ኢትዮ ማል ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት

ኢትዮ ማል ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት Ethio Mal-Eso Health charitable Organization

ባለጠጋና ለጋሽ ወጣቶች በመሎ ኮዛ !!የለጋሾች ወይም የበጎ አድራጊዎች ባህርይ እንደየግል ተነሳሽነታቸው ቢለያይም፣ አብዛኛውን ጊዜ ርኅራኄ እና ለሌሎች ማሰብ ለጋሾች የሌሎችን ችግር እንደ ራ...
12/04/2026

ባለጠጋና ለጋሽ ወጣቶች በመሎ ኮዛ !!

የለጋሾች ወይም የበጎ አድራጊዎች ባህርይ እንደየግል ተነሳሽነታቸው ቢለያይም፣ አብዛኛውን ጊዜ ርኅራኄ እና ለሌሎች ማሰብ ለጋሾች የሌሎችን ችግር እንደ ራሳቸው አድርገው የመረዳት ችሎታ አላቸው።

ድጋፍ የሚያደርጉት በግዴታ ሳይሆን፣ በሌሎች ሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት ካላቸው ቅን ፍላጎት በመነጨ ነው።
ማኅበረሰቡን የመርዳትና ያሉትን ሀብቶች ገንዘብ፣ ዕውቀት ወይም ጊዜ ለጋራ ጥቅም የማዋል የሞራል ግዴታ እንዳለባቸው ያምናሉ።
"ካለኝ ላይ ማካፈል አለብኝ" የሚል ጽኑ አቋም አላቸው።
እነዚህ ወጣት ባለጠጋዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ላሃ ከተማ ነዋሪዎች ይገርማል ብርሀኑ እና ሞኮንን ድንቁ ዛሬ ከ100 መቶ ሺህ ብር በላይ ለአቅመ ደካሞች ለግሰዋል። ይህ የሁለቱ ወጣቶች ባህርይ የሀብታሞች ባህርይ ሳይሆን የባለጠጎች ነው።

ወንድሞቼ ይገርማል እና ሞከ ባለጠግነት ከፈጣሪ የሚሰጥ ስጦታ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ መልካም ይሁን እላለው !!
ከናንተ ብዙ እንመራለን።
🇪🇹ወንድማችሁ አለሙ አይሳ

እነዚህ ታዳጊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስከቶ ዞን እና በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ይገኛሉ።  ለነዚህ ታዳጊዎች ተስፋ ለመስጠትና የነገን የህይወት መስመራቸው የተስተካከለ እንዲሆን ኢትዮ ማ...
08/04/2026

እነዚህ ታዳጊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስከቶ ዞን እና በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ይገኛሉ። ለነዚህ ታዳጊዎች ተስፋ ለመስጠትና የነገን የህይወት መስመራቸው የተስተካከለ እንዲሆን ኢትዮ ማል-ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተለያዩ ሆስፒታሎች እና ድርጅቶች ጋር ስሰራ ቆይቷል።

በመሆኑም የሁለቱ ታዳጊዎች የህክምና ድጋፍ የተገኘ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ሚያዚያ 8/2018 ወደ ሆስፒታል መግቢያ ቀጠሮ የተያዘ ሲሆን የመሎ ኮዛ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ,የጎፋ ዞን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መመሪያ ,እና የባስኬቶ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መመሪያ ድጋፍ በማድረግ እንድትተባበሩን መልካም ፍቃዳችሁን እንጠይቃለን።

ተስፋ ለቆረጠ ወይም ተስፋ ለሌለው ሰው ተስፋ መሆን ማለት ትልቅ ሰብአዊነት እና የልብ ቅንነት የሚጠይቅ ተግባር ነው። ይህ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባርና በባህሪ የሚገለጽ ሲሆን፣
ተስፋ የቆረጠ ሰው መጀመሪያ የሚፈልገው የሚሰማው ሰው ነው። ምክር ከመስጠት ይልቅ የሰውየውን ስሜት ሳይፈርዱበት፣ በጥሞና እና በትዕግስት ማዳመጥ ትልቅ እፎይታ ይሰጣል። "እረዳሃለሁ" ወይም "ብቻህን አይደለህም" የሚል ስሜት እንዲሰማው ማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

አብረን እንቆማለን !!

ለበለጠ መረጃ 0911378954

  ሰሞኑን በከባድ ሁኔታ መታመሙን በሚዲያ መግለፁ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ አምና በ2017 ዓ.ም በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት በርካታ ንጹሀን ሰ...
18/12/2025



ሰሞኑን በከባድ ሁኔታ መታመሙን በሚዲያ መግለፁ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ አምና በ2017 ዓ.ም በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት በርካታ ንጹሀን ሰዎች ተቀብረዉ በነበረበት ወቅት ወደ ስፍራዉ ፈጥኖ በመድረስ ራሱን ለጉዳት እስኪያጋልጥ ድረስ ድጋፍ ሲያደርግ ለቆየዉ፣ በበጎ ስራዉ ለሚታወቀው፣ ለባለዉለታቸዉ ለ master abinet kebede ማስተር አብነት ከበደ የቡልቂ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሐሙስ በቀን 09/04/2018ዓ.ም በአደባባይ ወጥተዉ ፀልየዋል።
የቡልቂ ከተማ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ እናቶች እና አባቶች በጋራ በመሆን ማስተር አብነት ከበደን ፈጣሪ እንድምረዉና እንዲፈዉሰዉ በአደባባይ ፀሎት አድርገዋል።

እኛም;- ፀሎታችሁ ይሰማ!! ፈጣሪ ይፈዉሰዉ ብለናል!!

በNetsa Gemeda

‎ምሁራኑ እና የሚዲያ ባለሙያዎች "ማልኤ-ሶን" ለአለም የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለጸ።‎‎ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ‎‎በጎፋ ዞን ካሉ ቱባ ባህሎች አንዱ የሆነው በመሎ ህዝቦች...
18/06/2025

‎ምሁራኑ እና የሚዲያ ባለሙያዎች "ማልኤ-ሶን" ለአለም የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለጸ።

‎ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

‎በጎፋ ዞን ካሉ ቱባ ባህሎች አንዱ የሆነው በመሎ ህዝቦች "ማልኤሶ" ተብሎ የሚጠራው ማር የመጎራረስ የፍቅር መገለጫ ፕሮግራም በአካባቢ ተወላጆችና ምሁራን ተካሂዷል።

‎በፕሮግራሙ ምሁራኑ እና የሚዲያ ባለሙያዎች "ማልኤ-ሶን" ለአለም የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል።

‎ይህ ፕሮግራም በመሎ ህዝቦች ዘንድ በስፋት የሚታወቅና ረጂም ዓመታት እርስበርስ ሳይገናኙ የቆዩ ሰዎች ማርን በመጎራረስ ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ልዩ ባህል ነው።

‎ "ማልኤሶ" ማር በመጎራረስ በጣም የሚዋደዱ ፣ የሚቀራረቡና የሚተማመኑ ሰዎች የእምነትና የመሐላ ምምልክት እንደሆነ ይነገራል።

‎ማልኤሶ የህዝቡን አንድነት የሚያጠናክር በመሆኑ ለትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር የሀገር መሪዎችና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ሚና በመጫወት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሀገር ሽማግሌዎች አሳስበዋል።

‎ከሚያለያዩን ይልቅ አንድነታችንና ፍቅራችን የሚያጠናክሩ ባህላዊ በርካታ እሴቶችን በማጎልበት አካባቢውን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለፁት የሀገር ሽማግሌዎቹ የአካባቢውን ቱባ ባህል በማሳደግ በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ለዓለም ለማስተዋወቅ ትውልዱ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

👉የመሎ ኮዛ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

18/05/2025

ያልተኖረ ልጅነት 😞

ያማል እረ ምን አይነት ዘመን ላይ ነው የደረሰነው😭እኝህ አባት ዛሬ በአክሱም ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ለህልፈታቸው ምክንያት ደግሞ ሀኪሞች የስራ ማቆም ሰልፍ በግቢ ውስጥ እያካሄዱ ስ...
13/05/2025

ያማል እረ ምን አይነት ዘመን ላይ ነው የደረሰነው😭

እኝህ አባት ዛሬ በአክሱም ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ለህልፈታቸው ምክንያት ደግሞ ሀኪሞች የስራ ማቆም ሰልፍ በግቢ ውስጥ እያካሄዱ ስለነበር ነው።

በመጨረሻም የድንገተኛ ክፍል ተረኛ የነበረው ሀኪም ጋወኑን አውልቆ ጠቅልሎ በላያቸው ላይ ጥሎ ዳግም ወደ ህክምና ላይመለስ እያለቀሰ ግቢውን ለቆ ወጣ ። Via፦ቃልኪዳን ዳዊት

Ghion Maleda ግዮን ማለዳ

በናይጀሪያ የ18 አመት ወጣት በአምስት ወር 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ ተገለፀ !በናይጀሪያ አናምብራ ግዛት የ18 ዓመት ወጣት   በ5 ወር ውስጥ ብቻ  የአለቃዉን ሴት ልጅን ጨምሮ 10 ልጃገ...
13/05/2025

በናይጀሪያ የ18 አመት ወጣት በአምስት ወር 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ ተገለፀ !

በናይጀሪያ አናምብራ ግዛት የ18 ዓመት ወጣት በ5 ወር ውስጥ ብቻ የአለቃዉን ሴት ልጅን ጨምሮ 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ እያነጋገረ ይገኛል።

እንደ ዘገባው ከሆነ በናይጀሪያ አናምብራ በተባለችዉ ግዛት ውስጥ ተወላጅ የሆነዉ ታዳጊ የተላከው በአሰሪዉ ስር ስር ሁኖ ሙያ እንዲማር ነበር ሆኖም በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ የመምህሩን ሴት ልጅ እና በሱቁ ውስጥ የምትሰራውን ሻጭ ልጅና ሌሎች 8 ስቶችን አስረግዟል ተብሏል።

እንዴት ብዙ ልጃገረዶችን ማርገዝ እንደቻለ ሲጠየቅ ሁሉንም ሴቶች በቀላሉ በማግባባት በፍቅር እና እንደማይገባቸው ቃል በመግባት በፍቃደኝነት እንዳረገዙለት ገልጿል።

አሰሪዉና መምህሩ ወዲያውኑ ከሙያ ስልጠናው እንዲሰናበት ቢያደርጉትም ይህን አስደንጋጭ ተግባር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመለከቱት የአናምብራ ግዛት የሴቶች እና ማህበራዊ ደህንነት ኮሚሽነር ኢፊ ኦቢናቦ የክልሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግስት በወጣቱ ላይ ክስ እንደሚመሰርትና ሁኔታው ከአቅሟ በላይ ስለሆነ ህዝቡ ምክር እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ሰይፊሻ እግዚአብሔር አምላክ ጨርሶ ይማርህ 🩷!
12/04/2025

ሰይፊሻ እግዚአብሔር አምላክ ጨርሶ ይማርህ 🩷!

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለ...
09/04/2025

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።

ሰላምና ጤና።
Ethio Mal-Eso

ህፃን  ፀጋነሽ አዲሱ  በደቡብ  ኢትዮጵያ  ክልል  በጎፋ  ዞን መሎ  ጋዳ  ወረዳ  ሻማ  ቀበሌ  ነዋሪ  ስትሆን  አይኗን ሊያጠፋ የነገ ተስፋዋ  ወደ መጥፎ  ጨለማ  ሊቀየር  ስም  የሌለ...
04/03/2025

ህፃን ፀጋነሽ አዲሱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን መሎ ጋዳ ወረዳ ሻማ ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን አይኗን ሊያጠፋ የነገ ተስፋዋ ወደ መጥፎ ጨለማ ሊቀየር ስም የሌለው ከባዱ በሽታ ይኸዉ ዓይኗ ላይ ያለከልካይ ቁጭ ብሏል።

ባለፈው ከስድስት ወር ጀምሮ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለች ቢሆንም ቀጣይ የህክምና ሂደት ለማስጨረስ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አጋጥሞናል። በመሆኑ መርዳት እና በአካል ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በመምጣት መጠየቅ የምትፈልጉ ወገኖች በምናስቀምጠው ስልክ አድራሻ ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። እናመሰግናለን !!

እናመሰግናለን !!

ንግድ ባንክ 1000212660896 አስረስ አዲሱ (ታላቅ መንድሟ)

ለበለጠ መረጃ :-አለሙ አይሳ 0911378954

-ከኢትዮ ማል-ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት
አዲስ አበባ

Share በማድረግ እግዙን እናመሰግናለን !!

May peace and health be everywhere.
16/01/2025

May peace and health be everywhere.

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911378954

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ማል ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ኢትዮ ማል ኤሶ ጤና የበጎ አድራጎት ድርጅት:

Share