Ethiopian National Assocation of the Deaf የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian National Assocation of the Deaf የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር

Ethiopian National Assocation of the Deaf  የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ENAD is a non profit, non-governmental Association established by the Deaf with the assistance of some of their hearing friends in 1970.

02/08/2026

🌍🇪🇹🤟የዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት ዝግጅት ወቅታዊ ማስታወቂያ

የመጪውን የዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት በተመለከተ ከአባላት የተለያዩ ጥያቄዎች፣ ሀሳቦች እና ጥቆማዎች ደርሰውናል።

👉በዚህ ቪዲዮ የዘንድሮውን መሪ ቃል፣ የዝግጅቱን አስፈላጊ መረጃዎች፣ እንዲሁም ለ"ብርታት" መጽሔት የጽሑፍ ጥሪ በተመለከተ ማብራሪያ እናጋራለን።

👉ENAD የአባላቱን ተሳትፎ እና ሀሳብ ከፍተኛ ዋጋ ይሰጣል። ለቀጣይ ሥራዎቻችን የሚረዱ አስተያየቶች፣ ጥቆማዎች እና ሀሳቦች እንድታካፍሉን እንጋብዛለን።

🎬 ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ መረጃውን ይከታተሉ፣ ለሌሎችም ያጋሩ።

🤝 አብረን በመሳተፍ የመስማት የተሳናቸው ማህበረሰብ ድምፅና መብት እናጠናክር።

31/07/2026

የሳምንቱ የምልክት ቋንቋ 3

🤟 በየሳምንቱ የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ ይማሩ፣ ለሌሎችም ያጋሩ፣ አብረን ተደራሽ ማህበረሰብ እንገንባ!

የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ለመግዛት የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር (ENAD) ቢሮን ይጎብኙ።

💬 አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም ጥቆማ ካለዎት በቴሌግራም ያጋሩን። አስፈላጊ ከሆነ በስራ ሰዓት ውስጥ በቪዲዮ ጥሪ እንዲያነጋግሩን ዝግጁ ነን።

እናመሰግናለን! የምልክት ቋንቋን በመማርና በማስተዋወቅ ተደራሽነትን እና አካታችነትን አብረን እናጠናክራለን።

30/07/2026

📢 የዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት እየተቃረበ ነው!

በየዓመቱ በመስከረም ወር የመጨረሻው ሙሉ ሳምንት የሚከበረው የዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት በዚህ ዓመትም በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል፣ በወላይታ ሶዶ ከተማ ይከበራል።

በዚህ ቪዲዮ፦
✅ የዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት ምን እንደሆነ፣
✅ ለምን እንደሚከበር፣
✅ ለENAD "ብርታት" መጽሔት የጽሑፍ ጥሪን ያገኛሉ።

🎥 ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ ለሌሎችም ያጋሩ፣ ለ"ብርታት" መጽሔት በእርስዎ ጽሑፍ ይሳተፉ!

#የመስማትየተሳናቸው #ብርታት

29/07/2026

በግብር ጉዳይ ላይ የENAD መልዕክት

በአሁኑ ጊዜ ብዙ መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን ከግብር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችና ችግሮች እያጋጠሟቸው እንደሆነ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር (ENAD) ተረድቷል።

ENAD ይህንን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለ ሲሆን፣ ከግብር ጋር የተያያዙ ሕጎችን፣ መመሪያዎችንና አሰራሮችን በጥልቀት እያጠና ይገኛል። የመስማት የተሳናቸው ሰዎችን መብቶች የሚመለከቱ የሕግ ወይም የፖሊሲ ክፍተቶች ካሉ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማትና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ተገቢ የመብት ጥብቅና ሥራ ለማካሄድ ይሰራል።

ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ መልዕክቱን ያስተላልፉ፣ እንዲሁም ከግብር ጉዳይ ጋር የተያያዘ ተሞክሮዎን፣ ጥያቄዎን ወይም አስተያየትዎን በቴሌግራም ቻናላችን ያካፍሉን። የሚያጋጥሟችሁ ችግሮችና ተሞክሮዎች ለምናካሂደው ጥናትና ለወደፊት የመብት ጥብቅና ሥራ ጠቃሚ ይሆናሉ።

🤝 አብረን እንስራ! የመስማት የተሳናቸው ማህበረሰብ ድምጽ በመሆን ፍትሃዊና ተደራሽ መፍትሄዎች እንዲገኙ ይህን ጉዳይ በአንድነት እናሳካ!

#ግብር

28/07/2026

📢 የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

🏫 የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር (School Principal)

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD) በስሩ በሚተዳደረው ኮ-አክሽን መስማት የተሳናቸው መዋለ-ሕፃናት ትምህርት ቤት ብቁ፣ ተነሳሽ እና ቁርጠኛ እጩዎችን ለርዕሰ መምህር (School Principal) የሥራ ቦታ እንዲያመለክቱ ይጋብዛል።

📍 የሥራ ቦታ
ኮ-አክሽን መስማት የተሳናቸው መዋለ-ሕፃናት ትምህርት ቤት (ENAD)

📄 የቅጥር ሁኔታ
• የውል ቅጥር
• ደመወዝ፦ በስምምነት

🎓 የትምህርት መስፈርት
በሚከተሉት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ያላቸው፦

ልዩ ፍላጎት ትምህርት
ኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ (ኢምቋ) እና መስማት የተሳናቸው ባህል
ማኔጅመንት/የቢዝነስ አስተዳደር
ወይም ተዛማጅ የትምህርት መስክ

💼 የሥራ ልምድ

ቢያንስ 2 ዓመት በትምህርት አመራር ወይም ተዛማጅ የሥራ መስክ ልምድ።

✅ ተጨማሪ መስፈርቶች

* የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ (EthSL) እውቀት
* ስለ መስማት የተሳናቸው ባህልና አካታች ትምህርት ግንዛቤ
* ጥሩ የአመራር፣ የግንኙነት፣ የእቅድ፣ የድርጅት እና የችግር አፈታት ክህሎት።

📝 እንዴት ማመልከት ይቻላል?

🔗 የማመልከቻ ሊንክ:
https://forms.gle/4rLqDDue12fUUZVNA

📅 የማመልከቻ መጨረሻ ቀን:ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. (August 7, 2026)

❓ ለተጨማሪ መረጃ፣ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ በቴሌግራም ቻናላችን መልእክት (Message) በመላክ ማግኘት ይችላሉ።

🌟 ሴቶች፣ መስማት የተሳናቸው ሴቶች እና ብቁ መስማት የተሳናቸው አመልካቾች በጽኑ እንዲያመለክቱ እናበረታታለን።

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD)
"ለመስማት የተሳናቸው ዜጎች እኩልነት፣ ተደራሽነት እና አካታችነትን እናበረታታለን።"

27/07/2026

📢 የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የቅበላ እና ምዝገባ ማስታወቂያ

🏫 ኮ-አክሽን መስማት የተሳናቸው መዋለ-ሕፃናት ትምህርት ቤት

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD) በስሩ በሚተዳደረው ኮ-አክሽን መስማት የተሳናቸው መዋለ-ሕፃናት ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ምዝገባ ጀምሯል።

👶 የምዝገባ መስፈርቶች
✅ ዕድሜ፦ 4 ዓመት እና ከዚያ በላይ
✅ መስማት የተሳናቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የሕክምና ማስረጃ
✅ የልደት ካርድ
✅ 1 የተማሪ ጉርድ ፎቶ እና 2 የወላጅ/አሳዳጊ ጉርድ ፎቶዎች
✅ ሌሎች ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

📍 የምዝገባ ቦታ
የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD) ዋና ጽሕፈት ቤት

📌 አድራሻ
6 ኪሎ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ፣ መነን አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 3።

📞 ለተጨማሪ መረጃ
📱 0963 14 39 17
📱 0910 89 96 11
📧 [email protected]

🌟 ለመስማት የተሳናቸው ሕፃናት የትምህርት እድል!

እያንዳንዱ መስማት የተሳነው ሕፃን የመማር፣ የማደግ እና ህልሙን የማሳካት መብት አለው። የተደራሽ፣ አካታች እና ጥራት ያለው የቅድመ ትምህርት እድል ለልጆቻችን እናቀርባለን።

📢 ይህን መረጃ ለሚጠቅማቸው ቤተሰቦች በማጋራት ያድርሱ!

#ኮአክሽን #መስማትየተሳናቸው #የቅድመትምህርት #የሕፃናትትምህርት #አካታችትምህርት

27/07/2026

ከየት ወደ የት?

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD) እንዴት ተመሠረተ? መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከዚህ በፊት ምን ዓይነት ተግዳሮቶችን ያጋጥሟቸው ነበር?

በዚህ አጭር ቪዲዮ የENADን ታሪክ፣ የትግል ጉዞ እና የተሳካውን ለውጥ ይመልከቱ።

📌 ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ENAD) ኦፊሴላዊ ድህረ ገጽ። https://www.enadet.org/history/

Rights Internationalts

24/07/2026

የምልክት ቋንቋን አብረን እንማር፣ እናሻሽል!🤟

🎥 ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ አዲስ ምልክቶችን ይማሩ፣ እና ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!

YouTube - https://www.youtube.com/

Facebook - https://web.facebook.com/ENAD1972

Telegram - https://t.me/+hD972gTcpodlM2Y8

WhatsApp - https://whatsapp.com/channel/0029VbD38FzKgsNzqWv5lw2B

Linkden - https://www.linkedin.com/company/ethiopian-national-association-of-the-deaf-enad/
#የምልክትቋንቋ
#የኢትዮጵያየምልክትቋንቋ



22/07/2026

📢 የሥራ መብትዎን ያውቃሉ?

በ2000 ዓ.ም. በወጣው የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ሥምሪት መብት ስለመጠበቅ አዋጅ ቁጥር 568/2000 አንቀጽ 4 መሠረት፣ አካል ጉዳተኞች በቅጥር፣ በሥልጠና፣ በዕድገት እና በሥራ ዕድሎች ላይ ከአድልዎ የተጠበቁ መብቶች አሏቸው።

🎥 በዚህ አጭር ቪዲዮ አንቀጽ 4 ምን እንደሚል በኢትዩጵያ ምልክት ቋንቋ እናብራራለን።

✅ መብትዎን ይወቁ።
📲 ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ ያጋሩት፣ ለሌሎችም ያድርሱ።

20/07/2026

🎉 ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. 10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

በዚህ ልዩ የክብር በዓላችሁ ላይ በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር (ENAD) ስም ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

ኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ለመስማት የተሳናቸው የኮ-አክሽን መዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎችና ትምህርት ቤቱ ያደረገውን 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።

ይህ ድጋፍ ህፃናቱ የተሻለ የመማር እድል እንዲያገኙ፣ የመማሪያ ሁኔታው እንዲሻሻል እና የኮ-አክሽን መዋዕለ ሕፃናት አገልግሎት እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

ለመስማት የተሳናቸው ህፃናት ትምህርትና ዕድገት በማገዝ ያሳያችሁትን ማህበራዊ ኃላፊነት፣ በጎ ፈቃድ እና አጋርነት በእጅጉ እናደንቃለን።

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር (ENAD) ወደፊትም ከመንግስት ተቋማት፣ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከግሉ ዘርፍ ተቋማት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር የመስማት የተሳናቸው ህፃናትን ትምህርትና ተሳትፎ ለማጠናከር ይቀጥላል።

በድጋሚ ለ10ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችሁ እንኳን አደረሳችሁ!

አንድነት የተሻለ ትምህርትና ተስፋ እንገንባ።🤝

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:30
Tuesday 09:00 - 17:30
Wednesday 09:00 - 17:30
Thursday 09:00 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Telephone

+251111222517

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian National Assocation of the Deaf የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian National Assocation of the Deaf የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር:

Shortcuts

Share