Buzuayehu Tadele Family Foundation

Buzuayehu Tadele Family Foundation Buzuayehu Tadele Family Foundation is a non-governmental organization (NGO) Buzuayehu Tadele and His Family Foundation (BTFF).

is a non-governmental organization established in 2019, registered with the FDRE Charities and Societies Agency (License No. 4381) as an Ethiopian Residents Charity. The Foundation represents East African Holding's philanthropic effort, intended to fulfill the company's corporate social commitments. BTFF is driven by a mission to assist the underprivileged, In line with its corporate social responsibilities, BTFF has adopted a guiding principle of actively involving with and benefiting the local community through diverse initiatives. Essentially, the Foundation aims to carry out community-based services and environmentally friendly projects, mobilize the local community on a large scale as well as support the society to create strength and sense of ownership for the company's socially benefiting businesses.

የብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን (BTFF) እና የተባበሩት መንግስታት ሥነ-ሕዝብ ፈንድ(UNFPA) የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ​የብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን (BTFF) ከ...
17/06/2026

የብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን (BTFF) እና የተባበሩት መንግስታት ሥነ-ሕዝብ ፈንድ(UNFPA) የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

​የብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን (BTFF) ከተባበሩት መንግስታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ (UNFPA) ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ተፈራርሟል።

​ይህ ስምምነት ፋውንዴሽናችን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ጋር በይፋ በመተባበር በሀገራችን በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፍበት ታሪካዊ ምዕራፍ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከUNFP ጋር አጋርነት የፈጠረ የመጀመሪያው የቤተሰብ ፋውንዴሽን እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተብራርቷል።
​ይህ የአጋርነት ስምምነት የማህበረሰቡን ሕይወት በዘላቂነት በሚያሻሽሉ እና ተጨባጭ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ በሚከተሉት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያተኩራል፦
1. በሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነትን ማስፋፋት።
2. የወጣቶችን ጤና መጠበቅ እና የሕይወት ክህሎት ትምህርቶችን መደገፍ።
3. ​የአዕምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን ማጠናከር።
4. በማህበረሰብ አቀፍ ሥራዎች አማካኝነት በጾታ ላይ ለተመሰረቱ ጥቃቶች የሚሰጡ ምላሾችን ማሻሻል።

የብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ አክሲዮን ማኅበር ማኅበራዊ ኃላፊነትን (CSR) የሚያስፈፅም አካል እንደመሆኑ መጠን ልማት ይበልጥ ትርጉም የሚኖረው ከኢንዱስትሪው አልፎ ለምናገለግላቸው ማህበረሰቦች በተግባር በአጋርነት ሲደርስ ነው ብለን እናምናለን።
ፋውንዴሽናችን ዘላቂና ተሻጋሪ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን የትውልዱን መፃዔ ዕድል የተሻለ ለማድረግ ማህበረሰቡን በቅንነት ለመደገፍ በቁርጠኝነት ይሠራል።
ይህ አጋርነት የተወለደው ፋውንዴሽናችን ባለው ጥልቅ የማኅበረሰብ ውግንና እና ተጨባጭ ውጤት የማስመዝገብ ልምድ ላይ ተመስርቶ ነው። ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመገንባት የምናደርገውን ጥረት የበለጠ አጠናክረን ለመቀጠል ከተባበሩት መንግስታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ድርጅትጋር ተጨባጭ ውጤቶችን እናስመስገናለን።

​ለዘላቂ ለውጥ ዘወትር በትጋት እንሠራለን!

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በልደታ ክፍለ ከተማ 11ኛ ጊዜ እና በቪላ አፍሪካ የምግባ መርሃ- ግብራችን ለታቀፉ ወገኖች ደግሞ ለ5 ተኛ ጊዜ  ማዕድ አጋርተናል።በቪላ አፍሪካ  የማዕድ...
10/04/2026

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በልደታ ክፍለ ከተማ 11ኛ ጊዜ እና በቪላ አፍሪካ የምግባ መርሃ- ግብራችን ለታቀፉ ወገኖች ደግሞ ለ5 ተኛ ጊዜ ማዕድ አጋርተናል።

በቪላ አፍሪካ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አቶ ደረጀ ፈይሳ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ዮሐንስ ሰለሞን ወረዳ 8 ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ሀላፊ በተገኙበት ነው የተካሄደው።

ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በአላትን ምክንያት በማድረግ ከሚያደርገው የማዕድ ማጋራት ባሻገር የእለት ጉርስ የሌሌቸውን ወገኖች በቋሚነት እየመገበና የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ለዚህም ምስጋናቸው የላቀ መሆኑን እና እውቅና እንደሚሰጡ አቶ ደረጀ ባደረጉት ንግግር አሳውቀዋል ።

እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የተድላ እንዲሆንላችሁ ይመኛል ዒድ ሙባረክ!!
19/03/2026

እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የተድላ እንዲሆንላችሁ ይመኛል

ዒድ ሙባረክ!!

እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!
19/01/2026

እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!

መልካም ገና ! ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በዓሉ የደስታና የፍሰሃ እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!
06/01/2026

መልካም ገና !

ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን በዓሉ የደስታና የፍሰሃ እንዲሆንላችሁ ይመኛል!!

የጌታችን የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ገናን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማዕድ አጋርተናል።በተጨማሪም በቪላ አፍሪካ የምገባ መርሃ ግብራ...
05/01/2026

የጌታችን የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ገናን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማዕድ አጋርተናል።

በተጨማሪም በቪላ አፍሪካ የምገባ መርሃ ግብራችን የዕለት ጉርስ ለምናቀብላቸው ወገኖችም እንደዚሁ ማዕድ አጋርተናል።

ፋውንዴሽናችን በዘድሮው የገና በአል በድምሩ ለ1200 ዜጎች ማዕድ አጋርቷል።

ባለፉት ተከታታይ 4 አመታት በበአላት ወቅት ለወገኖቻችን ማዕድ በማጋራት እና ሌሎች ማህበራዊ ድጋፎች በማድረግ ፋውንዴሽናችን አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል ።

ኢኮኖማያዊ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወኖች ድጋፍ ማድረጋችንን በማጠናከር ማህበራዊ ሃላፊነታንን እንወጣለን።

Address

Sarbet
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Buzuayehu Tadele Family Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share