Shanan Jimmaa

Shanan Jimmaa Non profit service

ዛሬ የቆምንበት ከፍታ ነገ ለማሳካት ላቀድነው ትልቅ ተቋማዊ ራእይ ስኬት ማሳያና ማረጋገጫ ነው ፤ ስንተባበር ለአላማችን ስኬት በጋራ ስንቆም ተአምር መስራት እንችላለን፤ ለተቋማችን ዕድገትና ...
05/09/2026

ዛሬ የቆምንበት ከፍታ ነገ ለማሳካት ላቀድነው ትልቅ ተቋማዊ ራእይ ስኬት ማሳያና ማረጋገጫ ነው ፤ ስንተባበር ለአላማችን ስኬት በጋራ ስንቆም ተአምር መስራት እንችላለን፤ ለተቋማችን ዕድገትና ለዘርፉ መሻሻል አሁንም እጅ ለእጅ ተያይዘን መትጋት ይኖርብናል ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ገለፁ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ተቋማዊ ሪፎርም ስኬቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ሰፊ የምክክርና የጋራ ቃል ኪዳን መግባት ስነስርአት መድረክ አካሄደዋል።

በዛሬው እለት የ2018 አ.ም ማጠቃለያ እና የ2019 አ.ም መባቻን አስመልክቶ የባለስልጣኑን ራእይና ተልእኮን በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ የስራ ተነሳሽነትና ዝግጁነት መከወንን አላማ አድርጎ በተዘጋጀው አጠቃላይ የሠራተኛ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የማኔጅመንትና የኤዲቶሪያል አባላት እንዲሁም የባለስልጣኑ የክልል ላይዘን ኦፊሰሮች እና መላው ሠራተኞች ተሳትፈዋል ።

በመድረኩም ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ እንደገለፁት እየተጠናቀቀ ባለው የ2018 አ.ም አጋማሽ ጀምሮ የ100 ቀናት እቅድ ከማቀድ ጀምሮ ሌሎች የተቋማዊ ሪፎርምና ስትራቴጂካዊ እቅዶችን በማቀድና ከመላው ሠራተኞች ጋር በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር ተቋሙ በብቃት ተልእኮውንና ራእዩ እንዲፈፅም ያስቻሉተሻጋሪ ስራዎችን በ2019 አ.ም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም በ2018 አ.ም በመላው አመራርና ባለሙያ ርብርብ ያስመዘገብናቸውን አበረታች ትሩፋቶች በቀጣይ 2019 አዲስ አመት በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ ምእራፍና አዲስ ራእይ ሰንቀን የአገርን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ብዝሃነትን ለማጠናከርና የወል ትርክትን ለማፅናት የሚተጋ የሚዲያ ምህዳር የማጠናከር ጉዳይ በትኩረት እንደሚሰራበት አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የተቀናጀ ዘመናዊ የሚዲያ ሪጎላቶሪ አስተዳደር ስራዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የዘመነና ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ለማድረግ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እየተተገበሩ ያሉ ስራዎችም በ2019 አ.ም የህብረተሰቡን ተሳትፎ ያጎለበተ ዘመናዊ የጥቆማና የክትትል ስርዓት EMA Appን እውን በማድረግ የሚዲያ ፕሮፋይሊንግ ስራዎችን በቴክኖሎጅ የማዘመን ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አንስተዋል ።

አክለውም የክልልና የማህበረሰብ መገናኛ፤ እንዲሁም ለበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በሁሉም የሚዲያ ፕላትፎርም ለሚሰሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በብሔራዊ ጥቅሞቻችን፣እንዲሁም በሐሰተኛ መረጃ፣ በጥላቻ ንግግር፣ በሃቅ ማጣራትና በዲጂታል ፎረንሲክ ዙሪያ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሠጠቱ በዚህ አመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

በ2018 አ.ም ባለስልጣኑ የሚዲያ ክትትል የድጋፍና ቁጥጥር ስራዎች በተሻለ ውጤታማነት መፈፀማቸውን አመልክተው በዚህ ረገድ በዘንድሮው አመት የተጣለው ጠንካራ መሠረትም በአዲሱ አመት ይበልጥ እንደሚጎለብት አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የማይነጣጠል ታሪካዊ ቁርኝት ያላትና የ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የማይነጣጠል ታሪካዊ ቁርኝት ያላትና የባሕር በር ጥያቄዋም የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከጥንት ጀምሮ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ግዛት ወሰን አካል ሆኖ መኖሩን አውስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎችም የራሳቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም በቀይ ባሕር በኩል እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ ይነግዱ እንደነበር አውስተዋል።

ከ1950ዎቹ በኋላም አሰብና ምፅዋ የኢትዮጵያ ዋና የባሕር በር ወደቦች ሆነው ማገልገላቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም የኢህአዴግ መንግሥት ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት በሌለው ሁኔታ፣ ያለምንም የሕዝብ ውይይትና ያለ በቂ ጥናት በድንገተኛ ውሳኔ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ ማድረጉንም አብራርተዋል።

ለሀገርና ለሕዝብ ኃላፊነት በማይሰማው መንግሥት የተፈጸመው ይህ የጥፋት ውሳኔ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በባሕር ንግድ በተሳሰረች ዓለም ውስጥ 130 ሚሊዮን ሕዝብን ይዞ ያለ ምንም የባሕር መውጫ ረጅም ጉዞ ማሰብ አይቻልም ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ።

የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በቁጭት የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁን ያለው መንግሥት ኃላፊነት የሚሰማው በመሆኑ የባሕር በር አጀንዳን ፊት ለፊት ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።

የባሕር በር ለንግድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን ከጥቃት ለመከላከልም ወሳኝ የብሔራዊ ደህንነት ዓምድ ነው ብለዋል።

አክለውም የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ትውልድ የማይተወው የህልውና አጀንዳ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።

በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ ሀገራት የሕዝብ ብዛትና ኢኮኖሚ ተደምሮ የኢትዮጵያን ግማሽ አቅም እንኳ እንደማይደርስ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መምጣት ለእነዚህ ሀገራትም ትሩፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ቀጣናው የኃያላን ሀገራት መራኮቻና የተለዋዋጭ ሁኔታዎች ሰለባ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ አኳያ የቀጣናው ሀገራት በጋራ መልማት የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል ።

የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመቀነስ በኢኮኖሚና በታሪክ የተሳሰረውን ሕዝባቸውን ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ በአካባቢው ግዙፍ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅስ መሆኗ ፋይዳው ድንበር ዘለል ነው ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ፥ ከባሕር በር ተነጥላ ልትኖር ስለማትችል የአካባቢው ሀገራት የመውጫ በር ሊሰጧት ይገባል ነው ያሉት።

ይህ ካልሆነ ግን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር ያላት በመሆኗ በጊዜ ሂደት በተፈጥሯዊ መንገድ የታፈነው ጥያቄ መፈንዳቱ አይቀሬ ነው ብለዋል።

ይህ እንዳይሆን የቀጣናው ሀገራት በሰላማዊ መንገድ የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመከላከልና ሀብትን በጋራ በመጠቀም መርህ ለኢትዮጵያ የባሕር በር በማመቻቸት የጋራ ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

#ኢዜአ

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ...
27/08/2026

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፣ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ዳግም «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ተኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq

FDREGovermentCommunication

ፋኖ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር መስርቶ አማራ ክልልና ህዝብን ሰላም ሲነሳ፣ ብልፅግና በላይ ዘለቀ ኤርፖርትን ገንብቶ አስመርቋልየቀድሞው “ባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት” ተርሚናል በህወሓት ሮኬት...
06/08/2026

ፋኖ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር መስርቶ አማራ ክልልና ህዝብን ሰላም ሲነሳ፣ ብልፅግና በላይ ዘለቀ ኤርፖርትን ገንብቶ አስመርቋል

የቀድሞው “ባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት” ተርሚናል በህወሓት ሮኬት ከተመታ በኌላ በከፊል ነበር አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው። ዛሬ አዲሱ “ባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አለማቀፍ ኤርፖርት” ተርሚናል፣ ደረጃውም ከፍ ያለና አለማቀፍ በረራዎችንም ማስተናድ እንዲችል ተደርጎ ነው የተገነባው።

ፋኖ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር መስርቶ አማራ ክልልና ህዝብን ሰላም ሲነሳ፣ ብልፅግና በላይ ዘለቀ ኤርፖርትን ገንብቶ አስመርቋል። ፋኖ ክልሉንም ኤርፖርቱንም ወደ ግንቦት 20 መመለስ ነው አላማው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ ሰጠ።በኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ከባለስልጣኑ ፈቃድ  ወስደው የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ቁጥር በአሁ...
04/08/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ ሰጠ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ወስደው የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 329 መድረሱ ተገልፀዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ከባለስልጣኑ የማኔጅመንት አባላት ጋር በ2019 በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ባካሄዱት ውይይት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የሚዲያ ዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ሁለንተናዊ የሪፎርም ሥራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

በዚህም ባለስልጣኑ የሃገራችን መገናኛ ብዙኃን በአኸዝ፣ በዓይነትና እንዲሁም በብዝሃ ተደራሽነት የተሻለ ዕድገት እንዲያስመዝግቡ ለዘርፉ የሚያደርገውን ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚፈፅም አፅንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም ባለሥልጣኑ በ2018 በጀት አመት ለ14 የበየነ መረብ ሚዲያዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ ለ5 የማህበረሰብ ብሮድካስት ሚዲያዎች ፈቃድ መስጠቱን ገልፀው እንዲሁም ለ19 የሚዲያ ፕሮግራም አዘጋጆቾና እና ለ9 የማስታወቂያ አዘጋጆች የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱንም አመልክተዋል።

እንደ ዋና ዳይክተሯ ገለፃ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በተያያዘ ለ5 ቋሚ የዜና ወኪሎች ፈቃድ ተሰጥቷል ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በበጀት አመቱ ከተለያዩ የውጭ አገራት ለአጭር ጊዜ የፊልም ቀረፃና ዘገባ ወደ ወደ ኢትዮጵያ ለመጡ 78 የውጭ ጋዜጠኞችና ዘጋቢዎችም ፈቃድ ተሰጥቷል።

በአገራችን ከዴሞክራሲያዊ ስርአት መጠናከር ጋር ተያይዞ የሚዲያ ምህዳሩ ጉልህ መሻሻል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳዬ መጥቷል ሲሉም አመልክተዋል ።

ዋና ዳይሬክተሯ በማጠቃለያቸውም በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ላይ እንደተቀመጠው ሚዲያዎች ለአገር ደህንነት፣ ሰላም መጎልበት እንዲሁም ለህዝብ ጥቅምና ለአገራችን ብሔራዊ ጥቅሞች መረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጉልህ በማሳዬት ረገድድ ያላቸውን ሚና ተገንዝበው ስራቸውን ለማከናወን በሚያደርጉት ጥረት ባለስልጣኑ አስፈላጊውን የአቅም ግንባታና መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

03/08/2026
03/08/2026
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚዲያ ተቋማት ሕግና የሙያ ሥነ ም...
31/07/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚዲያ ተቋማት ሕግና የሙያ ሥነ ምግባርን አክብረው መስራታቸውን እየተከታተለ ድጋፍና እርምት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት፦
• አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና
• አርትስ ቴሌቪዥን
ውል የገቡበትን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር በተስተዋሉ ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች ላይ ውይይቶች ያደረገ ቢሆንም ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታውቃል፡፡

ስለሆነም ጣቢያዎቹ በቀጣይ ሥራቸውን በሕግና በሙያ ሥነ ምግባር መሠረት እንዲያከናውኑ በጥብቅ ለማሳሰብ ይወዳል።

ባለስልጣኑ ማስጠንቀቂያው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 74/ሠ መሠረት የተሰጠ መሆኑን እየገለፀ ሚዲያዎቹ ተመሳሳይ የህግ መተላለፍ እና ጥሰት እየፈፀሙ የሚቀጥሉ ከሆነ በህጉ መሠረት ቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ባለሥልጣኑ ያስታውቃል።

ባለስልጣኑ የሚዲያ ተቋማት በሁሉም የዘገባ ስራዎቻቸው ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና የሀገሪቱን ሕጎች እንዲሁም የዘርፉን የሙያ ሥነ ምግባር አክብሮ መስራት የሁሉም ግዴታ መሆኑን ለአፍታም ሊዘነጉት እንደማይገባ ያሳስባል።


25/07/2026

Ethiopia Built a Dam. Egypt Built a Narrative.

The GERD dispute has moved beyond water becoming a struggle between Ethiopia’s development ambitions and attempts to preserve an outdated regional order

Ethiopia built the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) to generate electricity, transform its economy, and improve the lives of millions of its citizens. Egypt built a narrative around it one that presents Ethiopia’s development project as a threat rather than recognizing it as a legitimate exercise of sovereign development rights.

For Ethiopia, the position has always been clear: the Nile is a shared resource, and every country within the basin has the right to utilize it in an equitable and reasonable manner.
The GERD is not designed to deprive downstream countries of water. It is a hydropower project that stores and regulates the flow of the river while generating electricity before allowing water to continue downstream. Its purpose is development not domination.

Yet Egypt has continued an international campaign portraying the dam as an existential threat. Ethiopia argues that this narrative does not reflect the technical realities of the project but serves a broader political objective: preventing Ethiopia from exercising its legitimate right to develop its own resources.

A Dam That Challenged an Old Political Reality
The controversy surrounding the GERD is not simply about water. It is about the changing balance of power in the Nile Basin.
For decades, Ethiopia argues, the management of the Nile was shaped by arrangements that gave greater weight to downstream interests while limiting the development opportunities of upstream countries.

Despite contributing the largest share of the Nile’s flow, Ethiopia has historically faced severe energy shortages and development challenges. The GERD represents a direct response to that reality a project financed largely through Ethiopian determination and public contribution.
Ethiopia’s position is that no nation should be permanently denied development because of its geographical location.

Equitable use of shared resources does not mean preserving historical advantages. It means recognizing the rights and interests of all countries connected to the river.

From Water Debate to Political Pressure
Ethiopia views Egypt’s approach to the GERD as an attempt to transform a development project into a political weapon.
Instead of focusing on practical cooperation, Ethiopia argues that Egypt has pursued diplomatic pressure by presenting the dam as a danger to regional stability and attempting to gain international support against Addis Ababa.
According to Ethiopia, this approach ignores a fundamental reality: the GERD does not consume Nile water. It does not divert the river away from downstream countries. It produces electricity while maintaining the flow of the river.
The disagreement, therefore, is not only about the operation of a dam. It is about whether one country can continue to influence another country’s development choices.

The GERD Beyond Water: Ethiopia’s Strategic Space
The GERD debate is unfolding alongside Ethiopia’s broader efforts to strengthen its economic and strategic position.
Ethiopia is expanding its energy capacity, pursuing regional connectivity, attracting investment, and seeking sustainable access to international trade routes, including the Red Sea.
From Ethiopia’s perspective, the pressure surrounding the GERD reflects a wider geopolitical contest over its growing role in the Horn of Africa.
The dam has become a symbol of Ethiopia’s determination to pursue development without external restrictions.

The Nile’s Future Cannot Be Built on Old Privileges
Ethiopia has repeatedly stated that it supports dialogue and cooperation. However, cooperation cannot mean accepting permanent inequality or allowing historical arrangements to define the future.
The Nile is not the possession of one country. It is a shared resource whose benefits must extend to all nations connected to it.
The GERD is not a weapon against Egypt.

By: Bethel Sileshi

23/07/2026

OBN Haqabaas
OBN Afaan Oromoo Plus
OBN አማርኛ
OBN English
OBN Afaan Oromoo

Address

Hayile
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shanan Jimmaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share