Ethiopian Quality Award Organization - EQA

Ethiopian Quality Award Organization - EQA EQA is established to recognize organizations for their achievement in quality & performance, raise awareness about the concept of quality and excellence.

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ።የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ትናንት መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፤ በዋናነት በስትራቴጂ...
18/09/2026

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ።

የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ትናንት መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ፤ በዋናነት በስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም እና ተያያዥ በሆኑ ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ተወያይቷል።

በውይይቱም የድርጅቱን ጠንካራ ጎኖች በማጠናከር እና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በመቅረፍ ተቋማዊ የላቀ ብቃትንና የጥራት ባሕልን ማሳደግ በሚቻልባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!

መልካም አዲስ ዓመት!ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!
11/09/2026

መልካም አዲስ ዓመት!

ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!

02/09/2026

"....የ EQA Excellence Model ግን አንድ Step ወደፊት ሄዶ ይጠይቃል Financially ምን result አገኘህ , Market wise ምን result አገኘህ,, societal wise ምን result አገኘህ ብሎ እያንዳንዱን ነገር ይጠይቃል......"

ግርማ ማሞ
የቴክኒክ ኮሚቴ አባል

የ13ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት የውጤት ማጣጣምና የወጥነት ማረጋገጫ (Harmonization & Calibration) ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ በትናንትናው ዕለት በስኬት ተጠናቋል።የቴክኒ...
30/08/2026

የ13ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት የውጤት ማጣጣምና የወጥነት ማረጋገጫ (Harmonization & Calibration) ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ በትናንትናው ዕለት በስኬት ተጠናቋል።

የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት ትናንት ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጨረሻ የውይይት መድረክ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሥር በሚገኙ አምስት ኩባንያዎች ላይ ያተኮረ የጋራ የውጤት ማጣጣም ሥራን አከናውነዋል።

ይህ የCalibration እና Harmonization ሥራ የተከናወነባቸው ድርጅቶች፦

• የአውሮፕላን ጥገና እና ዕድሳት (Maintenance, Repair and Overhaul - MRO)
• የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት (Ethiopian Cargo & Logistics Services)
• የኢትዮጵያ ኬተሪንግ አገልግሎት (Ethiopian Catering Services)
• የኢትዮጵያ ግሎባል ደንበኞች መስተጋብር ማዕከል (GCIC) እና
• የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል (Ethiopian Skylight Hotel)ናቸው::

ይህ ተከታታይ ሂደት፤ የሽልማት ውድድሩ ፍጹም ወጥ፣ አስተማማኝ እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ግልጽ አሠራር እንዲኖረው ለማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

"ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!" 🇪🇹

የ13ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር ሂደትን ግልጽና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለመምራት የቴክኒክ ኮሚቴው የውጤት ማጣጣምና የወጥነት ማረጋገጫ (Harmonization & Calibra...
26/08/2026

የ13ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር ሂደትን ግልጽና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለመምራት የቴክኒክ ኮሚቴው የውጤት ማጣጣምና የወጥነት ማረጋገጫ (Harmonization & Calibration) ሥራውን በስኬት እያከናወነ ይገኛል።

ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 4ኛው የጋራ መድረክ፤ ኢትዮፖስታን፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS)ን እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ጨምሮ በአገልግሎት ዘርፍ ተወዳዳሪ በሆኑ ተቋማት ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

ይህ ተከታታይ የምዘና ሂደት በቀጣይ ቅዳሜ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኩባንያዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይቀጥላል።

"ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!" 🇪🇹

እንኳን ለመውሊድ በዓል ደረስዎ!
25/08/2026

እንኳን ለመውሊድ በዓል ደረስዎ!

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የ13ኛውን ዙር ተወዳዳሪዎች የመስክ ግምገማ (Site Visit ) ካጠናቀቀ በኋላ፣ የወጥነት ማረጋገጫ የጋራ ግምገማውን በትኩረት ቀጥሏል! ቅዳሜ ነሐሴ 16 ...
23/08/2026

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የ13ኛውን ዙር ተወዳዳሪዎች የመስክ ግምገማ (Site Visit ) ካጠናቀቀ በኋላ፣ የወጥነት ማረጋገጫ የጋራ ግምገማውን በትኩረት ቀጥሏል!

ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ለሦስተኛ ጊዜ ባደረጉት የጋራ የግምገማ መድረክ፣ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥር በሚገኙ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድንን ጨምሮ በሌሎች የማይኒንግ እና አግሮ ፕሮሰሲንግ ክላስተር ድርጅቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ውሏል።

ገምጋሚ ባለሙያዎቹ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ቀኑን ሙሉ ባደረጉት ጥልቅ ውይይት፣ በተናጥል የሰጧቸውን ውጤቶች እርስ በእርስ የማጣጣም (Harmonization) እና ገምጋሚ ባለሙያዎችም እርስበእርስ የሚገነዛዘቡበት (Calibration) ወሳኝ ሥራዎችን በስኬት አከናውነዋል።

ይህ ተከታታይ መድረክ፤ የሽልማት ውድድሩ ፍጹም አስተማማኝ፣ ወጥ እና ግልጽ በሆነ ሥርዓት እንዲመራ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ መሰል ውጤታማ ውይይቶች በቀጣይም በሌሎች ዘርፎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን! 🇪🇹

19/08/2026

“……ለ International እና ለ Local የሚል Quality የለም:: Quality አንድ ነው። International ሆነ Local ሆነ የሚባል ነገር ስለሌለ ወገቧችን ጠበቅ አድርገን ለማይቀረው International Competition መዘጋጀት ነው……."

ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የዳኞች ጉባኤ ሰብሳቢ እና የቦርድ አባል

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የመስክ ግምገማ (Site Visit) ካጠናቀቀ በኋላ፣ ተወዳዳሪ ድርጅቶችን በየዘርፋቸው በጋራ የመገምገም ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል!ቅዳሜ ነሐሴ 09 ቀን 201...
16/08/2026

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የመስክ ግምገማ (Site Visit) ካጠናቀቀ በኋላ፣ ተወዳዳሪ ድርጅቶችን በየዘርፋቸው በጋራ የመገምገም ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል!

ቅዳሜ ነሐሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ም፤ በ13ኛው ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ከተሳተፉ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች መካከል የሃይኒከን ኢትዮጵያ፣ የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ (ኮካ ኮላ)፣ ኮማሪ ቢቬሬጅ፣ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ፣ ቶፕ ውኃ፣ ዲና ምግብ ማቀነባበሪያ፣ ኢትዮ ኤዥያ፣ የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ እና የሌሎችንም ድርጅቶች የመስክ ምልከታ ያደረጉ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋራ ተገኝተዋል።

የኮሚቴው አባላት በተናጥል የገመገሟቸውን ኩባንያዎች ውጤት እርስ በእርስ የማጣጣም (Harmonize የማድረግ) እና የጋራ መለኪያዎችን የማስተካከል (Calibrate የማድረግ) ወሳኝ ሥራዎችን በጋራ አከናውነዋል።

ይህ በየዘርፉ የሚደረግ የጋራ ግምገማ፤ በባለሙያዎቹ መካከል ግልጽ ግንኙነትና መናበብ ለመፍጠር እንዲሁም ወጥነት ያለው እና አስተማማኝ የግምገማና የውጤት አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ታስቦ የሚከናወን ነው::
እንዲህ ያሉ ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ የጋራ ውይይቶች በቀጣይ የእረፍት ቀናትም (Weekends) ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

ጥራት ቀዳሚ አገራዊ አጀንዳ እንዲሆን እንተጋለን!

Address

Meskel Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 08:30 - 11:30

Telephone

+251115541445

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Quality Award Organization - EQA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Quality Award Organization - EQA:

Shortcuts

Share