Commercial Bank of Ethiopia Trade Union

Commercial Bank of Ethiopia Trade Union ማኅበሩ የተመሠረተበት ዓመት :- ታኅሣስ 2 /1960 ዓ ም
የአባላት ብዛት:- ከ 35,000 በላይ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር 69ኛ ዓመታዊ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ፡፡********የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር 69ኛ ዓመታዊ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ...
05/08/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር 69ኛ ዓመታዊ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ተካሄደ፡፡

********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር 69ኛ ዓመታዊ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ከሐምሌ 27–28 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄዷል።

በምክር ቤት ስብሰባው የ2018 ዓ.ም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት፣ የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የበጀት ዕቅድ በሰፊው ተወያይቶባቸው በምክር ቤቱ ጸድቀዋል።

በተጨማሪም ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ወቅታዊ የሠራተኞች ጥያቄዎች የባንካችን ኤክስኩቲቭ ም/ፕሬዘዳንት ኮርፖርት ሰርቪስ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና ም/ፕሬዝዳንት ሰው ሀይል ወ/ሮ እየሩሳሌም አመሃ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ተጠሪ ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ተሰጥቷል።
በዚሁ መሠረት፡-
1ኛ ደረጃ – ንፋስ ስልክ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት
2ኛ ደረጃ – አሰላ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት
3ኛ ደረጃ – ዲላ ተጠሪ ጽሕፈት ቤቶች በመሆናቸዉ እውቅና ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር
"በአንድነት ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!"

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ስፖርት ቡድን እዉቅና ፕሮግራም ተካሄደ፡፡*******በኢሠማኮ የ2018 ዓ.ም የበጋ ወራት ሠራተኞች ዉድድር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ የባንካችን የወንዶች እግር ኳ...
25/07/2026

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ስፖርት ቡድን እዉቅና ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
*******
በኢሠማኮ የ2018 ዓ.ም የበጋ ወራት ሠራተኞች ዉድድር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ የባንካችን የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ላለፉት ስምንት ወራት ሲካሄድ የነበረዉን ዉድድር በአንደኝነት በማጠናቀቅ የዓመቱ ሻምፕዮን መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ዛሬ በባንካችን ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደዉ ፕሮግራም የባንካችን ሰዉ ኃይል ም/ፕሬዝደንት ወ/ሮ እየሩሳሌም አመሀ፣ የማሕበራችን ፕሬዝደንት አቶ አበራ ጌታቸዉ፣ የማሕበራችን ስራ አስፈፃሚ እና ኦዲት አባላት እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት ለስፖርት ቡድን አባላት እዉቅና ፕሮግራም ተካሂዷል።

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድን የኢሠማኮ የበጋ ውድድር ሻምፒዮን ሆነ::***********በኢሠማኮ አዘጋጅነት  ሲካሄድ በቆየው የበጋ ወራት የሠራተኞች ስፖርት ውድድር የተሳ...
19/07/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድን የኢሠማኮ የበጋ ውድድር ሻምፒዮን ሆነ::

***********

በኢሠማኮ አዘጋጅነት ሲካሄድ በቆየው የበጋ ወራት የሠራተኞች ስፖርት ውድድር የተሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድን የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኗል።

የስፖርት ውድድሩ መዝጊያ ፕሮግራም ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን በዕለቱም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ቡድን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድንን 3 ለ1 በሆነ ሠፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

የዉድድሩ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት የኢሠማኮና የፌዴሬሽኑ አመራሮች፣ የማህበራችን አመራሮች፣ የስፖርት ኮሚቴ አባላት፣ የባንኩ ሠራተኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

የስፖርት ቡድኑ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን ለዚህም መላዉን የባንካችንን ማሕበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

ባንካችን የ2025/26 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አደረገ!*****በተደረገው ግምገማ ባንካችን በሁሉም KPI አስደሳች ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል።በጉባኤው ላይ ተሳታፊ የሆነው ማህበ...
14/07/2026

ባንካችን የ2025/26 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አደረገ!

*****

በተደረገው ግምገማ ባንካችን በሁሉም KPI አስደሳች ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል።
በጉባኤው ላይ ተሳታፊ የሆነው ማህበራችን በመላው የባንካችን ሠራተኞችና የስራ መሪዎች በቅንጅት ለተመዘገበው ታሪካዊ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በመላው ሠራተኞች የተገኘውን ውጤት የሚመጥን የቦነስና እርከን ጭማሬ እንዲሁም ሳይከለሱ የቆዩ የሠራተኞች ጥቅማጥቅሞች እንዲከለስ በመላው ሠራተኞች ስም ለባንካችን ጥያቄውን አቅርቧል።

ባንኩ በዓመቱ ለተመዘገበው ታሪካዊ ውጤት መላ የባንካችንን ሠራተኞችና በየደረጃው ለሚገኙ የማህበሩ አመራሮች የእውቅና ዋንጫ አበርክቷል።
ይህ ሽልማት ሠራተኞቻችን ዓመቱን ሙሉ በትጋት ለሠሩት ሥራ የተሰጠ እውቅና ከመሆኑ ባሻገር ለቀጣዩ ዓመት ተግተን እንድንሠራ የተጣለ አደራ ጭምር ነው።
በመሆኑም መላው የባንካችን ሠራተኞች በቀጣይ ዓመት የተያዙትን ዕቅዶች ለማሳካት ከወዲሁ በቁርጠኝነትና በትጋት እንድትሠሩ አደራ እንላለን።

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

የኢትዮጵያ  ንግድ  ባንክ 3ኛዉ ዙር  የአዲሰ አበባ ከተማ አቀፍ የውስጥ  ውድድር  መዝጊያ  ተካሄደ።****** በአዲስ  አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2018 አ ም የውስጥ  ለውስጥ የእግር ኳ...
12/07/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ኛዉ ዙር የአዲሰ አበባ ከተማ አቀፍ የውስጥ ውድድር መዝጊያ ተካሄደ።

******

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2018 አ ም የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ውድድር በሠራተኞችና ማነጅመንት መገናኛ እና የዋናው መ/ቤት የደረሱ ሲሆን በሠራተኞች ዋናው መ/ቤት በማኔጅመንት የመገናኛ ዲስትሪክት አሸናፊ ሲሆኑ የሽብርቅ ዋንጫ ለመገናኛ ዲስትሪክት ተበርክቷል::
ለአሸናፊ ዲስትሪክቶችም የዋንጫ ሽልማት በእለቱ የክብር እንግዳ ም/ኘሬዚደንት የሰዉ ሃይል አስተዳደር ወ/ሮ እየሩሳሌም አማሃ ፣ የኢንባ ሰራተኞች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ጌታቸው እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ለሁሉም ሃላፊዎች በኩል ተበርክቶላቸዋል ።
የውስጥ ለውስጥ መውደድሩም በቀጣይ አመት በሁሉም ዲሰትሪክቶች ለማካሄድ በእቅድ ተይዟል ::

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

02/07/2026
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ የአፈፃፀም መለኪያዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዘገበ።አቶ አቤ ሳኖ  ለተገኘው ውጤት ለባንካችን ደንበኞች ከፍተኛ  ምስጋና አቅርበዋል።**...
01/07/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ የአፈፃፀም መለኪያዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዘገበ።
አቶ አቤ ሳኖ ለተገኘው ውጤት ለባንካችን ደንበኞች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
******

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተመዘገበውን አፈፃፀም በተመለከተ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ባንካችን በተለያዩ የአፈፃፀም መለኪያዎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን የገበያ ድርሻውንም ማሳደግ ችሏል።

ባንካችን ትናንት ባጠናቀቅነው በጀት ዓመት ከ707.4 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ታላቅ ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡ ከ2.4 ትሪልዮን ብር በላይ ተሻግሯል።

በአገራችን ባንኮች ታሪክ ይህን ያህል ተቀማጭ ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ ሲሰበሰብ በታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ከ6 ዓመት በፊት ከነበረው በ4 እጥፍ ማደጉን አመልክተዋል።

ባንካችን ባለፈው በጀትዓመት ከ648.02 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን የገለፁት አቶ አቤ፣ ከ90.7 በመቶ በላይ (588.11 ቢሊዮን ብር) የሚሆነው ብድር ለግሉ ዘርፍ መሰጠቱን ገልፀዋል።

አቶ አቤ በ2019/20 በጀት ዓመት ባንኩ ከሰጠው ብድር ለግሉ ዘርፍ የተሰጠው 10 በመቶ አካባቢ እንደነበር ገልፀው፣ የዘንድሮው አፈፃፀም ባንኩ ለግሉ ዘርፍ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያሳይ ገልፀዋል።

በባንካችን የተሰጠ ጠቅላላ የብድር መጠን 1.64 ትርሊዮን ብር መድረሱንም ነው አቶ አቤ የገለፁት።

ባንካችን በብድር አሰባሰብም ያስመዘገበው ውጤት ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ 546.26 ቢሊዮን ብር ብድር መሰብሰቡን አመልክተዋል።

አቶ አቤ የባንኩ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ከ1.4 በመቶ በታች እንደነበር ገልፀው፣ ይህም ባንካችን በብድር አሰባሰብ ዙሪያ እየሠራ ያለውን ውጤታማ ሥራ እንደሚያመለክት አስረድተዋል።

በውጭ ምንዛሬ ግኝትም በተመሳሳይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የገለፁት አቶ አቤ፣ በዓመቱ ከ5.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በዲጂታል ክፍያ ዘርፍም ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ የገለፁት አቶ አቤ፣ በዓመቱ በ3.48 ቢሊዮን የገንዘብ ዝውውሮች ከ22.24 ትሪሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በባንካችን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች መንቀስቀሱን አስረድተዋል።

የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አፈፃፀም በሀገር ደረጃ 70 በመቶ ድርሻ እንዳለው እና ይህም በዲጂታል ክፍያ ዘርፍ ባንካችን የሀገራችን ዋልታ መሆኑን ያስመሰከረበትእንደሆነ አቶ አቤ አመልክተዋል።

አቶ አቤ ባንካችን በአጠቃላይ የገበያ ድርሻውን ያሳደገበትን አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀው፣ በተቀማጭ ገንዘብ 50.1 በመቶ፣ በብድር 48.3 በመቶ፣ በጠቅላላ ሀብት 50.1 በመቶ እንዲሁም በካፒታል 45.4 በመቶ የገበያ ድርሻ መያዙን አስረድተዋል።

አቶ አቤ ባንካችን ላስመዘገበው የላቀ ውጤት ባንካችንን አምነው አብረው እየሠሩ ያሉ ደንበኞች ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀው ከባንኩ ጋር አብረው ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት አስተዋፅዎ መስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሩ መልክ የሀገር መልክ ነፀብራቅ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ አስቻይ የኢኮኖሚ ሥርዓት በሀገራችን መዘርጋቱ ለተመዘገበው ውጤት ምክንያት በመሆኑ ይህን ላደረገው መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።

በገበያው ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ የላቀውን ድርሻ ለመውሰድ ትልቅ ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅ የገለፁት አቶ አቤ፣ ለመላው የባንኩ ሠራተኞች ትጋት እና ቁርጠኝነት እንዲሁ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የባንካችንን መልካም ነገር ለህዝባችን ለሚያደርሱት የሚዲያ አካላትም ከአቶ አቤ ታላቅ ምስጋና ተችሯቸዋል።

01/07/2026
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ707.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ታሪካዊ አፈፃፀም አስመዘገበ።***********...
01/07/2026

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ707.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ታሪካዊ አፈፃፀም አስመዘገበ።
********************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጠናቀቅነው የ2018 በጀት ዓመት (2025/26 FY) ከ707.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡን ከ2.4 ትሪልዮን ብር በላይ በማድረስ ታሪካዊ ውጤት አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህ ታሪካዊ ውጤት እንዲመዘገብ ላስቻሉት መላው የባንኩ ደንበኞች ታላቅ ምስጋና ያቀርባል!

******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

Address

Addis Ababa
2176

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 18:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Commercial Bank of Ethiopia Trade Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Commercial Bank of Ethiopia Trade Union:

Shortcuts

Share

Category