08/03/2026
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ወደ ተራራም ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቴንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እከብርማለሁ ይላል እግዚአብሔር።" (ት. ሐጌ 1፡8)
✨ ! ✨
በሰሜን ወሎ ዞን፣ በጋሸና ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 የሚገኘው የእድገት በር ፈለገ ሕይወት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ሕንጻ ግንባታ ከተጀመረ 9ኛ ዓመቱን ይዟል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ለዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር ሲባል ምእመናን ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሌት ተቀን እየተጉ ይገኛሉ።
ሆኖም ግን የሰበካ ጉባኤው አባላት ቁጥር (90 አባወራዎች) ብቻ በመሆኑና የግንባታ ቁሳቁስ ዋጋ መናር፣ ይህንን ታላቅ የጌታ ቤት ብቻችንን ሠርተን ለአገልግሎት ለማብቃት ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል።
"ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው!" እንደሚባለው ሁሉ፣ የእናንተ ጥቂት ድጋፍ ተደምሮ ለዚህ ቅዱስ መቅደስ መታነጽ ትልቅ አቅም ይሆናል። ዛሬ ለቤተክርስቲያን የምንዘራው ዘር ለትውልድ የሚተርፍ የነፍስ ስንቅና በረከት ነው።
🙏 በምን መርዳት ይችላሉ?
በገንዘብዎ፦ አቅም የፈቀደውን ያህል ወደ ባንክ አካውንታችን ገቢ በማድረግ።
በቁሳቁስ፦ ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ብረት እና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን በመለገስ።
በጸሎትና በሃሳብ፦ በሥራው ላይ አምላከ መድኃኒዓለም እንዲረዳን በመለመን።
📍 የባንክ አካውንት መረጃ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000724372377
የአካውንቱ ስም፦ Ediget Ber Feleghiwot Medihanialem (እድገት በር ፈለገ ሕይወት መድኃኒዓለም)
"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና!" (2ኛ ቆሮ. 9:7)
መልዕክቱን ለሌሎች ክርስቲያን ወገኖች በማጋራት (Share) የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!