achieved by the government and EHRC for political agendas or to cause public disorder.

🔗 https://ehrc.org/?p=39066
..
https://ehrc.org/



📌 አማርኛ/English - https://web.facebook.com/EthioHRC
📌 Afaan Oromo- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
📌 Af-Soomaali- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
📌 ትግርኛ- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

You can file a human rights violation complaint by calling our toll-free line at 7307.

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.

መንግሥት ለሀገራዊ መግባባት፤ ለዴሞክራሲ ምኅዳር መስፋት እና ለሰላም ግንባታ የሚረዱ ሕጋዊ እርምጃዎችን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል..ጋዜጣዊ መግለጫ - ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ...
10/09/2026

መንግሥት ለሀገራዊ መግባባት፤ ለዴሞክራሲ ምኅዳር መስፋት እና ለሰላም ግንባታ የሚረዱ ሕጋዊ እርምጃዎችን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል..
ጋዜጣዊ መግለጫ - ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሕገ መንግሥቱ እና በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሕጋዊ ሥልጣን መሠረት፣ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን የመከታተል፣ የመመርመር፣ ምክረ ሃሳብ የማቅረብ እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ የማስገንዘብ ጥረት የማድረግ ተልዕኮ ያለው ነጻና ገለልተኛ ብሔራዊ ተቋም ነው።

ኢሰመኮ በሚያወጣቸው ወቅታዊ ሪፖርቶች እና ምክረ ሃሳቦች በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ አለመግባባቶችና ልዩነቶች በሕጋዊ፣ በሰላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ምክረ ሃሳቦችን ሲያቀርብ፣ በተግባርም እንዲፈፅም ያልተቋረጠ ጥረት ሲያደርግ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሰብአዊ መብቶችን ማስከበር እና ማስፋፋት የሚቻለው የኮሚሽኑን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከመንግስት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀራረብ በመስራት (constructive engagement) መሆኑን በማመን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፤ በርካታ ውጤቶችም ተገኝተዋል፡፡

በዚህም መሠረት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እና በሽብርና ሌሎች ከባባድ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠባቸው፣ እንዲሁም በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ ዜጎች፣ ጉዳያቸው በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው በኮሚሽኑ በኩል ለመንግሥት እንዲቀርብላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ፤ እንዲሁም በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሲደረጉ የነበሩ ጥረቶችን በማቀናጀት ኮሚሽኑ ጉዳዩን ለመንግሥት አቅርቧል።

ይህንኑ በክስ ሂደት ላይ የሚገኙ ወገኖች በራሳቸው ፍላጎት ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ ያቀረበውን ጉዳይ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ምንጊዜም የሕግ የበላይነትን ባከበረ መልኩ ለሰላም፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚረዱ እርምጃዎችን ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆኑን በመግለፅ የቀረበውን ጉዳይ በአዎንታ በመቀበልና ኢሰመኮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል በመደገፍ፣ መንግሥት ይህንን ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሂደት በሕግ አግባብ በተግባር እንዲያስፈጽም ለሚመለከታቸው የመንግሥት መዋቅሮች ቁርጠኛ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በተመሳሳይ መልኩ በክልል ደረጃ በሚታዩ ጉዳዮች ላይ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ተመሳሳይ ውሳኔ እና ቁርጠኝነት ወስደዋል።

በዚሁ መሠረት የተቀመጠው የሕግና የይቅርታ አሰራር ሂደትን ተከትሎ በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው በይቅርታ፤ በክስ ሂደት ላይ ያሉ ተከሳሾች በቅድመ ሁኔታ ክሳቸዉ ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ፤ ከክስ ሂደቱ ጋር በተያያዘ የተገደቡ መብቶቻቸው በሕግ መሠረት እንዲከብሩላቸው እና ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ የተወሰነውን ወሳኔ ኢሰመኮ አድናቆት የሚሰጠው እና ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ነው፡፡

ኢሰመኮ መንግሥት ሀገራዊ ሰላምን፣ ሀገራዊ መግባባትን እና የዲሞክራሲ ስርዓትን ለማጠናከር ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት፦ ማለትም የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን፣ የትጥቅ ማስፈታትና መልሶ ማቋቋም (DDR) ፕሮግራሞችን፣ በክልሎች የተደረጉ የሰላም ጥሪዎችን እንዲሁም ሕዝባዊ የሰላም ውይይቶችን በበጎነት ይመለከታል። በተጨማሪም ባለፉት 5 ወራት በኮሚሽኑ በኩል ለተደረገው ጥረት በሂደቱ ላይ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ እውቅና እየሰጠ፣ መንግሥት ይቅርታንና የሕግ አሰራርን መሠረት በማድረግ የወሰደው ይህ እርምጃ ለዘላቂ ሰላም፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለዲሞክራሲ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው እንደሆነ ያለውን እምነትም ያረጋግጣል።

ኮሚሽኑ በቀጣይም እነዚህን መንግሥት በተለይም ለሰላም ግንባታ የመፍትሔ ሂደቶች የወሰዳቸውን አዎንታዊ እርምጃዎችና ጥረቶች በቅርበት የሚከታተል እና ሂደቶቹ በሙሉ ሰብአዊ መብቶችን ባከበረና አካታች በሆነ መልኩ ተተግብረው ለዘላቂ ሰላም፣ ለፍትሕና ለተጠያቂነት መረጋገጥ ጠንካራ መሠረት እንዲሆኑ የክትትል ሪፖርት የማቅረብ ተግባራትን የሚያከናውን ሲሆን፣ ዘላቂ ሰላም ለሰብአዊ መብቶች በሁለንተናዊነት መከበር መሰረታዊ መሆኑን የሚያምን በመሆኑ ጥረቶቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳስባል፣ ለእስክ አሁኑ ጥረቶቹም እውቅና ይሰጣል፡፡

ኢሰመኮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥረት መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ ዜጎች ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ከመሆኑም በላይ ለሌላው ዓለም ምሳሌ የሚሆን እርምጃ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በድጋሚ ያረጋገጣል።

በመንግስት ውሳኔ መሰረት በዛሬው እለት ከ 600 በላይ ሰዎች ከእስር ተለቀዋል። ኮሚሽኑ በሂደቱ የነበረውን ከፍተኛ ጥረት መሰል ስራዎችም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል።ኮሚሽኑ መንግስት በወሰደው ቁርጠኛ አቋም እንዲሁም እስር ላይ የነበሩ ወገኖቻችን ለሂደቱ ስኬት ላሳዩት ዝግጁነት እና ለሂደቱ ውጤታማነት ለተረባረቡ ወገኖች በሙሉ ምስጋና ማቅረብ ይወዳል፡፡

በዛሬው እለት ከእስር የወጡ ዜጎች ወደየአካባቢያቸው በመመለስ በሀገራዊ የሰላም ግንባታ እና ልማት ተግባራት ላይ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲሳተፉ እና ከጸረ ሰላም ተግባራት እራሳቸውን እንዲያርቁ ኮሚሽኑ ያሳስባል። በየአካባቢው በተዋረድ የሚገኙ የመንግስት የአስተዳደር አካላት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከእስር የተለቀቁ ዜጎቻችንን በማቋቋም ወደ መደበኛ ህይወታቸው ለመመለስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንዲያግዙ ኢሰመኮ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ችግሮች በትጥቅ ትግል እና በኃይል ይፈታል ብለው የሚያምኑ ኃይሎች ወደ ሰላምና ድርድር እንዲመጡ ኢሰመኮ አሁንም በድጋሚ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።

በመጨረሻም በእስር ላይ የነበሩ ወገኖቻችን እንዲለቀቁ በመንግሥት እና በኮሚሽኑ የተደረገውን ጥረትና ውጤት ላልተገባ የፖለቲካ አጀንዳ፤ ለሰላምና ፀጥታ መደፍረስ ለማዋል የሚፈልጉ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ ያሳስባል።

🔗 https://ehrc.org/?p=39056
..

https://ehrc.org/



📌 አማርኛ/English - https://web.facebook.com/EthioHRC
📌 Afaan Oromo- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
📌 Af-Soomaali- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
📌 ትግርኛ- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከኒው ዚላንድ አምባሳደር ጋር በሰብአዊ መብቶች ትብብር ላይ ውይይት አካሄዱ።አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)የኢትዮጵያ ሰብአዊ መ...
10/09/2026

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከኒው ዚላንድ አምባሳደር ጋር በሰብአዊ መብቶች ትብብር ላይ ውይይት አካሄዱ።

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ኅብረት የኒው ዚላንድ አምባሳደር ከሆኑት ኦሊቪያ ኦወን ጋር ገንቢ እና ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች ቁልፍ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ሐሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፣ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃና ውትወታን ለማጎልበት የሚያስችሉ ተጨባጭ የትብብር መስመሮችን አንስተዋል።

ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ኮሚሽኑ ዘላቂ የሰብአዊ መብቶች መሻሻል ለማምጣት ጠንካራ ዓለም አቀፍ አጋርነት ያለውን ጠቀሜታ በማጉላት፣ ወደፊት ከአምባሳደር ኦወን እና ከኒው ዚላንድ ኤምባሲ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

ኢሰመኮ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሾች ሰብአዊ መብትን መሰረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ..የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲትዩት (DIHR) በተ...
08/09/2026

ኢሰመኮ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሾች ሰብአዊ መብትን መሰረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ..

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲትዩት (DIHR) በተገኘ ድጋፍ፣ ከነሐሴ 25 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እና ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ እና የምክክር አውደ ጥናት አካሂዷል። በአውደ ጥናቱ የመንግሥት ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የትምህርትና ምርምር ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ታድመዋል።

አውደ ጥናቱ ባለድርሻ አካላት ስለ አየር ንብረት ለውጥ የሰብአዊ መብት ገፅታዎች ያላቸውን ግንዛቤ ለማጠናከር፣ የኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች ከሰብአዊ መብቶች መርሆዎች አንጻር የሚገመግመውን የኢሰመኮ ጥናት ግኝቶች ለማረጋገጥ ያለም መድረክ ሲሆን፣ የአየር ንብረት ለውጥ በሰብአዊ መብቶች ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽዕኖ ለመወያየት እና በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ላይ የተመሰረቱ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሾችን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶችን ለመቃኘት ያለመ ነበር።

በአውደ ጥናቱ ወቅት ከኢሰመኮ፣ ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲትዩት ፣ ከኢትዮጵያ ሚትዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከኢኮ-ጀስቲስ ኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ ብሔራዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት ጥምረት (NANHRI) እና ከቁም ለአካባቢ የተውጣጡ ባለሙያዎች ገለጻዎችን አቅርበዋል፤ መድረኩ ተሳታፊዎቹ ሰብአዊ መብትን መሰረት ያደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለማጎልበት ልምድና ተሞክሮ እንዲለዋወጡ አስችሏል። አውደ ጥናቱ የአየር ንብረት አስተዳደርና የመንግሥት ግዴታዎችን፣ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን፣ በአየር ንብረት ለውጥና ሰብአዊ መብቶች መካከል ያለውን ግንኙነት፣ ሰብአዊ መብትን መሰረት ያደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን ፣ ተጠያቂነትና ከአየር ንብረት ጋር ለተያያዙ ጉዳቶች መፍትሄዎችን፣ የአካባቢ ጥበቃ የህዝብ ጥቅም ክርክሮችን፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሁነቶች አማካኝነት ሰብአዊ መብትንና የአየር ንብረት ፍትህን ለማራመድ ያሉ እድሎችን ጨምሮ ቁልፍ ጉዳዮችን ዳስሷል።

ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ያልተስተካከለ የዝናብ ሁኔታ፣ የመሬት ናዳ እና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ በሽታዎች ኑሮን በቀጥታ አደጋ ላይ እየጣሉ ናቸው። እየተባባሱ ያሉት እነዚህ የአካባቢ ቀውሶች ለህይወት፣ ለምግብ፣ ለውሃ፣ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለዘላቂ ኑሮ እና እንደ በቂ መጠለያ ካሉ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች አጠቃቀም ጋር የተያያዙ መብቶችን እያዳከሙ ሲሆን፣ በአየር ንብረት ምክንያት የሚደርስ የመፈናቀል አደጋንም እያባባሱ ነው።

የአውደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ ስለ አየር ንብረት ለውጥና ሰብአዊ መብቶች የተዘጋጀውን የኢሰመኮ ግምገማ ማቅረብና ማረጋገጥ ነበር። ተሳታፊዎች በግምገማው ግኝቶችና ምክረ ሃሳቦች ላይ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ሰብአዊ መብትን መሰረት ያደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን ለማጠናከር ስለሚወሰዱ እርምጃዎችም ተወያይተዋል። እንዲሁም ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብት ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን አካታችነት ለማረጋገጥ በመንግሥት ተቋማት፣ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ በትምህርት ተቋማት፣ በልማት አጋሮች እና በተጎዱ ማህበረሰቦች መካከል ቀጣይነት ያለው ትብብር የሚኖረው ጠቀሜታ ላይ አጽንኦት ተሰጥቶበታል። የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን በአየር ንብረት ህጎች፣ ፖሊሲዎች፣ የማላመድ እርምጃዎች እና በአየር ንብረት ፋይናንስ ውስጥ በተሻለ መልኩ ማካተት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ፣ የአየር ንብረት ለውጥ በሰዎች ህይወት፣ ኑሮ እና መሰረታዊ መብቶች ላይ በሚያደርሰው ቀጥተኛ ተጽዕኖ የተነሳ የሰብአዊ መብት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። የፖሊሲ አውጪዎችና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሁሉንም ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሾች በሰብዊ መብት መርሆች ላይ መመስረት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ወደፊት፣ ኢሰመኮ ግምገማውን አጠናቅቆ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ መብትን ማዕከል ያደረገ የአየር ንብረት አስተዳደርን ለማስፋፋት ባለድርሻ አካላትን ማሳተፉን ይቀጥላል። ኢሰመኮ የህዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብት ተጽዕኖዎችን ለመከታተል እና በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ጥበቃ ለመሟገት የሚያደርገውን ጥረት የበለጠ ያጠናክራል፣ ይህም በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ እንዲሻሻል አስተዋፅኦ ያደርጋል።

https://ehrc.org/?p=39047

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937
በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

በኢሰመኮ አዲሱን ስትራቴጂካዊ እቅድ በውጤታማነት ለማስፈጸም የሚያስችለው የመዋቅር ማሻሻያ ትግበራ ላይ ውይይት ተካሄደ።..አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)በኢትዮጵያ ሰ...
07/09/2026

በኢሰመኮ አዲሱን ስትራቴጂካዊ እቅድ በውጤታማነት ለማስፈጸም የሚያስችለው የመዋቅር ማሻሻያ ትግበራ ላይ ውይይት ተካሄደ።..
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዲሱን ስትራቴጂካዊ እቅድ በውጤታማነት ለመተግበር የሚያስችለው የመዋቅር ማሻሻያ ላይ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱን በዋናነት የመሩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ የየዘርፍ ኮሚሽነሮች እና የየሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የቀረበው የመዋቅር ማሻሻያ የኮሚሽኑን ተቋማዊ ነጻነት፣ ገለልተኝነት እና የሥራ ውጤታማነት በተሻለ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለመ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነቶች በሚገባ ለመወጣትና ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት እና መጠበቅ በሚሠራቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ ስልታዊው የመዋቅር ማሻሻያ አስፈላጊነቱ ግልፅ መሆኑን አስረድተዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር) ማሻሻያው ለምን እንዳስፈለገ ያብራሩ ሲሆን፣ ከ2019- 2023 የሚተገበረው አዲሱ ስታራቴጅክ እቅድ በቀደመው መዋቅር ቢተገበር ውጤታማነቱ ላይ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ መሻሻሉን አብራርተዋል።

በተጨማሪም የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት የመከላከልና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅምን በማሳደግ ተቋማዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር፣ እንዲሁም ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ለማስፈን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነውም ብለዋል።

በውይይቱ ወቅት የሥራ ክፍል ኃላፊዎቹ በመዋቅር ማሻሻያው ላይ ያላቸውን አስተያየትና ግብአት ያቀረቡ ሲሆን፣ አዲሱ ስትራቴጂካዊ እቅድ ስኬታማ እንዲሆን የተዘጋጀው መዋቅር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።

በማጠቃለያው ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ መላው የኮሚሽኑ አመራር እና ሰራተኞች ለስትራቴጅክ እቅዱ ውጤታማ ትግበራ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ....
04/09/2026

በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራው ልዑክ በዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት ፖሊሲ ምክትል ሚኒስትር ኦሌ ቶንኬ ጋር
በሰብአዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት ዋና ኮሚሽነሩ የዴንማርክ መንግስት በዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ኢንስቲትዩት (DIHR) በኩል በባስኬት ፈንድ (Basket Fund) አስተዳዳሪነትና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ለኢሰመኮ ተቋማዊ እድገትና ስኬቶች ለሚያደርገው ዘላቂ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የዴንማርክ መንግሥት ለአፍሪካ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ምህዳር ያለውን ጥልቅ ግንዛቤ ያደነቁት ዋና ኮሚሽነሩ፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር፣ ዲሞክራሲያዊ ምህዳርን ለማጎልበት እና ነጻና ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት የተጀመረውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት አጠናክሮ ለመቀጠል ኮሚሽኑ ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር የሚመሩት የከፍተኛ አመራር የልዑካን ቡድን ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም (DIHR) ጋር በሚያደርገው የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዴንማርክ ኮፐንሃገን ማቅናቱ የሚታወስ ነው።

#ኢሰመኮ #ዴንማርክ #ዲሞክራሲ

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
📌 ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
****
📌 ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770

📌 ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231

📌 ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

📌 በነጻ የስልክ መስመራችን 👉 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

የኢመደበኛ ፍልሰት ተጠቂ የሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞችን ለመጠበቅ ያለመ ምክክር እየተካሄደ ነው..አርባ ምንጭ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ...
03/09/2026

የኢመደበኛ ፍልሰት ተጠቂ የሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞችን ለመጠበቅ ያለመ ምክክር እየተካሄደ ነው..
አርባ ምንጭ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ በኩል ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሶስተኛ ሀገራት የሚያደርጉትን መደበኛ ያልሆነ እንቅስቃሴን በተመለከተ በአርባ ምንጭ ከተማ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ማካሄድ ጀምሯል።

ይህ የምክክር መድረክ ኢሰመኮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን አድርገው ወደ ሦስተኛ ሃገራት በሚደረግ ኢመደበኛ እንቅስቃሴ ወቅት የሚያዙ ስደተኛችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በተመለከተ ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዞኑ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ያደረገውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል መሰረት ያደረገ ነው።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ የምክክር መድረኩ በኢሰመኮ የሚነሱት ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ላይ መሰረት በማድረግ በችግሮቹ ይዘት ላይ መግባባት በመድረስ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እንደሚለይ ይጠበቃል ብለዋል።

ነሓሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው ይህ የውይይት መድረክ በሁለተኛው ቀንም የሚቀጥል ሲሆን፣ የወረዳ፣ ዞን እና የክልል የሕግ አስፈጻሚ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ላይ ይመክራሉ።

🔗 https://ehrc.org/



📌 አማርኛ/English - https://web.facebook.com/EthioHRC
📌 Afaan Oromo- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770
📌 Af-Soomaali- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231
📌 ትግርኛ- https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

በዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኢሰመኮ ልዑክ በኮፐንሃገን ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ጋር ምክክር ማካሄድ ጀመረ።አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)የኢትዮ...
01/09/2026

በዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኢሰመኮ ልዑክ በኮፐንሃገን ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ጋር ምክክር ማካሄድ ጀመረ።

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢሰመኮ)

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር የሚመሩት የከፍተኛ አመራር የልዑካን ቡድን ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም (DIHR) ጋር በሚያደርገው የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዴንማርክ ኮፐንሃገን ገብቷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነሩ፤ የሁለቱ ተቋማት አጋርነት ከመደበኛ ግንኙነት የተሻገረ ኢሰመኮን ራሱን የቻለ፣ ጠንካራ እና ስትራቴጂካዊ ብሔራዊ ተቋም አድርጎ ለመገንባት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም እውነተኛና ዘላቂ አጋርነት የሚገነባው ግልጽና ታማኝ ግምገማ በማድረግ በመሆኑ እዚህ መገኘታችን በለውጥ ሂደታችን ውስጥ ትልቅ ትርጉም የምንሰጠው ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የሁለቱ ተቋማት ውይይት አዲሱን የኢሰመኮ የ2018–2022 (2026–2030) የ5 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወደ ትግበራ ማሸጋገር፣ እስከ 2020 (2028) የሚዘልቀውን የጋራ ፈንድ (Basket Fund) አፈጻጸም ገምግሞ በቀጣይ ስላለው ዘላቂ የፋይናንስ ማዕቀፍ መምከር፣ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ማረጋገጥ፣ አዲስ የሚቋቋመውን የምርምር፣ ሕግ እና ፖሊሲ ክፍል አቅም ማጠናከር እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የሽግግር ፍትህ ፕሮጀክት አፈጻጸምን መገምገም ላይ ያተኩራል።

ዋና ኮሚሽነሩ አበክረው እንደገለጹት፤ የኢሰመኮ ተቋማዊ ነፃነት እና ውሳኔ ሰጪነት መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ፣ ይህ ምክክር የወደፊት የቴክኒክ ድጋፍ እና የሀብት ማሰባሰብ አቅጣጫዎችን በግልጽ በማስቀመጥ በውጤታማነት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

#ኢሰመኮ #ሰብአዊመብቶች

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የትስስር ግጾቻችንን ይወዳጁ
📌 ድረ ግጽ ፦ https://ehrc.org
****
📌 ኢሰመኮ አፋን ኦሮሞ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591797593770

📌 ኢሰመኮ አፍ ሶማሌ ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591810527231

📌 ኢሰመኮ ትግርኛ፦ https://web.facebook.com/profile.php?id=61591382141937

📌 በነጻ የስልክ መስመራችን 👉 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Address

Headquarters: Meskel Square, On Bole Airport Road Next To Hyatt Regency Hotel
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Human Rights Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Human Rights Commission:

Shortcuts

Share