28/11/2023
እሁድ ጥቅምት 25 2016 በጊዮን ሆቴል ያደረግነው አመታዊ የጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና አጠቃላይ ስለ አለምፍሬ ፒንክሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን እየሰራ ስላለው እና ወደ ፊት ምን ለመስራት እንዳቀድን ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች እና የጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ተውያይተናል።
የድርጅታችን መስራች እና ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶር ፍሬሂዎት ደርሶ ስለጡት ካንሰር እና ስለድርጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ንግግር አድርገዋል።
ውድ ጊዜዎን ሰውተው በመካከላችን ለተገኙት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ክብርት ዶር ኤርጎጌ ተስፋዬ አብረውን ስላሳለፉ እና መለዕክት ስላስተላለፉልን ምስጋናችን ከልብ ነው፣ በቀጣይ ልንሰራ ካሰብናቸው እቅዶቻችን አብረውን እንደሚሰሩም ቃል ገብተውልናል።
ዶር ኤዶም ከጥቁር አንበሳ እና ዶር ሙሉጌታ ከጳውሎስ ሆስፒታል ስለጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ መለዕክት አስተላልፈዋል የተለያዩ ጥያቄዎችም ተነስተዋል። መድረኩን በመምራት ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ ላደረግሽው አስተዋፆ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
ሴታሴት _Power ለፒንክሀውስ የተለያዩ አስቤዛዎችን ለማሰባሰብ ባደረጉት የአባሎቻቸው ዝግጅት ላይ ደስ በሚል መንፈስ አስቤዛዎችን አሰባስበውልናል፣ ይህ እንዲሆንም ስላደረጋችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
እንዲሁም Rotract club of Finot አባሎች ላደረጋችሁት አስተዋፆ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
በአጠቃላይ ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ ድርጅቶች ግለሰቦች እና አባሎች ዝግጅቱ እንዲሳካ ከጎናችህን ስለነበራችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
www.abcfonline.org
ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል
Early detection and awareness of cancer saves lives!