24/12/2023
የእንቆጳ ጉባዔ ነገ ይጀምራል
ትኩረቱን በሥራ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ ያደረገው የእንቆጳ ጉባዔ ከጥቅምት 1 – 2 /2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ቴክኖሎጂ አልሚዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ጀማሪ የንግድ ሥራ ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮች እንዲሁም የትምህርትና የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡
የጉባኤው ዓላማ ኢትዮጵያ በዲጂታል የሥራ ፈጠራ ያላትን እምቅ አቅም በማስተዋወቅ በዘርፉ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን ማስፋት ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው መርሃ ግብር በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡
ከውይይቶቹ ጎን ለጎንም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ኤግዚቢሽን ይካሄዳል፡፡
መስከረም 30/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃዎች
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- mols_official በመወዳጀት ይከታ